Monday, October 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናፓርላማው ከዕረፍት መልስ መደበኛ ስብሰባውን ሐሙስ ይጀምራል

ፓርላማው ከዕረፍት መልስ መደበኛ ስብሰባውን ሐሙስ ይጀምራል

ቀን:

– የመንግሥት ሪፖርት በተሰናባቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ስለመቅረቡ ውሳኔ አልተሰጠበትም

የ2010 ዓ.ም ግማሽ የሥራ ዘመኑን መጠናቀቅ ተከትሎ ለዕረፍት ዝግ ሆኖ የከረመው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ከአንድ ወር በኋላ መደበኛ ስብሰባውን ከሐሙስ መጋቢት 6 ቀን 2010 ዓ.ም. እንደሚጀምር የምክር ቤቱ ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ምንም እንኳ ፓርላማው የዕረፍት ጊዜው ከተጠናቀቀበት የካቲት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ መደበኛ ሥራ እንደተመለሰ ታሳቢ ተደርጎ የሚወሰድ ቢሆንም፣ የመጀመርያውን መደበኛ ስብሰባውን ለሐሙስ ዕለት በተያዘው አጀንዳ ላይ በመምከር በይፋ እንደሚጀምር ታውቋል፡፡

በዕለቱም በሚያካሂደው የመጀመሪያው መደበኛ ስብሰባ በአጀንዳነት የሚቀርበውን የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር የ2010 በጀት ዓመት የስምንት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ማዳመጥ መሆኑን፣ ከምክር ቤቱ ለመረዳት ተችሏል።

እስከ ሰኔ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. በሚቆየው ሦስተኛ የሥራ ዘመኑ አጋማሽ የተለያዩ ሕጎችንና አዋጆችን ከማፅደቅ ጎን ለጎን፣ በሕገ መንግሥቱ በተሰጠው አስፈጻሚውን የመንግሥት አካል የመከታተልና የመቆጣጠር ሥልጣንና ተግባር መሠረት የተለያዩ መንግሥታዊ ተቋማትን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቶችን እንደሚያዳምጥ ይጠበቃል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ የሥራ አስፈጻሚውን፣ የሕግ ተርጓሚውን አካል፣ እንዲሁም ለራሱ ለምክር ቤቱ ተጠሪ ናቸው የሚባሉ የዴሞክራሲ ተቋማትን ሪፖርት ማዳመጥና በሪፖርቶች ላይ በመወያት ውሳኔ ማሳለፍን የተመለከቱ ጉዳዮች፣ ለፓርላማው ከተሰጡ ዋና ዋና ኃላፊነቶችና ሥልጣኖች ውስጥ ይገኙበታል፡፡

ባለፈው ወር በምክር ቤቱ አሠራር መሠረት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀርበውን የመንግሥትን የስድስት ወራት ሪፖርት ማዳመጥ የነበረበት ቢሆንም፣ ሪፖርቱ ሳይቀርብ ነበር ለዕረፍት የተበተነው፡፡

ምክር ቤቱ ለዕረፍት በተዘጋበት ወቅት ነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሥራ መልቀቂያ ማቅረባቸውን ያስታወቁት፡፡ ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግሥታቸውን የሥራ ክንዋኔ ሪፖርታቸውን እንደ ከዚህ በፊቱ ያላቀረቡበት ምክንያት ከሥራ መልቀቂያቸው ጋር በመገናኘቱ፣ ወይም በሌላ ምክንያት መሆኑን ለማወቅ የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

ነገር ግን ለምክር ቤቱ በቀጥታ የሚቀርብ ሪፖርትን በተመለከተ በምክር ቤቱ የአሠራርና የአባላት ሥነ ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀጽ 81(3) እንደተደነገገው፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚያዝለት ፕሮግራም መሠረት የመንግሥትን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ አስመልክቶ በዓመት ሁለት ጊዜ ለምክር ቤቱ ሪፖርት ያቀርባል፡፡ ሆኖም መቅረብ የሚገባው ጉዳይ አለ ብሎ ካመነ በማንኛውም ጊዜ ሪፖርት ማቅረብ እንደሚችል ተደንግጓል፡፡

በዚህም መሠረት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርት በተጠናቀቀው ግማሽ ዓመት ይጠበቅ የነበረ ሲሆን፣ የሥራ ዘመኑ ከመጠናቀቁ በፊት ባሉት ቀሪ ጊዜያትም በአካል ተገኝተው ሪፖርቱን ማቅርብ እንደሚጠበቅባቸዋል ይታመናል፡፡ ይሁን እንጂ ሪፖርተር ከምንጮች ለማወቅ እንደቻለው ምክር ቤቱ ከሐሙስ ጀምሮ በሚያካሂዳቸው መደበኛ ስብስባዎች፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለሚያቀርቡት ሪፖርት አጀንዳ አልተያዘም፡፡

እንዲሁም ኢሕአዴግ ተተኪውን ጠቅላይ ሚኒስትር በምክር ቤቱ አቅርቦ ከማሰየሙ በፊትም ሆነ አቶ ኃይለ ማርያም በይፋ ሥልጣናቸውን ከማስረከባቸው በፊት፣ ሪፖርቱን ስለማቅረባቸው ውሳኔ ተደርሶበት በአጀንዳነት እንዳልተያዝ  ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ነገር ግን የተተኪው ጠቅላይ ሚኒስትር ሹመትና አገሪቱን ካለፈው ዓመት ጀምሮ ሲንጣት በቆየው ተቃውሞ ሲፈተን የቆየው የመንግሥትን የሥራ አፈጻጸም የሚመለከተው ሪፖርት፣ ምክር ቤቱ እንደሚያዳምጣቸው ከሚጠበቁ ዓበይት ጉዳዮች ውስጥ ቀዳሚውን ሥፍራ መያዙም እየተነገረ ነው፡፡

ምክር ቤቱ ባለፈው ወር በዕረፍት ላይ በነበረበት ወቅት በአፈ ጉባዔው ለአስቸኳይ ስብሰባ ተጠርቶ ለስድስት ወራት የሚቆየውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የካቲት 23 ቀን 2010 ዓ.ም. ማፅደቁ ይታወሳል፡፡ በ88 ተቃውሞና በሰባት ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ አዋጁ መፅደቁ አይዘነጋም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...