Friday, March 24, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

እናት ባንክ ሁለተኛዋን የቦርድ ሰብሳቢ ሰየመ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

በ11 ሴቶች መሥራችነት የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማጎልበት የተነሳው እናት ባንክ፣ በቅርቡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተቀባይነት ካገኙት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ውስጥ ወ/ሮ ሀና ጥላሁንን የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ በማድረግ መረጠ፡፡ እናት ባንክ ከተመሠረተ ጀምሮ ወ/ሮ ሀና ለባንኩ ሁለተኛዋ ከፍተኛ ኃላፊ ለመሆን በቅተዋል፡፡ 

ከምሥረታው ጀምሮ የእናት ባንክ መሥራችና በመጀመርያዋ የባንኩ ቦርድ ሰብሳቢ በወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ምትክ የተመረጡት ወ/ሮ ሀና፣ በባንኩ ለስድስት ዓመታት በቦርድ አባልነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

የባንኩ ባለአክሲዮኖች በቅርቡ ባደረጉት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ ወቅት ከፍተኛ ድምፅ ካገኙት መካከል ወ/ሮ ሀና አንዷ ሲሆኑ፣ የቀሪዎቹን የቦርድ አባላት ሹመት ብሔራዊ ባንክ ማፅደቁ ይታወሳል፡፡ ከአዲሶቹ የባንኩ ቦርድ አባላት መካከል አቶ ሀብቱ ድምፁ፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ሆነው እንደሰየማቸውም ለማወቅ ተችሏል፡፡ አቶ ሀብቱ የምክትል ቦርድ ሰብሳቢነቱን ቦታ የያዙት የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን አቶ ማንያለው ይልማን በመተካት ነው፡፡

አዲሲቷ የእናት ባንክ ቦርድ ሰብሳቢ፣ በአካውንቲንግ የመጀመርያ ዲግሪ አላቸው፡፡ በሕግ የተመሰከረላቸው የሒሳብ አዋቂም ናቸው፡፡ ወ/ሮ ሀና የኤምኤች ኢንጂነሪንግ የፋይናንስና አስተዳደር አማካሪ፣ በኖሪላ ኢንጂነሪንግና ኮንስትራከሽን ኩባንያ የመምሪያ ኃላፊና ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆን አገልግለዋል፡፡ ቤዛለኩሉ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ኩባንያን በዋና ሥራ አስኪያጅነት እየመሩ ይገኛሉ፡፡ በፋይናንስ ዘርፍ አማካሪነታቸውም ይታወቃሉ፡፡

ምክትል የቦርድ ሰብሳቢው አቶ ሀብቱ በበኩላቸው፣ በልማትና በፕሮጀክት ዕቅድ ትምህርት መስክ የሁለተኛ ዲግሪ፣ በግብርና ምጣኔ ሀብት ሁለተኛ ዲግሪ፣ በልማት ሀብት ከፍተኛ ዲፕሎማ አላቸው፡፡ በፋይናንስ ዘርፉ አማካሪነትም እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተለያዩ ኃላፊነት ደረጃዎች የሠሩት አቶ ሀብቱ የረጅም ጊዜ ልምድ ካካበቱ የዘርፉ ተዋናዮች መካከል አንዱ ናቸው፡፡

እናት ባንክ በአሁኑ ወቅት ያስመዘገበው አጠቃላይ የሀብት መጠን ከአምስት ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል፡፡ የተከፈለ ካፒታሉም ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ሲሆን፣ ከ13 ሺሕ በላይ ባለአክሲዮኖችን ያካተተና ከ36 በመቶ በላይ በሴት ባለአክሲዮኖች ድርሻ የሚተዳደር የግል ባንክ ነው፡፡

 

 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች