Friday, June 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም ግለ ታሪክ ዓርብ ይመረቃል

የልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም ግለ ታሪክ ዓርብ ይመረቃል

ቀን:

በሃያኛው መቶ ዓመት የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በሚኒስትርነት፣ በአውራጃና ጠቅላይ ገዥነት የረዥም ዘመን አገልግሎት የሰጡት ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም ግለ ታሪክ ታተመ፡፡ ‹‹የትውልድ አደራ›› በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን የልዑል ራስ መንገሻ የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ ያሳተመው የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዴሚ ነው፡፡

 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ኢሜሪተስ ፕሮፌሰር ሽፈራው በቀለ አገላለጽ፣ ይህ መጽሐፍ ለታሪክ ጥናት አስተዋፅኦ የሚያደርግ ቀዳማይ ምንጭ ነው፡፡ አንደኛ የመሳፍንት ልጆች አስተዳደግ ላይ ያለንን ግንዛቤ ያበለጽጋል፡፡ ሁለተኛ የጠቅላይ ግዛት አስተዳደርን በሚመለከት በተለይ ለአገራችን የልማት ታሪክ ጥናት አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡ ሦስተኛ ኢዲኅ (የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ኅብረት) አስመልክቶ የልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም ዕይታን ያቀርባል፡፡

መጽሐፉ በአካዴሚው ዋና ጽሕፈት ቤት መጋቢት 7 ቀን 2010 ዓ.ም. ከ9፡00 ሰዓት ጀምሮ እንደሚመረቅ አሳታሚው አስታውቋል፡፡ ጽሕፈት ቤቱ ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ቀጥሉ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍ አለፍ ብሎ ወደ ቀኝ በሚያስገባው መንገድ ይገኛል፡፡

በምረቃ መርሐ ግብሩ የዘመነኛው የዓይን ምስክርነት በደጃዝማች ወልደ ሰማዕት ገብረ ወልድ፤ ሙያዊ አስተያየት በፕሮፌሰር ኢሜሪተስ ገብሩ ታረቀ የሚቀርብ ሲሆን፣ ልዑሉም አጭር ትውስታና ምስጋና እንደሚያቀርቡ ታውቋል፡፡

ልዑል ራስ መንገሻ የአፄ ዮሐንስ አራተኛ ንጉሠ ጽዮን ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ (1864-1881) የልጅ ልጅ፣ ልጅ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ