ጥሬ ዕቃዎች፡-
1.5 ግራም ዶሮ
1 ራስ ቀይ ሽንኩርት
4 ፍሬ ነጭ ሽንኩርት
(1/2) ግማሽ የሻይ ማንኪያ በርበሬ
(1/2) ግማሽ የሻይ ማንኪያ እርድ
(1/2) ግማሽ የሻይ ማንኪያ የተፈጨ ዝንጅብል
4 የሾርባ ማንኪያ የገበታ ቅቤ
1 ፍሬ ሎሚ
ዘይት ለመጥበሻ
ጨውና ቁንዶ በርበሬ
አዘገጃጀት
- በቅድሚያ ኦቨኑን በ3500 ሴንቲ ግሬድ ማሞቅ፣
- ዶሮውን በደንብ ማጠብ፣
- የታጠበውን ዶሮ በደንብ በጨርቅ ማድረቅ፣
- የዶሮውን ቆዳ ዘይት መቀባት፣
- ቀይና ነጭ ሽንኩርቱን፣ ሎሚውን ቆራርጣ የዶሮው ሆድ ውስጥ መክተት፤
- ከቆዳው ሥር ቅቤውን ቆራርጣ ማስገባት፤
- በርበሬ፣ የተፈጨ ዝንጅብል፣ እርድ፣ ጨውና ቁንዶ በርበሬ ቆዳው ላይ ማሸት፤
- በላዛኛ መስሪያ ላይ ዘይት ጨምሮ ዶሮውን ለአንድ ሰዓት ከ45 ደቂቃ ማብሰል፡፡
- ጆርዳና ኩሽና ‹‹የምግብ አዘገጃጀት›› (2007)