Thursday, October 6, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፖርትየወርቅ ጫማ ለአዲሷ የረዥም ርቀት ንግሥት

  የወርቅ ጫማ ለአዲሷ የረዥም ርቀት ንግሥት

  ቀን:

  ከሁለት ሳምንት በፊት ቤጂንግ ባስተናገደችው 15ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአትሌቲክስ የዓለምን ትኩረት ካገኙ ድንቅ አትሌቶች መካከል ትጠቀሳለች፡፡ አትሌት አልማዝ አያና በዚሁ በ15ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ5,000 ሜትር ባስመዘገበችው ድንቅ የአጨራረስ ብቃት፣ አዲዳስ ኩባንያ ያዘጋጀውን የወርቅ ጫማ ሽልማት አሸናፊ መሆኗ ይፋ ሆኗል፡፡

  አዲዳስ ለዚህ ሽልማት ዕጩ አድርጎ ከመረጣቸው ውስጥ እንደ አልማዝ ሁሉ በቤጂንጉ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በዴክታሎን አዲስ ክብረወሰን ያስመዘገበው አሜሪካዊው አሽተን ኤንተና ኔዘርላንዳዊቷ የ200 ሜትር አሸናፊ ዳፍኔ ሸፐርስ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በዚሁ መሠረት ለአትሌቶቹ በተሰጠው ድምፅ ኢትዮጵያዊቷ አልማዝ አያና 23.84 በመቶ፣ አሜሪካዊው አሽተን 17.15 በመቶና ኔዘርላንዳዊቷ ዳፍኔ ደግሞ 14.68 በመቶ አግኝተዋል፡፡ አዲሷ የረዥም ርቀት ንግሥት አልማዝ በሰፊ የድምፅ ልዩነት አሸናፊ ሆናለች፡፡ ሽልማቱም በአዲሱ የውድድር ዓመት ኅዳር ወር ላይ እንደሚበረከትላት ተገልጿል፡፡

   

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img