Monday, February 6, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየህዳሴውን ግድብ እንዲያጠኑ የተመረጡት ኩባንያዎች የቴክኒክ ሰነዳቸውን በቀኑ አላቀረቡም

የህዳሴውን ግድብ እንዲያጠኑ የተመረጡት ኩባንያዎች የቴክኒክ ሰነዳቸውን በቀኑ አላቀረቡም

ቀን:

በታላቁ ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ላይ የቀረቡ ሁለት ጥናቶችን እንዲያጠኑ የተመረጡት የፈረንሣዩ ቢአርኤል ኢንጂነርስና የኔዘርላንዱ ዴልታ ሬዝ ኩባንያዎች የቴክኒክ ሰነዳቸውን ማቅረብ በሚገባቸው ጊዜ ሳያቀርቡ ቀሩ፡፡

የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን ብሔራዊ የቴክኒክ ኮሚቴዎች ባለፈው ወር በአዲስ አበባ ተገናኝተው ኩባንያዎቹ ማለትም የማኔጅመንት ኮንትራት የሚወስደው የፈረንሣዩ ቢአርኤል፣ የተወሰኑ የጥናቱን ክፍሎች ከፈረንሣዩ ኩባንያ የሚወስደው የኔዘርላንዱ ኩባንያ ዴልታ ሬዝ በጋራ ሆነው፣ እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2007 ዓ.ም. የቴክኒክ ሰነዳቸውን እንዲያቀርቡ ጊዜ ተሰጥቷቸው ነበር፡፡

ይሁን እንጂ በተሰጣቸው ጊዜ የቴክኒክ ሰነዱን ለሦስቱም መንግሥታት ብሔራዊ ቴክኒክ ኮሚቴ ሳያቀርቡ ቀርተዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኢንጂነር ጌድዮን አስፋው፣ በሁለቱ ኩባንያዎች በኩል መቅረብ የነበረበት ሰነድ ኩባንያዎቹ መግባባት ባለመቻላቸው ሳያቀርቡ እንደቀሩ ገልጸዋል፡፡

ቢአርኤል የተባለው ኩባንያ የኮንትራት ማኔጅመንቱን ማለትም የሚፈለጉት ሁለት ጥናቶችን ለማጥናት ሕጋዊ ተዋዋይ ሲሆን፣ የጥናቱንም 70 በመቶ እንዲያከናውን በሦስቱም አገሮች ብሔራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡

የኔዘርላንዱ ዴልታ ሬዝ ኩባንያ ደግሞ ከሚፈለጉት ጥናቶች ውስጥ 30 በመቶውን እንዲወስድ ነው የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት የተስማሙት፡፡ በዚህ መሠረት የሥራ ክፍፍል አድርገው የቴክኒክ ፕሮፖዛል እንዲያስገቡ የመጀመሪያ የጊዜ ገደብ የተሰጠው ባለፈው ወር በአዲስ አበባ በተካሄደው የሦስቱ አገሮች የቴክኒክ ኮሚቴ የጋራ ስብሰባ ላይ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ በጉባዔው ላይ መቅረብ ባለመቻሉ ተጨማሪ ማብራሪያ ተሰጥቶ ለነሐሴ 30 ቀን 2007 ዓ.ም. ለሦስቱም አገሮች የቴክኒክ ኮሚቴ የቴክኒክ ሰነዱን እንዲያቀርቡ ቀጠሮ ተይዞ ነበር፡፡

‹‹ሁለቱ ኩባንያዎች ቁጭ ብለው በሚነጋሩበት ወቅት አንዳንድ ያልተግባቡባቸው ነገሮች መኖራቸውን ሰምተናል፡፡ ነገር ግን ያለመግባባቱ ምክንያት ምን እንደሆነ በእርግጠኝነት ማወቅ አይቻልም፤›› ሲሉ ኢንጂነር ጌድዮን ገልጸዋል፡፡

የግብፅ የውኃና መስኖ ሚኒስትሩ በጉዳዩ ላይ ለግብፅ መገናኛ ብዙኃን በሰጡት አስተያየት፣ ‹‹የቴክኒክ ሰነዱ በወቅቱ ባለመድረሱ ደስተኞች አይደለንም፤›› ብለዋል፡፡

የሦስቱ አገሮች ብሔራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት እ.ኤ.አ. በጥቅምት 2015 አጋማሽ ላይ በካይሮ እንደሚገናኙ የገለጹት ኢንጂነር ጌድዮን፣ እስከዚያ ድረስ ኩባንያዎቹ ሰነዱን ሊያቀርቡ እንደሚችሉ ካልሆነም ለመፍትሔው ኮሚቴው ውይይት እንደሚያደርግ አስረድተዋል፡፡

በዋናነት ግን ግብፅ የፈረንሣዩ ኩባንያ ዋናው የጥናቶቹ ተጠያቂ መሆኑን ገልጻ፣ ዴልታ ሬዝ በተባለው ኩባንያ ድርሻ ማነስ ቀደም ብላ የተስማማችበት ቢሆንም አሁን ግን ተቃውሞዋን እያሰማች ትገኛለች፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቤተክህነት ባቀረበችው የይግባኝ አቤቱታ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለዕሮብ ተቀጠረ

የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሀገወጥ ነው በተባለው አዲሱ ሲኖዶስና...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...