ባወጣው መግለጫ፣ ኢትዮጵያ ኤርትራን ለመውረር እያስፈራራች መሆኗን አስታውቋል፡፡ ምንም እንኳ የመረጃው ምንጭ ማን እንደሆነ የኤርትራ መንግሥት ባይናገርም፣ ኢትዮጵያ ኤርትራን ለመውረር ከአሜሪካ ይሁንታ ማግኘቷንና ኢትዮጵያም በይፋ መግለጿን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ምንም እንኳ ከወራት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ኤርትራን በተመለከተ በፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ፣ የኤርትራ መንግሥት ኢትዮጵያንና ሌሎች የጎረቤት አገሮችን ለማተራመስ የያዘውን ስትራቴጂ የማይተው ከሆነ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ተገዶ ዕርምጃ እንደሚወስደና የኢትዮጵያን ሕዝብ እንደሚያሳውቅ መናገራቸው አይዘነጋም፡፡ በወቅቱ የኤርትራ መንግሥት በጉዳዩ ላይ ምንም ሳይል አሁን የኢትዮጵያ ወረራ ያሰጋኛል ማለቱ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ በምሥሉ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ጄኔራል ሳሞራ ዩኑስ በኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ቀን አከባበር ሥነ ሥርዓት በቅርቡ በተካሄደበት ወቅት የሚታዩ ሲሆን፣ ዝርዝር ዘገባው ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡