Friday, September 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህል‹‹ድሩትፃ›› ዘመን መለወጫ በጉሙዝ

‹‹ድሩትፃ›› ዘመን መለወጫ በጉሙዝ

ቀን:

መደበኛው የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ዓመቱን የሚጀምረው መስከረም 1 ቀን ቢሆንም በአገሪቱ ያሉ ልዩ ልዩ ብሔረሰቦች እንደየባህላቸው፣ ትውፊታቸው፣ ልማዳቸው የሚያከብሯቸው የዘመን መለወጫ በዓላት አሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል በምዕራብ ኢትዮጵያ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የሚገኘው የጉሙዝ ብሔረሰብ ነው፡፡ ብሔረሰቡ በዓሉን ‹‹ድሩትፃ›› በማለት ይጠራዋል፡፡ ዘመን መለወጫ እንደማለት ነው፡፡ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን በክልሉ አምስት ብሔረሰቦች ኢንታንጀብል (መንፈሳዊ) ባህላዊ ቅርሶች ላይ ያደረገውን ዳሰሰና ቆጠራ ሰነድ ላይም ድሩትፃን እንዲህ ተመልክቶታል፡፡

በየዓመቱ ከሚያከብራቸው ዓመታዊ ክብረ በዓላት መካከል አንዱና ዋነኛው ድሩትፃ የዘመን መለወጫ) ክብረ በዓል የሚከበረው መስከረም 16 ቀን ሲሆን፣ በዓሉን በደመቀ አኳኋን ለማክበር ቅድመ ዝግጅት የሚጀመረው ሐምሌ ላይ ነው፡፡ በዚህ መሠረት በየሰፈሩ የሚገኙ አባወራዎች የበዓሉን አከባበር የሚያስተባብሩ ሰዎችን ይመርጣሉ፡፡ እነዚህም ከእያንዳንዱ መንደርተኛ የገንዘብ መዋጮ ሲያሰባስቡ ይቆዩና በዓሉ ከመድረሱ አሥራ አምስት ቀናት በፊት እንደተዋጣው የገንዘብ መጠን ከሦስት እስከ አራት የሚደርሱ ከብቶችን ይገዙና በመኖሪያ አካባቢያቸው እየተንከባከቧቸው ይቆያሉ፡፡ ባህላዊ የቦርዴ ጠላ (ኪያ) ይጠመቃል፡፡

እያንዳንዱ አባወራም የባጉሪ (ቡጉሃ) የሚባል ሀገር በቀል እንጨቶችን ከበዓሉ በፊት ቆርጦ ያዘጋጅና ደጃፉ ላይ ያኖራል፡፡ የየሰፈሩ ልጆች (ወንዶች) ራሳቸውን በተለያዩ ቡድኖች ከቦደኑ በኋላ የሚዟዟሩበትን ቤቶች ይከፋፈላሉ፡፡ በእያንዳንዱ ቤት እንደደረሱም ለጋውን የባጉሪ እንጨት አንዱን ለሁለት ወይም ለብቻ እየያዙ ወደ ቤቱ በመግባት በእሳት ላይ ካያያዙት በኋላ ዮሔ፣ ዮሔ እያሉ ያዜማሉ፡፡ ይጨፍራሉ፡፡ ከዚያም ቤት ውስጥ

ትንሽ አረፍ ብለው የቦርዴ ጠላ ይጠጣሉ፡፡ የቤቱ አባወራም ለገሙሳ በማለት ይመርቋቸዋል፡፡ ይህም እግዚአብሔር ያሳድጋችሁ፣ ያኑራችሁ፣ ለዛሬ ዓመትም በሰላም ያድርሳችሁ እንደማለት ነው፡፡ ከዚያም ከአንዱ ቤት ወደ ሌላኛው በመሄድ ሁሉንም በዚህ መልክ ያዳርሳሉ፡፡ በማግስቱ መስከረም 16 ቀን ጠዋት ላይ የሰፈሩ ነዋሪዎች (ወንዶች) ችቦ በእሳት አያይዘው ቀደም ብሎ በየጐጡ ወደተደመረው ደመራ በመሄድ ችቦውን በእጃቸው እንደያዙ ሦስት ጊዜ ደመራውን ከዞሩት በኋላ አዋቂዎች ኤዩውትካ ዴካ (ለሚቀጥለው ዓመት በሰላም ያድርሰን) በማለት ይመርቃሉ፡፡ ከዚያም ሁሉም የያዘውን ችቦ ደመራው ላይ ይጥላል፡፡ ትንሽ አረፍ ተብሎ የቦርዴ ጠላ ይጠጣል፡፡ ቀደም ብለው ለበዓሉ የተገዙትን ከብቶች ወደ ደመራው ቦታ በመውሰድ ያርዳሉ፡፡ እያንዳንዱ እንዳዋጣው የብር መጠንም ሥጋውን ቅርጫ አርገው ይከፋፈሉና ወደየቤታቸው ይዘውት ይገባሉ፡፡ በማግስቱ በ17 ጠዋት የሰፈሩ ነዋሪዎች ከዚሁ ሥጋ ላይ የተወሰነውን (በትንሹ) ይዘው ሰፊ ቤት ወዳለው ግለሰብ ቤት በጋራ በመሆን ይሄዱና ያመጡትን ጥሬ ሥጋ እያበሰሉ አብረው ይመገባሉ፡፡ ሴቶችም ከጠመቁት ቦርዴ ጠላ ድሮ በበገጋ (ቅል) አሁን አሁን ደግሞ በጀሪካን ይዘው ወደዚሁ ሥፍራ ያመጣሉ፡፡ ከወንዶች መካከል አስተናጋጅ ይመረጥና ለእንግዶች በንኳ (የቅል ኩባያ) ላይ ጠላውን እንዲቀዳ ኃላፊነት ይሰጠዋል፡፡ እሱም ቤት ውስጥም ሆነ ውጭ ያሉትን እንግዶች እኩል ማስተናገድ ይጠበቅበታል፡፡ በዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ አዋቂዎች ለገሙሳዲድማ (እግዚአብሔር ይስጣችሁ፣ ለዛሬ ዓመትም በሰላም ያብቃን) ብለው ከመረቁ በኋላ እግረ መንገዳቸውንም ወጣቶች ባህላቸውን እንዲያከብሩና ጠብቀው እንዲያቆዩ፣ እርስ በርስም እንዲዋደዱና እንዲከባበሩ ምክር ይለግሷቸዋል፡፡        

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...