Saturday, March 25, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊአራት ኢትዮጵያውያን በሜድትራንያን ባህር ሰጥመው እንዲሞቱ አድርገዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተከሰሱ

አራት ኢትዮጵያውያን በሜድትራንያን ባህር ሰጥመው እንዲሞቱ አድርገዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተከሰሱ

ቀን:

–  ከ100,000 ብር በላይ ከቤተሰቦቻቸው መቀበላቸው ተጠቁሟል

የማይገባ ጥቅም ከተጐጂዎች ለማግኘትና ለሌሎች ለማስገኘት በማሰብ ወደ አውሮፓ አገሮች እንደሚልኩ በመግለጽ፣ አራት ኢትዮጵያውያን በሕገወጥ መንገድ በጀልባ ተጭነው ሜዲትራንያን ባህር ውስጥ ሰጥመው እንዲሞቱ አድርገዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሁለት ሕገወጥ ደላሎች ተከሰሱ፡፡

በፌዴራል ዓቃቤ ሕግና በፌዴራል ፖሊስ አባላት ከፍተኛ ጥረትና ክትትል በቁጥጥር ሥር ውለው ክስ የተመሠረተባቸው ተጠርጣሪዎች፣ ኡመር ሙሳ አብዱላሂና አብደላ መናን አደም የሚባሉ ሕገወጥ ደላሎች መሆናቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡

ተከሳሾቹ ሱዳን ከሚገኙት አብዱላዚዝ ሁሴንና ታምራት በላቸው፣ እንዲሁም ሊቢያ ከሚገኘው ወንድወሰን ከተባለ ሕገወጥ ደላሎችና ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን፣ ወደ አውሮፓ አገሮች እንደሚልኩ በማግባባትና በማታለል ወንድወሰን አብዲሳ አወል፣ ከድር ይሁኔ፣ ማሜ አማንና አብዱሰላም አብደላ የተባሉትን ኢትዮጵያውያን በጀልባ አሳፍረው ሜድትራኒያን ባህርን እንዲያቋርጡ በማድረጋቸው፣ አራቱም በባህር ውስጥ ሰጥመው እንዲሞቱ ማድረጋቸውን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡

ተከሳሾቹ፣ በሜዲትራንያን ባህር አቋርጠው ጣሊያን እንደሚገቡ ሟቾቹን በማግባባትና በማታለል ወደ ሱዳንና ሊቢያ እንዲሄዱ ካደረጉ በኋላ፣ ሱዳንና ሊቢያ ሲደርሱ ወደ ቤተሰቦቻቸው በመደወል ለእነሱ (ለደላሎቹ) ገንዘብ ካልተላከ በኮንቴይነር አሽገው እንደሚያስቀምጧቸው በመግለጻቸው፣ ከእያንዳንዳቸው ቤተሰቦች 17,000 ብር በድምሩ 68,000 ብር በባንክ በኩል ማስላካቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡ የአብዲሳ አወል ቤተሰቦች እንደገና እንዲልኩ በማስገደድ ተጨማሪ 32,000 ብር መቀበላቸውንም ክሱ ያክላል፡፡ ተከሳሾቹ በሱዳንና ሊቢያ ካሉ ካልተያዙ ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን በፈጸሙት ሰውን በሕገወጥ መንገድ ይዞ ማስቀመጥና ዋና የወንጀል ተካፋይ በመሆን ወንጀል ተከሰዋል፡፡

ሙሐመድ አህመድ ሐሰን የተባለ ሌላ ተጠርጣሪም ብሩክ ካሳ የተባለ ግለሰብን ግብረ አበሮቹ ሊቢያ ውስጥ ከከተማ ውጪ የሆነ ቦታ ላይ አስረው እንዲያሰቃዩት ማድረጉን የተመሠረተበት ክስ ይገልጻል፡፡ ተከሳሹ ለብሩክ አባት ስልክ በመደወል ‹‹ልጅህ ሊቢያ ታስሯል፡፡ በአስቸኳይ በእኔ የባንክ ሒሳብ ቁጥር 32,000 ብር አስገባ፡፡ ካላስገባህ ግን አይለቀቅም፡፡ ካስገባህ ግን ደውዬ እንዲለቀቅ አደርጋለሁ፤›› በማለት ገንዘቡን እንዲያስገቡ በማድረጉ፣ በፈጸመው ሰውን በከባድ ሁኔታ ከሕግ ውጪ ይዞ ማስቀመጥ ወንጀል ተከሷል፡፡       

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኩባንያ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ባንኮች ውጤታማነት

የጠቅላላ ጉባኤ፣ የጥቆማና ምርጫ ኮሚቴ፣ የተቆጣጣሪ ቦርድ፣ የዳይሬክተሮች ቦርድና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...