Sunday, March 3, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትኢንተርናሽናል ሴቶች ዳኞች ለእግር ኳስ ፌዴሬሽን ጥያቄ አቀረቡ

ኢንተርናሽናል ሴቶች ዳኞች ለእግር ኳስ ፌዴሬሽን ጥያቄ አቀረቡ

ቀን:

በዓለም አቀፍ ደረጃ የእግር ኳሱን ዕድገት ተከትሎ የሴቶች ተሳትፎም በዚያው መጠን እየተጠናከረ መጥቶ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መታየታቸው ይታወቃል፡፡ በእግር ኳሱ ሌላው የሴቶች ተሳትፎ የሚታየው ደግሞ በዳኝነት ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያቱ ኢንተርናሽናል የእግር ኳስ ዋናና ረዳት ዳኞች ይጠቀሳሉ፡፡ እነዚህ ዳኞች ከሁለት ዓመት በፊት ይዳኙ የነበረውን የፕሪሚየርና ብሔራዊ ሊግ የወንዶች እግር ኳስ ጨዋታን ከ2006 የውድድር ዓመት ጀምሮ እንዳይዳኙ መደረጉን ይገልጻሉ፡፡ ለዚህ ክልከላ መሠረት የሆነው የወንዶችን መዳኘት የሚያስችል ዓለም አቀፍ መስፈርትን ማሟላት ቢሆንም፣ ዓለም አቀፉ ሕግስ ቢሆን የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ግንዛቤ ውስጥ የሚያስገባ መሆን የለበትም ወይ? የሚል ጥያቄ ያነሳሉ፡፡ ፌዴሬሽኑ በበኩሉ ሕጉ መስፈርቱን በብቃት ለሚያሟሉ ሁሉ እኩል የተቀመጠ በመሆኑ ክልከላ ሊባል እንደማይችል ይገልጻል፡፡

የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ሆነ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ቀደም ብለው ይፋ ያደረጉት የእግር ኳስ ዳኝነት መስፈርት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከ2006 የውድድር ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ ያደረገው ቢሆንም፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የወጣ እንዳልሆነ የሚናገሩት እነዚሁ ኢትዮጵያውያት የእግር ኳስ ዳኞች፣ መስፈርቱ እያለም ማለትም ከ2006 በፊት በነበሩ የውድድር ዓመታት ያውም የአገሪቱ እግር ኳስ አሁን ከሚገኝበት የተሻለ ደረጃ ላይ በነበረበት ወቅት ሳይቀር የወንዶችን ጨዋታ በዋና ዳኝነት ሳይቀር ሲዳኙ መቆየታቸውን ይናገራሉ፡፡ አሁንም ቢሆን ችግራቸው የመስፈርቱ መቀመጥ ወይም አለመቀመጥ ሳይሆን ተፈጻሚነት እንዲኖረው ሲደረግ ግን የአገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገባ ቢሆን የተሻለ ከመሆኑም በላይ የጋራ ተጠቃሚ ሊያደርጋቸው እንደሚችል ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሴቶች የእግር ኳስ ዳኞች መኖራቸው ይታወቃል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ በቅርቡ ካናዳ ባስተናገደችው የሴቶች የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ላይ አራተኛ ዳኛ በመሆን አራት ጨዋታዎችን የመዳኘት ዕድሉን ያገኘችው ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ሊዲያ ታፈሰን ጨምሮ ጽጌ ሲሳይ፣ ጌራወርቅ ተሰማና ፍቅረ ገነት አላምኔ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኞች ሲሆኑ፣ በረዳት ኢንተርናሽናል ዳኝነት ደግሞ ወጋየሁ ዘውዱ፣ ወይንሸት አበራና ማህሌት አስራት ይጠቀሳሉ፡፡ በተለይ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ ኢኳቶሪያል ጊኒ ያስተናገደችውን ስምንተኛው የአፍሪካ የሴቶች እግር ኳስ ዋንጫ ጨምሮ በመላው አፍሪካ የሴቶች እግር ኳስ ጨዋታዎችን በመዳኘት ትታወቃለች፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት ሲስተር ሳራ ሰይድ በበኩላቸው፣ መስፈርቱ እንደ ሕግ የመቀመጡ አግባብነት ባያከራክረንም፣ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ግን ሴቶች የእግር ኳስ ዳኞቻችን በፕሪሚየር ሊጉም ሆነ በብሔራዊ ሊጉ አራተኛ ዳኛ በመሆን እየተመደቡ በመሥራት ላይ ናቸው፤›› ብለዋል፡፡ ከዚሁ ጐን ለጐንም ‹‹ሊዘነጋ የማይገባው›› የሚሉት ኃላፊዋ፣ የወንዶችን እግር ኳስ ለመዳኘት የተቀመጠውን መስፈርት ማሟላት የሚችሉ ካሉ ዳኝነት መብታቸው መሆኑንና በአገሪቱ ከሚገኙት ሴቶች ኢንተርናሽናል ዳኞች ውስጥ ጽጌ ሲሳይ ሁለት ጊዜ ፈተናውን ወስደው እንዳልተሳካላቸው ጭምር ገልጸዋል፡፡ በቀጣይም ዕድሉ እንደሚኖር ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...