Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ሥነ ፍጥረትባለ አስገራሚ ድምፁ ወፍ

ባለ አስገራሚ ድምፁ ወፍ

ቀን:

‹‹ሉን›› በመባል የሚጠራው ወፍ አስገራሚ ድምፅ አለው ይሉታል፡፡ ይህ ወፍ የሚገኘው በካናዳ፣ በአውሮፓና በሰሜናዊ ዩናይትድ ስቴትስ ባሉ ሐይቆችና ወንዞች አቅራቢያ ሲሆን፣ ኮሽታ በማይሰማባቸው በእነዚህ አካባቢዎች ድምፁ ከርቀት ያስተጋባል። ጆሮ ጭው የሚያደርገው የሉን ጩኸት በቀላሉ ከአዕምሮ አይጠፋም ብሎ የዘገበው የጄደብሊው ድረ ገጽ በንቁ ዕትሙ ውስጥ ነው። 

በውኃ አካላት አካባቢ የሚኖረው ሉን በአሜሪካ የሚኒሶታ ግዛት መለያ ምልክት ነው፡፡ ሉኒ በተባለው የካናዳ ባለ አንድ ዶላር ሳንቲም ላይም ሥዕሉ ይገኛል። ይህ ወፍ ከቦታ ቦታ የሚፈልስ ሲሆን፣ የቅዝቃዜውን ወቅት የሚያሳልፈው በስተ ደቡብ ባሉ አገሮች ነው።

ሉኖች  አስደናቂ የሆኑ የተለያዩ ድምፆችን ማውጣት ይችላሉ። ምሽት አካባቢ ወይም ማታ ላይ የሚያሰሙት የማላዘን ዓይነት ድምፅ ነው፡፡ ወንድና ሴት ሉኖች እርስ በርስ ለመግባባት አሊያም ከጫጩቶቻቸው ወይም ከሌሎች ሉኖች ጋር ለመነጋገር እንደ ጉጉት ዓይነት ድምፅ ያወጣሉ። አደገኛ ሁኔታ ሲኖር የሚያሰሙት የማስጠንቀቂያ ድምፅም አለ፤ እንደ ማስካካት ያለው ይህ ድምፅ ‹‹የእብደት ሳቅ›› ተብሎም ተገልጿል።  ሉኖች በሚበሩበት ጊዜ የሚያሰሙት ድምፅም አለ፡፡

ሉኖች ቀጭንና ወፍራም ድምጾችን እያከታተሉ በማውጣት የሚያሰሙት ድምፅም አለ። እንዲህ ያለውን ድምፅ የሚያወጡት ተባዕቶቹ ብቻ ሲሆኑ፣ በርድ ዎች ካናዳ  የተባለው መጽሔት እንደገለጸው፣ ይህን የሚያደርጉት ‹‹የመኖሪያ ክልላቸውን ለማስከበር ነው፡፡ እያንዳንዱ ተባዕት የራሱ የሆነ የተለየ ድምፅም ያወጣል። የወፉ ክብደት በጨመረ መጠን ድምፁም ጎርናና ይሆናል፡፡ የመኖሪያ አካካቢ ሲቀይርም ድምፁን ይለውጣል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...