ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ያዘጋጀው 15ኛው ‹‹ቅድሚያ ለሴቶች›› የ5 ኪሎ ሜትር የሴቶች የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር መሰንበቻውን በአዲስ አበባ ተካሂዷል። ‹‹ከጥቃት ነፃ ሕይወት መብቴ ነው›› በሚል መሪ ቃል በተካሄደው በዚህ ውድድር 12 ሺህ ሴቶች ተሳትፈውበታል፡፡ በውድድሩ ፀሐይ ገመቹ፣ ደባሽ ኪላልና የኔነሽ ጥላሁን ከአንድ እስከ ሦስት ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል፡፡ እንደየደረጃቸው ከ15 ሺሕ እስከ 7500 ብር ተሸልመዋል፡፡ ውድድሩ በየዓመቱ ሲካሄድ የኢትዮጵያውያን ሴቶች ስኬት ለማክበርና እውቅና ለመስጠት እንዲሁም ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ማርች ኤይትን (የካቲት 29) ታሳቢ በማድረግ ነው። ፎቶዎቹ የውድድሩን ገጽታ በከፊል ያስቃኛሉ፡፡
ፎቶ ሚካኤል ተወልደ