ጥሬ ዕቃዎች
450 ግራም የጥጃ ሥጋ
የፈረንጀ ቃርያ
1ራስ ዝኩኒ
4 ፍሬ ድንች
3 ራስ ካሮት
1 ራስ ቀይ ሽንኩርት
50 ሚሊ ሊትር ወይን ጠጅ የቡና ስኒ
2 ብርጭቆ የአትክልት ማጣፈጫ ሾርባ
3 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
ጨው እና ቁንዶ በርበሬ
አዘገጃጀት
- የጥጃ ሥጋውን በረዣዥሙ ማቆራረጥ፤
- ቀይ ሽንኩርት እና ነጭ ሽንኩርቱን በደቃቁ መክተፍ፤
- በደቃቅ አራት መዓዘን የፈረንጅ ቃሪያ፣ ዝኩኒ፣ ድንች እና ካሮት መከታተፍ፤
- በትልቅ ድስት ዘይት አግሎ የጥጃ ሥጋውን በደንብ መጥበስ፤
- ከተጠበሰ በኋላ ሥጋውን ማውጣት፤
- ሥጋ በተጠበሰበተ ድስት ውስጥ ቀይ ሽንኩርቱንና ነጭ ሽንኩርቱን ማቁላላት፤
- የተከታተፈውን ካሮት፣ ዝኩኒ፣ የፈረንጅ ቃሪያ እና ድንቹን አስገብቶ ለተጨማሪ አሥር ደቂቃ ማቁላላት፤
- የተጠበሰውን ሥጋ አስገብቶ ማደበላለቅ፤
- ወይን ጠጅ እና የሾርባ ማጣፈጫውን ጨምሮ ለ20 ደቂቃ ማብሰልና ማውረድ፡፡
- ጆርዳና ኩሽና ‹‹የምግብ አዘገጃጀት›› (2007)