Friday, June 2, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት የዶክመንቴሽን ክፍልና የፋይል ካቢኔቶች ታሸጉ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

–  ድርጅቱ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰወር ተጠርጥሯል

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የመንግሥት የልማት ድርጅትየሆነውን የኢትዮጵያ ውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት፣ የዶክመንቴሽን ክፍልና የፋይል ካቢኔቶችን አሸገ፡፡

ባለሥልጣኑ የድርጅቱን የሥራ ክፍሎች ያሸገው መስከረም 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በውጭ ግዢ፣ በተለያዩ ማሽኖችና ተሽከርካሪዎች ኪራይ፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ ገቢና ከሚያገኘው የአክሲዮን ትርፍ ገቢ ጋር በተያያዘ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ ባለማሳወቅ ተጠርጥሮ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የድርጅቱ የሒሳብ ሥራ ኬዝ ቲም አስተባባሪ ወይዘሮ አልታዬ ገብረየስ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው፣ መስከረም 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በፖሊስ ተይዘው ላምበረት በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ካደሩ በኋላ፣ መስከረም 6 ቀን 2008 ዓ.ም. ፍርድ ቤት መቅረባቸው ታውቋል፡፡

በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የካ ምድብ ተረኛ ችሎት መስከረም 6 ቀን 2008 ዓ.ም. በቀረቡት ተጠርጣሪዋ ላይ ፖሊስ የሚሠራው ተጨማሪ ምርመራ እንዳለው ገልጾ፣ 14 ተጨማሪ ቀናትን የጠየቀ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ አልተቀበለውም፡፡

ተጠርጣሪዋ ወይዘሮ አልታዬ ፖሊስ ያቀረበባቸውን የተጨማሪ ቀናት ጥያቄ በመቃወም ለፍርድ ቤቱ ሲያስረዱ፣ ጉዳዩ በፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን የተያዘና የድርጅቱም የዶክመንቴሽንና የፋይል ካቢኔቶች በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የታሸጉ በመሆናቸው፣ ፖሊስ በእሳቸው ላይ የሚያካሂደው ተጨማሪ ምርመራ ባለመኖሩ ጥያቄው ውድቅ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የተጠርጣሪዋን አቤቱታ በመቀበል በስድስት ሺሕ ብር ዋስ ከእስር እንዲፈቱ አዟል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች