Monday, March 20, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትማሞ ወልዴ በአፍሪካ ጨዋታዎች የነሐስ ሜዳሊያ ያገኘው በ5,000 ሜትር ወይስ በ10,000?

ማሞ ወልዴ በአፍሪካ ጨዋታዎች የነሐስ ሜዳሊያ ያገኘው በ5,000 ሜትር ወይስ በ10,000?

ቀን:

‹‹የአፍሪካውያን ኦሊምፒክ›› የሚል ቅፅል ስም ያተረፈው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ዘንድሮ 50ኛ ዓመቱን ደፍኗል፡፡ የወርቅ ኢዮቤልዩንም የመጀመሪያውን ጨዋታዎች በሐምሌ 1958 ዓ.ም. ያዘጋጀችው ኮንጎ ብራዛቪል ዳግመኛ ለማስተናገድ በቅታበታለች፡፡

ኢትዮጵያ ከአንደኛው ጀምሮ እስከ ዘንድሮ በተካሄዱት 11ዱም ጨዋታዎች ለመካፈል የበቃች ሲሆን ውጤታማም ሆናበታለች፡፡ ሰሞኑን በተጠናቀቀው 11ኛው ጨዋታ በ11 ስፖርቶች ተሳትፋ 7 ወርቅ፣ 5 ብርና 10 ነሐስ በድምሩ 22 ሜዳሊያዎች አግኝታለች፡፡ በተለይ አንደኛው ወርቅ በወርልድ ቴኳንዶ በሴቶች መገኘቱ ልዩ አድርጎታል፡፡ በአትሌቲክሱ እንደተለመደው አሽናፊነቱም እንደቀጠለ ነው፡፡

ይሁን እንጂ አትሌቶቻችን የሚያስመዘግቡት ወርቃማ ድል ያህል ስፖርታዊውንም ሆነ ኦሊምፒካዊውን ታሪክ በአግባቡ እየተመዘገበ ነው ወይ? የሚል ጥያቄ ሲነሳ ግን ክፍተቱ ጎልቶ ይታያል፡፡ በስህተትም እየታጀበ ይገኛል፡፡

የዘንድሮውን የኮንጎ ብራዛቪል ጨዋታዎች አስመልክቶ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው ለሚዲያዎች ‹‹የአፍሪካውያን ኦሊምፒክ ቅኝ ግዛትና የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች›› በሚል ርእስ ባሠራጨው መግለጫው፣ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ በአፍሪካ ጨዋታዎች ያገኘችው በማሞ ወልዴ በ10,000 ሜትር ነበር ብሏል፡፡

‹‹ታላቅ እና ልባዊ ምስጋና ለሻምበል ማሞ ወልዴ ይድረሰውና በኦሊምፒክ ሻምበል አበበ ቢቂላ በሮም ኦሊምፒክ ለሀገሩና ለአፍሪካ በማራቶን የመጀመሪያውን ወርቅ እንዳመጣ ሁሉ፣ ሻምበል ማሞ ወልዴም በመላው አፍሪካ ጨዋታዎች እ.ኤ.አ 1965 ለኢትዮጵያ በ10 ሺ ሜትር የመጀመሪያውን የነሐስ ሜዳሊያ ያስገኘ ድንቅ አትሌት ነበር፡፡››

የመግለጫው ስህተትነት የሚነሳው በመጀመሪያው ጨዋታ ባልነበረ ውድድር 10,000 ሜትር ማሞ ወልዴ በሦስተኛነት የነሐስ ሜዳሊያ አገኘ መባሉ ነው፡፡ በየአራት ዓመቱ ጨዋታዎቹ በመጡ ቁጥር በሚዘጋጁ መጽሔቶች ይኸው ስህተት ሲደጋገም ይታያል፡፡ ኦሊምፒክ በመጣም ቁጥር ቀደም ባሉት ሕትመቶች ስህተት መከሰቱ አልቀረም፡፡

የሮም ኦሊምፒክ ባለድሉ አበበ ቢቂላ በክብር እንግድነት በተገኘበት የመጀመሪያው የኮንጎ ብራዛቪል ጨዋታ ማሞ ወልዴ ኬንያውያኑን ኪፕ ኬይኖና ናፍታሊ ቲሙን ተከትሎ 3ኛነትን ያገኘው በ5,000 ሜትር ነበር፡፡

በወቅቱ ለወንዶች የነበሩት ውድድሮች 100 ሜትር፣ 200 ሜትር፣ 400 ሜትር፣ 800 ሜትር፣ 1500 ሜትር፣ 5000 ሜትር፣ 3000 ሜትር መሰናክል፣ 110 ሜትር መሰናክልና 400 ሜትር መሰናክል፣ እንዲሁም ውርወራና ዝላይ ነበሩ፡፡ ማሞ ወልዴ በ5,000 ሜትር ባገኘው ነሐስ ሜዳሊያ ኢትዮጵያን በአትሌቲክስ የደረጃ ሰንጠረዥ 12ኛ፣ ላይ ባጠቃላይ ስፖርት 18ኛ ላይ ማስቀመጡ ይታወሳል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ዜጎች የተፈተኑበት የኑሮ ውድነት

በኢትዮጵያ በየጊዜው እየተባባሰ የመጣው የኑሮ ውድነት የበርካታ ዜጎችን አቅም...

በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚደረጉ ድጋፎች ዘላቂነት እንዲኖራቸው ተጠየቀ

በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚደረጉ ድጋፎች ዘላቂነት እንዲኖራቸውና በተቀናጀ መልኩ...

ወደ ኋላ የቀረው የሠራተኞች ደኅንነት አጠባበቅ

በአበበ ፍቅር ለሠራተኞች የሚሰጠው የደኅንነት ትኩረት አናሳ በመሆኑ በርካታ ዜጎች...