Monday, October 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትብሔራዊ ቡድኑ ለዓለም ዋንጫና ቻን ላለበት የማጣሪያ ጨዋታ ዝግጅት ጀመረ

ብሔራዊ ቡድኑ ለዓለም ዋንጫና ቻን ላለበት የማጣሪያ ጨዋታ ዝግጅት ጀመረ

ቀን:

–    ቡድኑ መስከረም 19 ከቦትስዋና ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መስከረም 19 ቀን 2008 ዓ.ም. ከቦትስዋና ጋር ለሚያደርገው የወዳጅነት ጨዋታው፣ እንዲሁም ለ2018 የዓለም ዋንጫና ለ2016 የአፍሪካ አገሮች የእግር ኳስ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ዝግጅት ጀመረ፡፡ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ 19 ተጨዋቾች ለዝግጅት ሆቴል ገብተዋል፡፡

በዚሁ መሠረት በግብ ጠባቂነት ታሪኬ ጌትነት፣ ለዓለም ብርሃኑና አቤል ማሞ ሲሆኑ፣ ተከላካይዎች ሥዩም ተስፋዬ፣ ተካልኝ ደጀኔ፣ አስቻለው ታመነ፣ አንተነህ ተስፋዬ፣ ሙጂብ ቃሲምና ዘካሪያስ ቱጂ ናቸው፡፡
አማካይዎች ኤፍሬም አሻሞ፣ ጋቶች ፓኖም፣ ሙሉዓለም መስፍን፣ ብሩክ ቃልቦሬ፣ ቢኒያም በላይ፣ በረከት ይስሃቅና አስቻለው ግርማ ሲሆኑ፣ በአጥቂነት ደግሞ ባዬ ገዛኸኝ፣ ዳዊት ፈቃዱና ራምኬሎ ሎክ ናቸው፡፡ እንደ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ መግለጫ ከሆነ መስከረም 11 ቀን 2008 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ስታዲዮም በተከናወነው የኢትዮጵያ ክለቦች ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ላይ ጥሩ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ተጨዋቾች በተጨማሪነት ጥሪ የሚደረግላቸው መሆኑም ገልጿል፡፡
በሌላ በኩል በ2008 ውድድር ዓመት የሚደረገው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት መስከረም 18 ቀን 2008 ዓ.ም. በይፋ እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡ የውድድር ዓመቱ መደበኛ ውድድርም ጥቅምት 18 ቀን ይጀመራል ተብሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...