Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ተጠቃሚዎችና እግረኞች ላይ ለሚደርስ አደጋ ኢንሹራንስ ተገባ

በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ተጠቃሚዎችና እግረኞች ላይ ለሚደርስ አደጋ ኢንሹራንስ ተገባ

ቀን:

– በተሳፋሪ እስከ 100 ሺሕ ብር ዋስትና ተሰጥቷል

ባለፈው እሑድ ይፋ የትራንስፖርት አገልግሎት ከምኒሊክ አደባባይ ቃሊቲ ድረስ መሰጠት ለጀመረው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት ተጠቃሚዎችና ሦስተኛ ወገኖች፣ የመድን ዋስትና (ኢንሹራንስ) መስጠቱን የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ምክትል ሥራ አስፈጻሚ አቶ ነፃነት ለሜሳ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የባቡር መሠረተ ልማት ግንባታው ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የመድን ዋስትና ከኢትዮጵያ መድን ድርጅት መገባቱን ገልጸዋል፡፡

ፕሮጀክቱን ሙሉ በሙሉ አጠናቆ የማስረከብ ኃላፊነት (turn key contract) የፈረመው የቻይና ባቡር ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ፕሮጀክቱን ሙሉ በሙሉ እስኪያስረክብ ድረስ ዋስትና እንደገባ አስታውሰዋል፡፡ ይሁን እንጂ ፕሮጀክቱ ከሞላ ጎደል በአሁኑ ወቅት ተጠናቆ ወደ ሥራ እየገባ በመሆኑ፣ ተጨማሪ የመድን ሽፋኖችን ለማቅረብ መስከረም 7 ቀን 2008 ዓ.ም. መፈራረማቸውን ገልጸዋል፡፡

በአዲሱ የዋስትና ስምምነት የተካተቱት ተሳፋሪዎች፣ ሦስተኛ ወገኖች (እግረኞችና ንብረቶች) እንዲሁም ባቡሩ ራሱ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የመድን ዋስትና ስምምነቱ የተፈጸመው የትራንስፖርት አገልግሎቱን ለሦስት ዓመት ተኩል ለመስጠት ከተፈራረመው ሼንዘን ሜትሮ ግሩፕ ጋር መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በስምምነቱ መሠረት አንድ ባቡር እስከ ሦስት መቶ መንገደኞች እንደሚያሳፍርና በተሳፋሪዎች ላይ ለሚደርስ አደጋ በአንድ ተሳፋሪ እስከ 100 ሺሕ ብር የሚደርስ የመድን ዋስትና መገባቱን፣ አቶ ነፃነት ገልጸዋል፡፡ በእግረኞች ላይ ለሚደርስ አደጋም በአንድ እግረኛ የ100 ሺሕ ብር የመድን ሽፋን መገባቱን ተናግረዋል፡፡

በንብረት ላይ ለሚደርስ አደጋም ተመሳሳይ ዋስትና መሰጠቱን የገለጹት አቶ ነፃነት፣ እንደ አደጋው ዓይነት እስከ አንድ ሚሊዮን ብር የሚደርስ ዋስትና እንደተገባ ገልጸዋል፡፡

አደጋው በአንድ ጊዜ በተሳፋሪና በሦስተኛ ወገን ላይ የሚደርስ ከሆነ ደግሞ እስከ ሁለት ሚሊዮን ብር የሚደርስ ዋስትና እንደተገባ ገልጸዋል፡፡

የመድን ዋስትና ውሉ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ሲሆን፣ በየሦስት ወራት የሚገመገም መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ከትኬት ሽያጭ ጋር በተያያዘ የትኬት መሸጫ ሱቆች ላይ ለሚደርስ አደጋ ዋስትና እንደተገባ አስረድተዋል፡፡

አጠቃላይ የግንባታ ሥራው ሲጠናቀቅ ደግሞ የጠለፋ ዋስትና በመስጠት የትራንስፖርት መቆጣጠሪያ ማዕከሎችንና ዴፖዎችን በዋስትና እንዲሸፈኑ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሔኖክ ቦጋለ ይህንኑ አረጋግጠዋል፡፡   

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ከፍተኛ የመንግሥት ፕሮጀክቶችን የመድን ሽፋን የመስጠት አቅም ያዳበረ መንግሥታዊ ድርጅት ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም የተገነቡ የውኃ ኃይል ማመንጫዎችን፣ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን፣ በአሁኑ ወቅትም ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመድን ሽፋን ሰጥቷል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...