Thursday, September 21, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልኢትዮጵያዊው ፊልም በፈረንሳይ

ኢትዮጵያዊው ፊልም በፈረንሳይ

ቀን:

‹‹ላምብ›› (ዳንግሌ) በካንስ ፊልም ፌስቲቫል ላይ የተሳተፈ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ፊልም ሲሆን፣ ከሁለት ሳምንት በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ለዕይታ በቅቷል፡፡

በያሬድ ዘለቀ ተፅፎ የተዘጋጀው ‹‹ላምብ››፣ ኤፍሬም በተባለ ታዳጊ ላይ ያተኮረ ፊልም ነው፡፡ ጩኒ የተባለችው የበግ ግልገል የኤፍሬም ብቸኛ ጓደኛ ናት፡፡ አባቱ ራቅ ወዳለ ስፍራ በመሔዱ ከዘመዶቹ ጋር ለመኖር ይገደዳል፡፡ ዘመዶቹም ጩኒን ለዓመት በዓል ለማረድ ይወስናሉ፡፡ ኤፍሬም የጩኒን ሕይወት ለመታደግ የሚያየውን ውጣ ውረድ ፊልሙ ያስቃኛል፡፡

ፍራንስ 24 እንደዘገበው፣ ፊልሙ በፈረንሳይ ፊልም ኢንዱስትሪ ተወዷል፡፡ ጋናዊቷ የፊልሙ ፕሮዲውሰር አማ አምፓዱ ‹‹የላምብን ጽሑፍ መጀመሪያ ሳነበው ፊልሙ በፈረንሳይ ተመልካች እንደሚያገኝ ተገንዝቤአለሁ፤›› ብለዋል፡፡ ፈረንሳውያን ተመልካቾች የአፍሪካን ሲኒማ እየወደዱ መምጣታቸውንም ያክላሉ፡፡

ፊልሙን በብሔራዊ ቴአትር ከተመለከቱ ኢትዮጵያውያን አንዱን ያነጋገረው ፍራንስ 24 የወጣቱን ሀሳብም አካቷል፡፡ ወጣቱ ዳንኤልም መለስ፣ ‹‹ፊልሙ ለንግድ ብቻ የተሠራ አለመሆኑን ወድጄዋለሁ፤ ለእኔ ትውልድ ከአዲስ አበባ ውጪ ወዳለው የገጠር ሕይወት የወሰደን ፊልም ነው፤›› ብሏል፡፡

‹‹ላምብ›› ያሬድ በኒውዮርክ ፊልም ትምህርት ቤት ስኩል ይማር በነበረበት ወቅት የተዘጋጀ ጽሑፍ ነበር፡፡ ሲጀመር 20 ገጽ የነበረው ጽሑፉን ወደ ፊልም እንዲያሳድግ ሐሳብ ያቀረቡት ከያሬድ መምህራን አንዱ ነበሩ፡፡

የፊልሙ ጽሑፍ እ.ኤ.አ. በ2012 በአሚኤንስ ፊልም ፌስቲቫል ላይ ባገኘው ገንዘብም ሊሠራ ችሏል፡፡ ፕሮዲውሰሯ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚቀረጽ፣ ትኩረቱን በሕፃናትና እንስሳት ላይ ያደረገ ፊልም ለመሥራት ገንዘብ ለማግኘት ቀላል እንዳልነበረ ያስረዳሉ፡፡

እ.ኤ.አ. በ2013 የፊልሙ ጽሑፍ ሲኤንሲ አውክስ ሲኒማስ ዱምንዴ ከተባለ ድርጅትና ከፈረንሳዊ ፊልም አከፋፋዮች ድጐማ አገኘ፡፡ ይህም ፊልሙ ገበያ ሊያገኝ እንደሚችል እንዳመላከታቸው ፕሮዲውሰሯ ያስረዳሉ፡፡ እንደ ፍራንስ 24 ገለጻ፣ ለፊልሙ በአጠቃላይ 1.5 ሚሊዮን ብር በጀት ማግኘት ተችሏል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2014ም ቀረጻው በኢትዮጵያ ተጀምሯል፡፡ ለፊልሙ ቀረጻ የሚሆኑ መሣሪያዎች ከፈረንሳይ፣ ጀርመንና ኬንያ ተወስደዋል፡፡

ያሬድ በበኩሉ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ አቅም ያለው የፊልም ኢንዱስትሪ ቢኖርም ዓለም አቀፍ ትኩረት የሚስብ ፊልም ለመሥራት የብዙ ዓለም አቀፍ ባለሙያዎችን ርብርብ ይጠይቃል ይላል፡፡

ፊልሙ ኢትዮጵያ ውስጥ ከተቀረጸ በኋላ አርትኦቱና ሌሎችም ሥራዎች የተጠናቀቁት ከኢትዮጵያ ውጪ ነበር፡፡ በፊልሙ ቀረጻ በዘርፉ ተሞክሮ ያላቸው ባለሙያዎች በመሳተፋቸው ለሀገር ውስጥ ባለሙያዎች ትምህርት እንዳስገኘም ተገልጿል፡፡

‹‹ላምብ›› ካገኘው ዓለም አቀፍ ዕውቅና በተጨማሪ ‹‹ድፍረት›› የተሰኘው ፊልም በሰንዳንስ ፊልም ፌስቲቫል ላይ የወርልድ ሲኒማቲክ ድራማቲክ አውዲየንስ ሽልማት አግኝቷል፡፡

ያሬድ በበኩሉ፣ ‹‹የሀገሪቱ የፊልም ዘርፍ በገንዘብ፣ በቴክኒክና በፈጠራ ካልጐለበተ ብዙ ፊልሞች ከሀገር ውስጥ ሊወጡ አይችሉም፤›› ብሏል፡፡ ፊልሙ በተለያዩ ሀገሮች የሚታይ ሲሆን፣ ለበርካታ ዓለም አቀፍ የፊልም ውድድሮች እንደሚታጭም ይጠበቃል፡፡ ‹‹ላምብ›› በሚመጣው ወር በፈረንሳይ ከታየ በኋላ በዴንማርክ፣ ሜክሲኮ፣ ታይዋንና ሌሎችም አገሮች ይቀርባል፡፡    

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...