Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናመንግሥት የጠቀለላቸውን ኃላፊነቶች ለአዲስ አበባ እንዲመልስ ሐሳብ ቀረበ

መንግሥት የጠቀለላቸውን ኃላፊነቶች ለአዲስ አበባ እንዲመልስ ሐሳብ ቀረበ

ቀን:

በአዲስ አበባ ከተማ የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ማሻሻያ ለማምጣት፣ የፌዴራል መንግሥት የወሰዳቸውን ኃላፊነቶች ለአዲስ አበባ መመለስ እንዳለበት ምክረ ሐሳብ ቀረበ፡፡

በጉዳዩ ላይ ጥናት ያከናወነው የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የጋራ ማስተር ፕላን ጽሕፈት ቤት ሲሆን፣ ጽሕፈት ቤቱ መስከረም 12 ቀን 2008 ዓ.ም. ከንቲባ ድሪባ ኩማ በተገኙበት ጥናቱን አቅርቧል፡፡

ጥናቱን ያቀረቡት ለረጅም ዓመታት በአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮና በከንቲባ ጽሕፈት ቤት በኃላፊነት የሠሩት አቶ አበበ ዘልዑል ናቸው፡፡

አቶ አበበ በአሁኑ ወቅት የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የጋራ ማስተር ፕላን ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ሆነው በመሥራት ላይ ይገኛሉ፡፡

አቶ አበበ ባቀረቡት ጽሑፍ ምሳሌዎች በመጥቀስ አስረድተዋል፡፡ እሳቸው እንዳሉት፣ በትራንስፖርት ዘርፍ በተለይ የአሽከርካሪዎች ማሠልጠኛ ተቋማትና የመናኸሪያዎች አስተዳደር ለክልሎች የተሰጠ ሥልጣን ነው፡፡

ነገር ግን በአዲስ አበባ ከዚህ የተለየ መሆኑን  አቶ አበበ ተናግረው፣ በዘርፉ ያለውን ችግር በተሻለ ለመፍታት እነዚህ ተቋማት ሊመለሱ እንደሚገባ ተከራክረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የአዲስ አበባ ገቢዎች ባለሥልጣን ሙሉ በሙሉ የፌዴራል መንግሥት ተቋም ወደሆነው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ተዛውሯል፡፡

አቶ አበበ እንዳሉት፣ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ወደ ፌዴራል ቢሄድም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጀት ይመድብለታል፡፡ ‹‹ይህ አሠራር ትክክል አይደለም፤›› በማለት የአሠራር ማሻሻያ ማድረግ እንደሚገባ ሐሳብ አቅርበዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ዝርዝር ማብራሪያ ባይሰጥበትም፣ በድፍኑ አዲስ አበባ የፌዴራል መንግሥት የድጎማ በጀት ማግኘት እንዳለበት ተጠቅሷል፡፡

የፌዴራል መንግሥት ከአዲስ አበባ በስተቀር ድሬዳዋን ጨምሮ ለዘጠኙም ክልሎች የድጎማ በጀት በፌዴሬሽን ምክር ቤት አማካይነት ያከፋፍላል፡፡ በአቶ ብርሃነ ዴሬሳ ይመሩ ከነበረው የባለ አደራው አስተዳደር ጀምሮ፣ አዲስ አበባ ድጎማ ሊሰጣት እንደሚገባ ሲጠየቅ ቢቆይም እስካሁን የተገኘ ምላሽ ግን የለም፡፡

በቀረበው ምክረ ሐሳብ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ይገኝበታል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ ኃይል ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤት እንዲያቋቁም ተጠይቋል፡፡ ኅብረተሰቡ በኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ከፍተኛ ቅሬታ ያለው ከመሆኑም በላይ፣ ከመሠረተ ልማት ተቋማት ጋር መናበብ ባለመቻሉ ችግር እየተፈጠረ መሆኑ ተገልጿል፡፡ አስተዳደሩ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋማትን በቀጥታ ማዘዝ ባለመቻሉ በራሱ መንገድ ለውጥ ማምጣት አልቻለም፡፡ የአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ ኃይል ቅርንጫፍ ቢኖር ግን የኅብረተሰቡን ችግር በመፍታት በኩል አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የአዲስ አበባ የመሠረተ ልማት ተቋማት ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን፣  መንገዶች ባለሥልጣን፣ እንዲሁም የኤሌክትሪክ ኃይል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ከተቋቋመ ደግሞ ሦስቱ መሥሪያ ቤቶችን ከአዲስ አበባ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ጋር በማቀናጀት የተናበበ ሥራ ማካሄድ ያስችላል ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚያካሂዳቸው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታም ሆነ ኮንዶሚኒየም ቤቶችን ለተጠቃሚዎች በማስተላለፍ ሒደት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ዋነኛ ችግር ነው፡፡ በቅርቡ 35 ሺሕ ቤቶችን በዕጣና ለልማት ተነሺዎች ቢደርሱም፣ ቤቶቹን ለማስረከብ ከፍተኛ ችግር የሆነው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እንደሆነ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት አስተዳደሩ የ39 ሺሕ ኮንዶሚንየም ቤቶች ግንባታን ከ90 በመቶ በላይ ቢያደርስም፣ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ባለመሟላቱ ዕጣ ለማውጣት ከፍተኛ እንቅፋት መፍጠሩን የአስተዳደሩ ከፍተኛ ባለሥልጣን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡    

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...