Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በትራንስፖርት እጥረት ችግር ተፈጠረባቸው

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በትራንስፖርት እጥረት ችግር ተፈጠረባቸው

ቀን:

በአዲሱ የትምህርት ዘመን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ ተመደቡባቸው ተቋማት ለመጓጓዝ ችግር ተፈጠረባቸው፡፡ ወደተለያዩ ሥፍራዎች በዓላትን ለማክበር በሚጓዙ ሰዎች ምክንያት የትራንስፖርት እጥረትና መጉላላት ሊፈጠር እንደሚችል ሥጋት መኖሩ ተገለጸ፡፡

አብዛኛዎቹ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎቻቸውን በተመሳሳይ ጊዜ ለምዝገባ መጥራታቸው፣ ለመስቀል በዓል ከሚጓጓዙና የአረፋን በዓል በየክልሎች አክብረው ከሚመለሱ ዜጎች ጋር ተደምሮ ችግሩ ሊባባስ እንደሚችል፣ የፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ሥጋቱን ገልጿል፡፡

ሪፖርተር ያነጋገራቸው የባለሥልጣኑ አገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት ስምሪት ክትትል ቡድን መሪ አቶ እንደሻው ጎሹ ግን፣ እስከ መስከረም 14 ቀን 2008 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ ድረስ ምንም እጥረት እንዳልተፈጠረ፣ ቀደም ብሎ በነበረው ዝግጅት መሠረት አገልግሎቱ ተቀናጅቶ እየተሰጠ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

‹‹ነገር ግን በቀጣዮቹ ቀናት ሊፈጠር ከሚችለው እጥረት አኳያ ከፍተኛ ሥጋት አለብን፤›› ብለዋል፡፡ ለዚህ ሥጋት መነሻ ነው ያሉት ከመስከረም 16 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት ቀናት ከአሥራ ዘጠኝ በላይ ዩኒቨርሲቲዎች አዲስ ተማሪዎቻቸውን በተቀራራቢ ቀናት በየተቋማቱ እንዲገኙ መጥራታቸው ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ከፍተኛ ጫና መፈጠሩ እንደማይቀር አስረድተዋል፡፡ ችግሩ የሚባባስ ከሆነ ለተማሪዎቹ ቅድሚያ በመስጠት በመደበኛ የትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ላይ የተወሰነ ጫና ሊፈጠር እንደሚችልም አቶ እንዳሸው ገልጸዋል፡፡ የመስቀል በዓልን ተከትሎም ሆነ ከአረፋ በዓል በኋላ በርካታ ሰዎች ከወትሮው በተለየ ሁኔታ የሚንቀሳቀሱ ቢሆንም፣ በመናኸሪያዎች አካባቢ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት እየተሞከረ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ሌላው ‹‹ትልቁ ሥጋት›› ነው ያሉት ደግሞ የግሸን ማሪያም በዓልን ለማክበር በሚደረግ ጉዞ ሳቢያ የሚኖረውን ጫና ነው፡፡ ይህንን ሲያስረዱም፣ ‹‹የግሸን ማሪያም በዓል ብቻውን ከ500 በላይ ተሽከርካሪዎች ይፈልጋል፡፡ የዚህ ጉዞ ትልቁ ችግር ደግሞ ተሽከርካሪዎች አድርሰው በዚያው ቀን መመለስ አለመቻላቸው ነው፡፡ ከአምስት ቀናት እስከ አንድ ሳምንት የሚቆዩ በመሆኑ ተጨማሪ ጫና ሊፈጥር ይችላል ብዬ እሠጋለሁ፤›› ሲሉ የቡድን መሪው ገልጸዋል፡፡

በአገር አቋራጭ ትራንስፖርት አገልግሎት መስክ 870 ደረጃ አንድ እና 400 ደረጃ ሁለት ተሽከርካሪዎች አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡

አሁን ያለው የትራንስፖርት አቅርቦትና ፍላጎት ያልተጣጣመ በመሆኑ፣ ሌሎች አማራጮችን ለመጠቀም እየተሞከረ መሆኑንም አቶ እንደሻው አስረድተዋል፡፡ አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች የራሳቸውን አውቶቡሶች በመላክ ተማሪዎቻቸውን ለማጓጓዝ እየሞከሩ እንደሆነ ገልጸው፣ እስከ መስከረም 14 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ ሰባት ዩኒቨርሲቲዎች ነፃ አገልግሎት እንደሰጡ አስታውሰዋል፡፡

የትራንስፖርት እጥረቱ በተደጋጋሚ በመከሰቱ ምክንያት መንግሥትን የሚተቹ አካላት በተለይ ከትራንስፖርት አመራር፣ እንዲሁም መንግሥት በዘርፉ የግል ባለሀብቶችን በበቂ መጠን እንዲገቡ አለማበረታታቱን በመጥቀስ ተጠያቂ ሲያደርጉት ይደመጣል፡፡ በሌላ በኩል በአገልግሎቱ ተሳታፊ የሆኑ ጥቂት የግል አጓጓዦችም በአብዛኛው ከተጓዦች ብዛት ጋር ባለመጣጣማቸው አስቸኳይ አገልግሎት መስጠት አልቻሉም፡፡ ለአብነት ያህል ሰላም ባስና ስካይ ባስ በጉዞ መስመሮቻቸው ተሳፋሪዎችን ለማስተናገድ ከአሥር እስከ 12 ቀናት ወረፋ በማስጠበቅ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...