Monday, May 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናተጠርጣሪው የኦሮሚያ ባለሥልጣን ከግለሰቦች ከ10.5 ሚሊዮን ብር ጉቦ መቀበላቸው ተገለጸ

ተጠርጣሪው የኦሮሚያ ባለሥልጣን ከግለሰቦች ከ10.5 ሚሊዮን ብር ጉቦ መቀበላቸው ተገለጸ

ቀን:

– በተጠረጠሩበት የነፍስ ግድያ መርማሪዎችና ዓቃቤ ሕግ መመሳጠራቸው ተጠቆመ

የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ባለሥልጣን አቶ ወንድሙ ቢራቱን በተጠረጠሩበት ከባድ የሙስና ወንጀል በቁጥጥር ሥር አውሎ እየመረመራቸው የሚገኘው የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን፣ ሰሞኑን ባካሄደው ምርመራ ተጠርጣሪው ከግለሰቦች 10.5 ሚሊዮን ብር ጉቦ የተቀበሉበትን ሰነድ መሰብሰቡን ገለጸ፡፡

መርማሪ ቡድኑ ከግለሰቦች ጉቦ ለመቀበላቸው የምስክሮችን ቃል መውሰዱን አክሏል፡፡ ተጠርጣሪው በሕገወጥ መንገድ ከቀረጥ ነፃ ተሽከርካሪዎችን በሌሎች ግለሰቦች ስም ማስገባታቸውን የጠቆመው መርማሪ ቡድኑ፣ ተሽከርካሪዎቹን ማሳገዱን አስረድቷል፡፡

የኮሚሽኑ መርማሪ በድን ባለፉት ሳምንታት ባካሄደው ምርመራ፣ ተጠርጣሪው በተጠረጠሩበት የነፍስ ግድያ ወንጀል በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖችና በአዲስ አበባ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን መሰብሰቡን ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ አቶ ወንድሙ በነፍስ ግድያ ተጠርጥረው እያለ፣ መርማሪዎችና ዓቃቤ ሕግ ተመሳጥረው ወደ ምስክርነት እንዲዛወሩ ማድረጋቸውንም የሚያስገነዝብ ማስረጃ መሰብሰቡን ገልጿል፡፡

ቀደም ብሎ እንደሚያከናውናቸው ከገለጻቸው የምርመራ ሥራዎች ውስጥ በተጠርጣሪው ላይ በጉምሩክ ተጀምሮ የነበረውንና በመመሳጠር ተቋርጦ የነበረውን ጅምር የምርመራ መዝገብ ከጉምሩክ መቀበሉንም ገልጿል፡፡ ሐሰተኛ ሰነድ እያሳተሙ በተለያዩ ከተሞች ሲፈጽሙ የነበረውን ግብር የመሰብሰብ ድርጊት የሚያስረዱ ምስክሮችን እያፈላለገ እንደሚገኝ መርማሪ ቡድኑ ገልጿል፡፡

የኮሚሽኑ መርማሪ ቡድን ጨምሮ እንደገለጸው፣ ለተጠርጣሪው ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ የመንግሥት ግብርን እንዲሰበስቡ ደረሰኝ አትሞ ከሰጣቸው ግለሰብ የምስክርነት ቃል መቀበል ይቀረዋል፡፡ ሌሎች ለመንግሥት መግባት የነበረባቸውን የተጨማሪ እሴት ታክስና ግብር ለማስቀረት ጉቦ የተቀበሉበትን የባንክ ሰነድ መሰብሰብና ተጨማሪ የሰው ማስረጃ መሰብሰብ ይቀረዋል፡፡

ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የሰው ማስረጃ ቃል መቀበሉን፣ ተጨማሪ የሰነድ ማስረጃ መሰብሰብ እንደሚቀረውና ሎሎች ተፈላጊ ተጠርጣሪዎችን አድኖ መያዝ እንዳለበት ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ ጉቦ ሲቀበሉና ሲያቀብሉ የነበሩበት የባንክና ሌሎች ሰነዶችን ከመጠቀም በተጨማሪ፣ በሥልጣን ዘመናቸው ሲያጠራቅሙ የነበረውን ተጨማሪ የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ ሀብት ማፈላለግ እንደሚቀረው ለፍርድ ቤቱ ገልጾ፣ ይኼንን ለሚያከናውንበት ተጨማሪ 14 ቀናት እንዲፈቀዱለት ጠይቋል፡፡

የተጠርጣሪው ጠበቃ መርማሪ ቡድኑ ያቀረበውን ተጨማሪ ጊዜ በመቃወም፣ እስካሁን ያደረገው ምርመራ በቂ መሆኑንና ተጨማሪ ምርመራ እንደማያስፈልግ በማስረዳት፣ የደንበኛቸው የዋስትና መብት እንዲጠበቅላቸውና ከእስር እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡

መርማሪ ቡድኑ ግን ቀሪ ምርመራ እንደሚቀረው ማስረዳቱን በማስታወስ ዋስትናውን ተቃውሟል፡፡

ተረኛ ችሎቱ የግራ ቀኙን ክርክር ካደመጠ በኋላ፣ የተጠርጣሪውን ጠበቃ አቤቱታ ውድቅ በማድረግ ለመርማሪ ቡድኑ የሰባት ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ፈቅዷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመስቀል አደባባይ የመግቢያ ክፍያ ለምን?

ወጣቶች፣ ሕፃናትና አረጋውያን ሳይቀሩ መንፈሳቸውን የሚያድሱበት እንዲሁም ሐሳባቸውን በነፃነት...

በሕገ መንግሥቱ የተዋቀረው ‹‹የብሔር ፖለቲካ›› እና ‹‹ሥርዓቱ›› ያስከተለው መዘዝና መፍትሔው

(ክፍል አራት) በዓቢዩ ብርሌ (ጌራ) ባለፈው ጽሑፌ (በክፍል ሦስት) አሁን ያለው...

የኢትዮጵያ ኅብረተሰብና የመንግሥት መሪ ምሥል

በበቀለ ሹሜ በ2015 ዓ.ም. መጋቢት ወር ውስጥ ይመስለኛል በ‹ሸገር ካፌ›...

ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ያደረገው አዋጅ የፍትሐዊነት ጥያቄ አስነሳ

በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ስምንት ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ በማድረግ ተቋማዊና...