Friday, June 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን የዋጋ ግሽበት የሚፈጥሩ ነጋዴዎችን ፍርድ ቤት አቆማለሁ አለ

የሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን የዋጋ ግሽበት የሚፈጥሩ ነጋዴዎችን ፍርድ ቤት አቆማለሁ አለ

ቀን:

በገበያ ውስጥ ያለ በቂ ምክንያት የሸቀጦች የዋጋ ግሽበት ፈጥረዋል የተባሉ የንግድ ድርጅቶችን ወደ ሕግ ለመውሰድ መረጃ እየተጠናቀረ መሆኑን፣ የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

በዘጠኙ ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ምግብ ነክና ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ የመጣ ሲሆን፣ የዋጋ ጭማሪው ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የለውም የሚል አቋም የያዙ የንግድ ቢሮዎች ለግሽበቱ ተጠያቂ ናቸው ያሏቸውን ድርጅቶችና ነጋዴዎች እየለዩና መረጃም እያሰባሰቡ መሆኑ ታውቋል፡፡

የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ እንዳልካቸው ፀጋዬ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በወንጀል የሚጠየቁትን ፖሊስና ዓቃቤ ሕግ፣ በፍትሐ ብሔር የሚጠየቁትን ደግሞ ባለሥልጣኑ ወደ ሕግ ለማቅረብ መረጃ እየተጠናቀረ ነው፡፡

መንግሥት በድጎማ ከሚያቀርባቸው ዘይት፣ ስኳርና ዱቄት በስተቀር ሌሎች ሸቀጦች በገበያ ዋጋ የሚመሩ ናቸው፡፡ አቶ እንዳልካቸው እንዳሉት፣ በገበያ ዋጋ መመራት የነበረባቸው ሸቀጦች ምንም ዓይነት ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ሳይኖር ሆን ተብሎ በሚደረግ አሻጥር ዋጋቸው ንሮ ተገኝቷል፡፡

ለዚህ ሕገወጥ ተግባር ተጠያቂ የሚሆኑት መረጃ ተሰብስቦ እንዳለቀ ወደ ሕግ የሚወሰዱ መሆኑን፣ ጥፋተኛ ሆነው በሚገኙት ላይ ከአጠቃላይ ሽያጫቸው አሥር በመቶ እንደሚቀጡ መደንገጉን አቶ እንዳልካቸው አስረድተዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ አድርገዋል የተባሉ 23 የብረታ ብረት ነጋዴዎች፣ 15 አስመጪዎች፣ 16 የእንስሳት የመድኃኒት አስመጪና አከፋፋዮች፣ 19 የሰው መድኃኒት አስመጪና አከፋፋዮችና ሰባት ቆርቆሮ አምራቾች ወደ ሕግ መወሰዳቸው ተገልጿል፡፡

አቶ እንዳልካቸው እንዳሉት፣ የእነዚህ አካላት ጉዳይ በሕግ ሒደት ላይ ነው፡፡ ወቅታዊ ሁኔታዎችን በመጠቀም ዋጋ የሚጨምሩ፣ የምርት ዝውውር የሚገድቡ፣ ምርት የሚያከማቹ፣ በመደበኛ የንግድ መስመር ምርት የማያቀርቡ፣ በኅብረት በመነጋገር (በአድማ) ዋጋ የሚተምኑ ነጋዴዎች መኖራቸው መታወቃቸውን ጠቁመው፣ በእነዚህ አካላት ላይ የሚካሄደው ምርመራ እንደተጠናቀቀ ለሕግ እንደሚቀርቡ አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ