Friday, December 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

መስከረም 16 ቀን 2008 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ የተከበረውን ደመራ

ትኩስ ፅሁፎች

መስከረም 16 ቀን 2008 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ የተከበረውን ደመራ የታደሙት የኢትዮጵያው ብፁዕ ወ ቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ፣ ፓትሪያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ እና የግብፁ ብፁዕ ወ ቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ ዳግማዊ፣ ፓትሪያርክ ዘመንበረ ማርቆስ ፖፕ ዘ እስክንድርያ

ኢትዮጵያ የቀለንቶን (ካሌንደር)

ሀብታም አዲሱ ዓመት መጣ!! አዲስ ምድር!! አዲስ ተስፋ…..የኔ አገር ዘመኗን የምትቀይረው ወረቀት ላይ አይደለም፡፡ ዘመኗ ከተፈጥሯ የተመሳጠረ ነው፡፡ እውነቷን ተፈጥሮ ትጋራታለች፡፡ የጠፋች ወፍ ዳግም የምትታይበት፣ አስፈሪ አፍላግ አደብ የሚገዛበት፣ እንደ ሰከረ ሰው ዓይን ገላው የደፈረሰ ኩሬ ጋቢ የሚመስልበት የሆነ አስማት፤ አስማተኛ አገር፣ አስማታዊ የዘመን ቀመር፤ አሉ እንጂ ወረቀት ላይ ዘመን የሚቀይሩ፣ ከበረዶ ወደ በረዶ፣ በረዶው ሲያልፍ በረዶ ሲመጣ፣ የጥላሁን ገሰሰ ክረምት አልፎ በጋ ዘፈን የማያውቁ፤ ደግሞ አንዳንዱ አለ ከኔም አገር ቀን መቁጠር ጥበብ የማይመስለው፡፡ የዚህን ዓይነቱ ሰው ሞኝነት እንደ ክረምቱ ጭጋግ ይግፈፍለት፡፡ አሥራ ሦስት ወር ያለው አገር የለም፡፡ በእርግጥ አሥራ ሦስተኛ ወርን ሠርቶ የወር ደመወዝ የተነፈገ ሕዝብ የሚኖርበት አገርም የለም፤ ከእኛ ውጪ…. መስከረም የብዙ ነገራችን መልክ ነው፡፡ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ገጽ ከመስከረም አዲስ የተስፋ ምስጢር ጋር ይመሳጠራል፡፡ መስኩ በአደይ ያሸበርቃል፡፡ አደይ ሳይመቻት ቀርታ አገሬ ተራቁታ አታውቅም፡፡ ለመስከረም ቢጫ ልብስን የምትጎናጸፍ አገር ከእኔ አገር ውጪ ያለ አይመስለኝም፡፡ ቢኖርም አልኮራበትም….የምኮራበትን አደይ በየዓመቱ እዘፍነዋለሁ፡፡ ብዙው ያላወቀው ትልቅ ጉድ የኔ አገር የቀለንቶን (ካሌንደር) ሀብታም መሆኗን ነው፡፡ ሲዳማ የራሱ ቀን አቆጣጠር፣ የራሱ የሥነ ከዋክብት ልኬት ጥበብ አለው፡፡ ፊቼ ጫምባላላ የሲዳማ ዘመን መለወጫ ነው፡፡ ጠንባሮ በሪ ወሊሶ ይለዋል የዘመን ቀመሩን የጠንባሮ አዲስ ዓመት መጋቢት ነው፡፡ ኮንሶ ደግሞ አለላችሁ በወርሀ ጥር ዘመኑን የሚቀይር፤ የያም ኢልቅ የስልጤዎች የዘመን መለወጫ ነው፡፡ መሰሮ ይሉታል ሰኔ ወርን የስልጤ አዲስ ዓመት ሰኔ ወር፡፡ በመስከረም ዘመን የሚቀይሩት ጊዲቾዎች የቀን ቀመራቸው ከጨረቃ ስሌት ጋር ይቆራኛል፡፡ ደግሞ ጳግሜን አምስት ቀን አለችላችሁ የዳውሮዎች ዘመን መለወጫ ቶክቢያ ይሉታል፡፡ መስከረም የዚህች ሀብታም የቀለንቶን ምድር የወል ፌሽታ ነው፡፡ የጋራ እሴት መሆኑን ከዳር ዳር በአደይ ውበት እውነት ይታወጃል፡፡ የመስቀልና የእሬቻ ጥላ መስከረም ለእኔ አገር ዘመን መለወጫ ብቻ አይደለም ከዓለም አገሬን የለያት ድንቅ የፈጣሪ ስጦታም ነው፡፡ የሀገሬ ሰው……. መስከረም ሲጠባ አደይ ሲፈነዳ እንኳን ሰው ዘመዱን ይጠይቃል ባዳ ይላል፡፡ ባዳ የሚጠይቅበት መስከረም፡፡ መስከረም ከጉጌ እስከ ዶርዜ መንደር፣ ከአምበርቾ እስከ ቱላ ሰገነት፣ ከዘቢዳር እስከ ዳሞታ በመስቀል በዓል ይናወጣሉ፡፡ የሸካ ጥቅጥቅ ደኖች፣ የቤንች ፏፏቴዎች፣ የማጂ ተራራዎች የካፋ ውብ መልከዓ ምድር፤ መስከረም የሁሉም ነው፤ ለሁሉም ነው፡፡ ከጉና ጫፍ እስከ ባሌ….ከጎዴ አናት እስከ ጋምቤላ…..ከአቡነ ዮሴፍ እስከ ቧሂት…. ከአክሱም ጫፍ እስከ ጅንካ…ከአሲምባ ካራ ማራ… ከዳሉል እስከ ራስ ደጀን ምድር የምታጌጥበት… ደዴሳ…. ግዮን… አዋሽ…. ባሮ…. ኦሞ…. ግቤ…. ጎጀብ…. ተከዜ…. ዋቤ… ገናሌ የአገሬ ወንዝ በርበሬ ከመምሰል እፎይ የሚልበት፣ ለምለም ወር… የቀለንቶን ሀብታሟ አገሬ ልዩ ስጦታ መስከረም፡፡

  • የሔኖክ ስዩም የጉዞ በረከት

********************

ኮንዶም ሠርቃለች ያላትን ልጁን የገደለው አባት ፍርድ ቤት ቀረበ

አብዱላህ ካህን የተባለ የ51 ዓመቱ አባት ኮንዶም ሠርቃለች ያላትን የ19 ዓመት ልጁን አንቆ በመግደሉ ፍርድ ቤት መቅረቡን ዴይሊ ሜይልን በመጥቀስ ዘ ኢንዲፔንደንት ዘግቧል፡፡

ከባለቤታቸው ጋር ፍርድ ቤት የቀረቡት የታዳጊዋ እናት፣ ልጃቸው ለቀናት ከቤት መጥፋቷንና በአለባበስ ምክንያት ከቤተሰብ ጋር ፀብ ውስጥ ገብታ እንደነበር ለፍርድ ቤት ተናግረዋል፡፡ በዚህ መልኩ ልጃቸው ለሪብ ከቤት ውጭ ባደረችበት ምሽት ከፖሊስ ስልክ ተደውሎ ልጃቸው በኮንዶም ሥርቆት መያዟ እንደተነገራቸውም አስረድተዋል፡፡

አባቷም፣ ልጃቸው ቤተሰብ የመረጠውን ሳይሆን የማይፈልጉትን ሰው ለማጨት ትፈልግ እንደነበርና ግንኙነት ውስጥም እንደነበረች ገልጸዋል፡፡ ይህን ደግሞ ቤተሰቡ እንደ ውርደት ቆጥሮታል፡፡

የታዳጊዋ እናት ልጃቸው በተገደለች ዕለት ምሽት ላይ ከአባቷ ጋር ተጣልተው እንደነበር፣ በመጨረሻም አባት ከመኝታ ክፍሏ ገብታ የተኛችውን ለሪብ በተኛችበት አንቀው እንደገሏት ለፍርድ ቤት አምነዋል፡፡ ምንም እንኳ እሳቸው ለመጮህ፣ ባለቤታቸውን ለማስቆምም ቢሞክሩ እንዳልተሳካላቸው እናት አስረድተዋል፡፡

***********

ራሱን ፎቶግራፍ ያነሳው ጦጣ በፎቶው የባለቤትነት መብቱ እንዲረጋገጥ ተጠየቀ

በአንድ የኢንዶኔዥያ ደሴት የሚኖረውና የስድስት ዓመት ዕድሜ ያለው ጦጣ የስማርት ፎኖችን መምጣት ተከትሎ ብዙዎች እንደሚያደርጉት ራሱን ፎቶግራፍ ማንሳቱ አነጋጋሪ ሆኖ መሰንበቱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ የጦጣው ራሱን ማንሳቱ ብቻም ሳይሆን ከሳምንት በፊት የእንስሳት መብት ተሟጋቾች ጦጣው ባነሳው ፎቶግራፍ የባለቤትነት መብቱ ሊጠበቅ ይገባል የሚል ጥያቄ ማንሳታቸው ደግሞ ሌላ ጉዳይ ሆኗል፡፡ ይህ ጥያቄ ለፍርድ ቤት የቀረበው ጦጣው ያነሳው ፎቶግራፍ የዱር እንስሳት መጽሐፍ ላይ መውጣቱን ተከትሎ እንደሆነ ዘገባው ያመለክታል፡፡

ጦጣው ከአራት ዓመታት በፊት ራሱን እንዲሁም በአካባቢው የሚገኙ ሰዎችንና የተለያዩ ነገሮችን ፎቶግራፍ ያነሳው ግን በሞባይል ስልክ አልነበረም፡፡ ዳቪድ ኮሌተር የተባለ እንግሊዛዊ ፎቶግራፍ አንሺ ካሜራውን ካስቀመጠበት ዘወር ባለበት አጋጣሚ ነበር፡፡

**************

ለቤት እንስሳት የሚደረግ የውበት ቀዶ ሕክምና

ለውሻዎ ወይም ለድመትዎ የውበት ቀዶ ሕክምና (ኮስሞቲክ ሰርጀሪ) ይደረጋል ቢባሉ ምን ይሰማዎ ይሆን? ምናልባትም በአገርዎ ተራ ሕክምና እንኳን አጥተው የሚሰቃዩ ወገኖችዎ በዓይንዎ ውልብ ይሉ ይሆናል፡፡ በፕላስቲክ ሰርጀሪ ጥበብ ዝናን ላተረፈችው ደቡብ ኮሪያ ግን ጉዳዩ ሌላ ነው፡፡ ቾሰን ዴይሊ እንደዘገበው፣ በደቡብ ኮሪያ ባለጠጎች የሚወዷቸውን ድመቶችና ውሻዎች ውበት ለመጠበቅ ሲሉ የኮስሞቲክ ሰርጀሪ ማሠራቱን ተያይዘውታል፡፡

ለአንድ ውሻ የኮስሞቲክ ሰርጀሪ ለማሠራት ሥራው ከ60 ዶላር የሚጀምር ሲሆን፣ የተለያዩ ሕክምናዎች ተደርገው እስኪጠናቀቁ ደግሞ በሺሕ የሚቆጠር ዶላር ድረስ ያስወጣል፡፡

ጭራ ማሳጠር፣ ጆሮ ማሳመር፣ ስብ መቀነስ፣ በመለጠጥ ምክንያት በሰውነት ላይ የሚወጣ ሰምበርን ማጥፋት፣ የተሸበሸቡ የሰውነት ክፍሎችን መወጠር፣ የተደራረቡ ቅንድቦችን ማስወገድና ፊት የተወጠረና የጠራ እንዲሆን የሚረዳ መድኃኒት በመርፌ መልክ መስጠትንም ያካትታል፡፡

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች