Friday, July 19, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ የወጣበት ስናፕ ፕላዛ ‹‹ዲፕሎማቲክ ሬስቶራንትን›› አካቷል

ተዛማጅ ፅሁፎች

ስናፕ ንግድና ኢንዱስትሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ኢንቨስትመንት የ‹‹ዲፕሎማቲክ ሬስቶራንት›› አገልግሎት ለመጀመር እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን አስታወቀ፡፡ የሬስቶራንቱ ግንባታው በአራት ወራት ውስጥ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት የሚጀምር ሲሆን፣ የኩባንያው አጋሮችም እንደተከራዩት ታውቋል፡፡

ሬስቶራንቱ የሚገነባው ባለፈው መስከረም 13 ቀን 2008 ዓ.ም. በተመረቀው ስናፕ ፕላዛ በተሰኘው ሕንፃ አናት ላይ እንደሆነ የድርጅቱ ኃላፊ አቶ ጌድዮን ሰለሞን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ሚሊኒየም አዳራሽ አጠገብ የተገነባው ሕንፃ ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሲሆን፣ ግንባታው አራት ዓመታት ፈጅቷል፡፡ በታይላንድ፣ በደቡብ ኮሪያ፣ በማሌዥያ፣ በፔሩ እንዲሁም በአሜሪካ የባህል ዴፕሎማሲ አካል ተደርጎ የሚቆጠረውና ‹‹ኩሊናሪ ዲፕሎማሲ›› ወይም በአገርኛ ግርድፍ ፍቺው የመብል ዲፕሎማሲ የሚባለው በመንግሥታት በጎ ፈቃድና መስተንግዶ የነፃ ምግብና መጠጥ አገልግሎት ለሕዝብ የሚቀርብበት ሥርዓት ነው፡፡ ስናፕ ፕላዛ የሚያስተዋውቀው ሬስቶራንት ግን ከዚህ ዓይነቱ የዲፕሎማሲ መስተንግዶ በመለየት ለንግድ ሥራ ሲባል ስያሜ የተሰጠውና ከመደበኛው የሬስቶራንት ንግድ ለየት ለማድረግ የተሞከረበት የመስተንግዶ ንግድ ነው፡፡

አሥራ ሦስት ፎቆችና ሁለት ከምድር በታች የተገነቡ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎችን አካቷል፡፡ ከሰባ በላይ የንግድ ሱቆች ሲኖሩት የወንድና የሴት የውበት ሳሎኖች፣ የአልባሳትና ጫማ ቤቶች ቡቲኮች፣ የአገር ባህል አልባሳት፣ የሕፃናት ልብስ መሸጫ፣ የመሞሸሪያ ዕቃዎች መሸጫ፣ የስፖርት ዕቃዎች መሸጫ፣ ካፊቴሪያ ሕንፃው ከሚያካትታቸው አገልግሎቶችና የንግድ መደብሮች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ በተጨማሪም ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ቢሮዎችንም አካቷል፡፡

የገበያ ማዕከሉ ከመቶ ሃምሳ በላይ የሥራ ዕድል ፈጥሯል፡፡ ‹‹አገሪቱን ማስተዋወቅ የሚችሉ ባህላዊ ቁሳቁስና አልባሳት መሸጫ ሱቆችም አሉን፤›› ያሉት አቶ ጌድዮን፣ ማዕከሉ ግብይትን ከማዘመን ባሻገር የአገሪቱን ባህል በማስተዋወቁ ረገድ ድርሻ እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡

ስናፕ ኩባንያ የተለያዩ እንደ ቶሺባ፣ ዴል፣ ኤችፒ ያሉ ላፕቶፖችና ዴስክቶፖች ኮምፒውተሮችን ከውጭ በማስገባት ሲያከፋፍል ቆይቷል፡፡ ከ15 ዓመታት በላይም በዚህ የንግድ ዘርፍ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች