Tuesday, October 4, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -

  የፈረንሳዩ አኮር ግሩፕ ኖቮቴል ብራንድን ለማስተዳደር ተስማማ

  - ማስታወቂያ -

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  – ከፑልማን ቀጥሎ ኖቮቴል ሁለተኛው የአኮር ሆቴል ይሆናል

  የፈረንሳዩ አኮር ሆቴሎች ግሩፕ ኖቮቴል የተባለውን ብራንዱን እዚህ ለማምጣትና ለማስተዳደር ንብራስ ሆቴልስ ዴቨሎፕመንት ከተባለው ኩባንያ ጋር ተስማማ፡፡ ሆቴሉ ከሁለት ዓመት በኋላ ሥራ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

  የአፍሪካ ሆቴል ኢንቨስትመንት ፎረም እየተካሄደ በነበረበት ወቅት በተፈረመው የሁለቱ ወገኖች ስምምነት መሠረት ኖቮቴል የተባለ አኮር ብራንድ ሆቴል በፒያሳ፣ ባንኮ ዲሮማ ሕንፃ አጠገብ ባለ12 ፎቅ ግንባታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የንብራስ ኩባንያ አጋር የሆኑትና የኢትዮ ካናዲያን ቢዝነስ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዮሴፍ አሥራት ነዋይ ስምምነቱን በማስመልከት ለሪፖርተር እንዳብራሩት፣ 25 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የሚጠይቀው ሆቴል በሁለት ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈና 156 ክፍሎች የሚኖሩት ብራንድ ሆቴል ነው፡፡ አቶ ዮሴፍ እንደገለጹት የአዋጭነት ጥናቱን ጨምሮ ሙሉ የሆቴል ሥራውን ዝርዝር ጥናት ካሊብራ ሆስፒታሊቲ ኩባንያ አካሂዷል፡፡ ሁለቱን ወገኖችም አገናኝቷል፡፡

  አኮር ግሩፕ ዓምና በተካሄደው የአፍሪካ ሆቴል ኢንቨስትመንት ፎረም ሲካሄድ እንይ ጄነራል ቢዝነስ ኩባንያ ጋር ፑልማን የተባለውን ብራንድ በማምጣት ለማስተዳደር ስምምነት ማድረጉ አይዘነጋም፡፡ የፑልማን ሆቴል ግንባታን ለማከናወን የሚጠይቀውን 20 ሚሊዮን ዶላር ከፈረንሳይ አበዳሪዎች በእንይ ስም ለማምጣት አኮር መስማማቱም ይታወሳል፡፡ እንይ እየገነባው የሚገኘው ፑልማን ሆቴል 330 ክፍሎች የሚኖሩትና ከፍተኛ ደረጃ ካላቸው ተርታ የሚመደብ መሆኑም ተነግሯል፡፡

  ካሊብራ የሆቴል አማካሪ ኩባንያ ሰሞኑን በተካሄደው ፎረም ላይ ዊንድሃም የተባለውና ራማዳ በሚል ብራንድ ስም እዚህ ካመጣው ሆቴል በተጨማሪ በዊንድሃም የሚተዳደር ሆቴል ስምምነት እንዲካሄድ ለማድረግ ተቃርቦ ነበር፡፡ ሆኖም ሒደቱ ባለማለቁ ለሌላ ጊዜ መተላለፉን ለመረዳት ተችሏል፡፡ እነዚህ ጨምሮ በካሊብራ አማካይነት አራት ስምምነቶች ሊደረጉ እንደሚችሉ ይጠበቅ ነበር፡፡ በቅርቡ ይፋ ሊደረጉ እንደሚችሉ የካሊብራ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ነዋይ ብርሃኑ ጠቅሰዋል፡፡

  ካሊብራ አማካሪ በአቶ ነዋይ ብርሃኑ፣ በአቶ ዮናስ ሞገስና በአቶ ቁምነገር ተከተል በተባሉ ቀድሞ የሒልተን ሆቴል ባለደረቦች ከአምስት ዓመት በፊት የተጠነሰሰ ኩባንያ ሲሆን፣ ከጅምሩ አቶ ቁምነገር ኩባንያውን ተሰናብተዋል፡፡ ካሊብራ በሁለት ዓመት ውስጥ አሥር ያህል የውጭ ብራንዶችን ከማምጣት ባሻገር በ30 ፕሮጀክቶች ላይ በአማካሪነት እየተሳተፈ የሚገኝ የሆቴል አማካሪ ኩባንያ ነው፡፡ 

   

  - Advertisement -spot_img

  የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

  - ማስታወቂያ -