በአጭር የምሥረታ ዓመታት ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያደገው የደደቢት እግር ኳስ ክለብ ከመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ጋር አንድ ዓመት የሚዘልቅ የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ማድረጉን አስታወቀ፡፡ ክለቡ በ2008 የውድድር ዓመት የሚለብሰውን አዲስ ማሊያ አስመርቋል፡፡
የደደቢት እግር ኳስ ክለብ መስከረም 29 ቀን 2008 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሆቴል ባከናወነው የስፖንሰርሺፕ የማሊያና ምርቃት ሥነ ሥርዓት መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካና ደደቢት ለአንድ ዓመት የሚዘልቅ 4 ሚሊዮን ብር የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ይፋ አድርገዋል፡፡ የክለቡ ቡድን መሪ አቶ ኪዳነ ሐፍተጽዮን እንደገለጹት ከሆነ፣ ደደቢት በ2008 የውድድር ዓመት ለብሶት ወደ ሜዳ የሚገባው አዲሱ ማሊያ የመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ አርማ በማሊያው ላይ የሚያስቀምጥ ይሆናል፡፡