Tuesday, November 29, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፖርትእያደረ አዲስ የሆነው የፊፋ የቅሌት ወሬ

  እያደረ አዲስ የሆነው የፊፋ የቅሌት ወሬ

  ቀን:

  ላለፉት ጥቂት ወራት አነጋጋሪ ሆኖ የሰነበተው የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) የቅሌት ዜና በከፍተኛ የሙስና ቅሌት ስማቸው ተነስቶ የነበሩትን ግለሰቦች በአሜሪካው የፌዴራል የወንጀል ምርመራ መሥሪያ ቤት ጣልቃ ገብነት ለምርመራ በቁጥጥር ሥር ካዋለ በኋላም አልተቋጨም፡፡ ከሰሞኑ ደግሞ ፊፋ ራሱ በስጋት ሲንገላቱ የነበሩትን ፕሬዚዳንት ሴፕ ብላተርን ጨምሮ ዋና ጸሐፊውን ዥሮም ቫልኬን፣ የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር ፕሬዚዳንቱን ሚሼል ፕላቲኒንና ምክትል ፕሬዚዳንቱን ቻንገ ምንግ ዩን በማገድ ትርምሱ ቀጥሏል፡፡

  በተለይ ሚሼል ፕላቲኒና የክብር ምክትል ፕሬዚዳንቱ ቻንግ ምንግ ዩን፣ ስዊዘርላንዳዊውን አዛውንት በመተካት ፊፋን ለመምራት ዕድል የነበራቸው መሆኑ ጉዳዩን ይበልጥ አነጋጋሪ አድርጐታል፡፡ ፊፋ በጊዜያዊነት ያስቀመጠው እገዳ እስከ ምን ሊደርስ እንደሚችልና ለምን ያህል ጊዜ መቆየት እንዳለበት በግልጽ የተቀመጠ ነገር ባይኖርም፣ እስከ 45 ቀናት ሊቆይ እንደሚችል ያስቀመጠው የጊዜ ገደብ ግን ግለሰቦቹን በሕግ ‹‹የመጠየቅ›› ወይም ‹‹አለመጠየቅ›› ዕጣ ፈንታን የሚወስን ሊሆን እንደሚችል ዘገባዎች ይጠቁማሉ፡፡
  ይህ በፊፋ የሥነ ምግባር ኮሚቴ ተግባራዊ የሆነው እገዳ፣ ሴፕ ብላተርም ሆነ ሌሎች ተሰሚነት ያላቸውን ግለሰቦች በግዳጅ ተጠያቂ ሊያደርጋቸው የሚያስችል መረጃን የማሰባሰብ ሒደቱ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፣ በአንፃሩ ሴፕ ብላተርን ጨምሮ የታገዱት ግለሰቦች የፊፋን የሥነ ምግባር ኮሚቴን መረጃ በማጣጣል የመከላከያ መረጃዎችን እንዲያቀርቡ ዕድል ሊሰጣቸው እንደሚገባ በተለይ ሴፕ ብላተር በየትኛውም መንገድ ተጠያቂ የሚሆኑበትን ወንጀል እንዳልፈጸሙ አስረድተዋል፡፡

  የፊፋ ተከታታይ የቅሌት ወሬ ከጫፍ ጫፍ የተዳረሰ መሆኑና የዓለምን ማኅበረሰብ በስፋት እያነጋገረ በመሆኑ፣ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽንንም (ካፍ) በኃላፊነት እየለበለበ ስለመሆኑ ይነገራል፡፡ ለጊዜው ግን የካፍ ፕሬዚዳንት ካሜሩናዊው ኢሳ ሐያቱ ፊፋን እንዲመሩ ተደርጓል፡፡ በአፍሪካ እግር ኳስ ውስጥ ታሪካዊ ሥፍራ ያለው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም የዚሁ የፊፋ የቅሌት ወሬ በሩቁም ቢሆን ሳይነካካው እንደማይቀርም መነገር ጀምሯል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት ፊፋ የ2018 እና የ2022 የዓለም ዋንጫ የአስተናጋጅነቱን ኃላፊነት ለሩሲያና ለኳታር ሲሰጥ፣ የኳታር እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት በተለይ በፊፋ ከፍተኛ ድምፅ ያላቸውን የአፍሪካንና የኤሽያን አባል አገር ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንቶችን ኳታር ድረስ ለስብሰባ ጠርተው፣ ፊፋ በእግር ኳስ ወደ ኋላ ለቀሩ አገሮች ለጐል ፕሮጀክት (የእግር ኳስ ልማት) ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓመት ሲሰጥ የቆየውን 250,000 ዶላር ወደ 500,000 ዶላር እንደሚያሳድግላቸው ቃል መግባታቸውን ተከትሎ፣ ሲፕ ብላተር የኳታሩንና የኤሽያውን እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ፕሬዚዳንቶች ማገዳቸው ይታወሳል፡፡    

          

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በችግር የተተበተበው የሲሚንቶ አቅርቦት

  ሲሚንቶን እንደ ግብዓት ተጠቅሞ ቤት ማደስ፣ መገንባት፣ የመቃብር ሐውልት...

  ‹‹የናይል ዓባይ መንፈስ›› በሜልቦርን

  አውስትራሊያ ስሟ ሲነሳ ቀድሞ የሚመጣው በተለይ በቀደመው ዘመን የባህር...

  ‹‹ልብሴን ለእህቴ››

  ለሰው ልጅ መኖር መሠረታዊ ፍላጎት ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ ልብስ...

  የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የምርመራ ውጤት እስከምን?

  በፍቅር አበበ የትምህርት ጥራትን፣ ውጤታማነትንና ሥነ ምግባርን ማረጋገጥ ዓላማ አድርጎ...