Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊኪነ ጠቢቡን ፍቃዱ ተክለማርያም ለመታደግ

ኪነ ጠቢቡን ፍቃዱ ተክለማርያም ለመታደግ

ቀን:

ቴዎድሮስ፣ ኤዲፐስ ንጉሥ፣ ሐምሌት፣ ንጉሥ አርማህ፣ በተሰኙ አራት ተውኔቶች መሪ ተዋናይ በመሆን በንጉሥነት ተውኗል፡፡ በሌሎች ተውኔቶች መቃብር ቆፋሪውና የሬሳ ሳጥን ሻጩ፣ እሳት ሲነድ፣ ቤቴ፣ የሠርጉ ዋዜማ፣ ደማችን፣ የሊስትሮ ኦፔራ፣ አቡጊዳ ቀይሶ፣ ባለካባ ባለዳባ፣ መልዕክት ወዛደር፣ ታርቲዩፍ ከተወነባቸው ይገኙበታል፡፡

ኪነ ጠቢቡ ፍቃዱ ተክለማርያም በቴሌቪዥን ከተወናቸው ተውኔቶች መካከልም ያልተከፈለ ዕዳ፣ የአበቅየለሽ ኑዛዜ፣ ባለጉዳይና በሕዝብ ዘንድ አድናቆትን ያተረፉለት ናቸው፡፡ ከዚህም ባሻገር ‹‹ከመጻሕፍት ዓለም›› ይባል በነበረው የኢትዮጵያ ሬዲዮ ፕሮግራም ‹‹ሞገደኛው ነውጤ፣ ጥቁር ደም፣ ሳቤላ፣ የነበረው እንዳልነበር›› የተባሉትን አጭርና ረዥም ልቦለዶችን ተውኔታዊ መልክ በመስጠት ቀልብን በሚይዝ የአተራረክ ስልት በመተረክ እንደሚታወቅ የፋንታሁን እንግዳ መዝገበ ሰብ ድርሳን ይገልጸዋል፡፡ ከአራት አሠርታት በላይ በኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ሕዋ ውስጥ ገዝፎ የሚታየው ፍቃዱ ተክለማርያም በፊልም ተዋናይነትም ከግዙፋኑ ከያንያን ተርታ ይሰለፋል፡፡

መሰንበቻውን በየሚዲያው እንደገለጸው፣ ኪነ ጠቢቡ ፍቃዱ ተክለማርያም ኩላሊቶቹ ከጥቅም ውጪ መሆናቸውንና ንቅለ ተከላ ያስፈልገዋል፡፡ በፍቃዱ ተክለማርያም ወዳጆችና የሥራ ባልደረቦች የተቋቋመው ኮሚቴ ሰሞኑን በሰጠው መግለጫ የኪነ ጠቢቡን ጤንነት ለመመለስ ኩላሊት ለመለገስ የቤተሰቡ አባላት በምስጢር ሞክረው በሕክምና ጉዳዮች ምክንያት ሳይሳካ መቅረቱን ገልጿል፡፡ ኮሚቴው እንዳስታወቀው ሕክምናው በውጭ አገር ለማከናወን እንዲቻል ገንዘብ ለማሰባሰብ የባንክ አካውንት ተከፍቷል፡፡

ኪነ ጠቢብ ፍቃዱን በገንዘብ ለመደገፍ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባንክ ቁጥር 1000239345488 ገንዘብ ገቢ ማድረግ ይቻላል፡፡ እንዲሁም በውጭ አገር ላሉ ‹‹gofundme›› በሚል የኦንላይን የገቢ ማሰባሰቢያ በቴዎድሮስ ተሾመ ስም የተከፈተ ሲሆን፣ “Please help save Fekadu” በማለት ድጋፍ ማድረግ ይቻላል፡፡

የኩላሊት ልገሳ ለማድረግ ለሚፈልጉም አቶ ግርማ ተክለማርያምን በ0911864396፣ ዮርዳኖስ ፍቃዱን በ0913023444 ማግኘት እንደሚቻል ተነግሯል፡፡ እንደመግለጫው የፍቃዱ የደም ዓይነት A ሲሆን፣ የኩላሊት ልገሳ ለማድረግ የሚችሉ A ወይም O የደም ዓይነት ያላቸው መሆናቸውም ተገልጿል፡፡

ኪነ ጠቢቡ ፍቃዱ፣ የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ከነበረበት ጊዜ አንስቶ ተስፋዬ አበበ መሥርተውት በነበረው የቴአትር ዕድገት ክበብ ውስጥ በነበረው የትወና እንቅስቃሴው እየታወቀ በመምጣቱ በ1967 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ በመቀጠር የተውኔት ጉዞውን መጀመሩ ገጸ ታሪኩ ያመለክታል፡፡

እንደ ታሪካዊ መዝገበ ሰብ አገላለጽ፣ ፍቃዱን አስደናቂ ተዋናይ ካስባሉት አጋጣሚዎች መካከል የአራት የተለያዩ ነገሥታትን ሚናዎች እየወሰደ የተጫወተው በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል፡፡ በቴዎድሮስ፣ በሐምሌት፣ በንጉሥ አርማህና በኤዲፐስ ንጉሥ ተውኔቶች የተለያየ ሰብዕና ያላቸውን ነገሥታት ሚናዎች ወስዶ በመጫወቱ ይታወቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...