Tuesday, October 3, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናለብይን ተቀጥረው የነበሩት ጦማሪያን ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ

ለብይን ተቀጥረው የነበሩት ጦማሪያን ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ

ቀን:

በተጠረጠሩበት የሽብርተኝነት ድርጊት ወንጀል ለብይን ለመስከረም 27  ቀን 2008 ዓ.ም. ተቀጥረው የነበሩት ጦማሪያን ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፉ ብርሃኔ፣ አቤል ዋበላና በፈቃዱ ኃይሉ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ፡፡

ጦማሪያኑ ፍርድ ቤት ያልቀረቡበት ምክንያት ደግሞ በዕለቱ በሌላ ሥራ ምክንያት ይሁን ወይም በሌላ ጉዳይ ባይታወቅም፣ ለብይን የቀጠሯቸው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ዳኞች እንደሌሉ ተነግሯቸው መሆኑ ታውቋል፡፡

ብይኑ በዕለቱ እንደሚሰጥ የገመቱ የጦማሪያኑ ቤተሰቦች፣ ጓደኞቻቸውና ጋዜጠኞች በፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ የተገኙ ቢሆንም፣ የፍርድ ቤቱ ሠራተኞች ‹‹ዳኞች ስለሌሉ እንዳይመጡ መስከረም 26 ቀን 2008 ዓ.ም. ለማረሚያ ቤቱ ተደውሎ ተነግሮታል›› በማለታቸው ለመከታተል የሄዱ ታዳሚዎች ተመልሰዋል፡፡

የጦማሪያኑ ጠበቆች ግን በሁኔታው ማዘናቸውን ተናግረዋል፡፡ ቢያንስ ቢያንስ ፍርድ ቤቱ በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ማስታወቂያ መለጠፍና ጉዳዩን የሚከታተሉ እንዲረዱ ማድረግ ሲገባው፣ ምንም ሳይል መሄዱ አግባብ አለመሆኑንና ታይቶም እንደማይታወቅ ገልጸዋል፡፡

ጦማሪያኑ እንዲከላከሉ ወይም መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ የሚሰናበቱበት ብይን ጥቅምት 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች በሙሉ ከመስከረም 26 ቀን እስከ 30 ቀን 2008 ዓ.ም. አዳማ ሥልጠና ላይ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...