Saturday, December 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናፓርላማው የአሠራርና የሥነ ሥርዓት ደንቡን አሻሻለ

ፓርላማው የአሠራርና የሥነ ሥርዓት ደንቡን አሻሻለ

ቀን:

– ተደጋጋሚ ችግር የታየባቸው አመራሮች እንዲነሱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያሳስባል

– የመከላከያና የደኅንነት ተቋማትን የሚከታተል ኮሚቴ እንዲመሠረት ወሰነ

ሙሉ በሙሉ በኢሕአዴግና አጋሮቹ የተሞላው አምስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መስከረም 24 ቀን 2008 የሥራ ዘመኑን በጀመረ በማግሥቱ፣ የፓርላማውን የአሠራርና የአባላት የሥነ ምግባር ደንብ አሻሻለ፡፡

በግንቦት ወር 2007 ዓ.ም. በተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ኢሕአዴግና አጋሮቹ የፓርላማውን ሙሉ ወንበር ማሸነፋቸው ይታወቃል፡፡ በዚህ የተነሳም በርካታ የፖለቲካ ተንታኞች የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ዋነኛ መድረክ የሆነው ፓርላማ በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር ውስጥ መውደቁ፣ ለፖለቲካ ሥርዓቱ አደጋ ነው በማለት እየተቹት ይገኛሉ፡፡

መስከረም 24 ቀን ሥራ የጀመረው አምስተኛው ፓርላማ የእዚህን ትችት መሠረት የተገነዘበ የሚመስል ማሻሻያ በአሠራርና በአባላት ሥነ ሥርዓት ደንቡ ላይ እንዲካተት አድርጓል፡፡ ሕዝቡና የተለያዩ ሕዝባዊ አደረጃጀቶች፣ እንዲሁም የብዙኃንና የሙያ ማኅበራትን ተሳትፎ ቀጣይነት ባለው መንገድ ለማረጋገጥ በምክር ቤቱ ሥራም ላይ እንዲሳተፍ የሚፈቅድ ማሻሻያ አድርጓል፡፡

በደንቡ ማሻሻያ አንቀጽ 103 ላይ ምክር ቤቱ በሚያከናውናቸው ተግባራት የዜጎችንና የተለያዩ አካላትን ተሳትፎ ለማረጋገጥ የሕዝብ አስተያየት መድረኮች እንደሚዘጋጁ፣ በነፃ የስልክ ጥሪና ለባለድርሻ አካላት በሚደረግ ጥሪ መሠረት በምክር ቤቱና በቋሚ ኮሚቴዎች ስብሰባዎች ሒደት እንዲሳተፍ እንደሚያደርግ ይደነግጋል፡፡

ዜጎችና የተለያዩ አካላት ተሳትፎ እንዲያደርጉባቸው ከተለዩ ጉዳዮች መካከል የሕግ አወጣጥ ሒደት፣ የወጡ ሕጎች አፈጻጸምና የሥራ አፈጻጸም ውጤትን በተመለከተ፣ በኦዲት ግኝት፣ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ፣ እንዲሁም ሌሎች የመንግሥትና የሕዝብን ጥቅም የሚመለከቱ ጉዳዮች ይሆናሉ፡፡

ተሳትፎ የሚያደርጉ አካላት እንደ ጉዳዩ አግባብነት የሚወሰኑ ናቸው፡፡ ምክር ቤቱ በሚያከናውናቸው ተግባራት የክልል መንግሥታትና የከተማ አስተዳደሮች፣ የትምህርት ተቋማት፣ የብዙኃን ማኅበራት፣ የሙያ ማኅበራት፣ የንግዱ ኅብረተሰብ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በማለት ይዘረዝራቸዋል፡፡

ለምክር ቤቱ በቀጥታ ተጠሪ የሆኑ የዴሞክራሲ ተቋማት ማለትም የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ ለምክር ቤቱ በቀጥታ ተጠሪ ባይሆንም የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በመንግሥት ተቋማት ላይ በተለየ ሁኔታ ለምክር ቤቱ ክትትልና ቁጥጥር ሪፖርት የሚያቀርቡ በመሆኑ በአግባቡ እንደሚጠቀምባቸው ይገልጻል፡፡

እነዚህ ተቋማት ለምክር ቤቱ ሪፖርት በሚያቀርቡበት ወቅት የሌሎች የመንግሥት ተቋም ኃላፊዎች በምክር ቤቱ እንዲገኙና እንደ አስፈላጊነቱም ምላሽ እንዲሰጡ የሚያደርግ አዲስ አሠራር አስቀምጧል፡፡ ይኼም ችግር ያለባቸው ኃላፊዎችን የማሳፈር የመጀመርያው ተግሳፅ ይሆናል፡፡

በዚህ ወቅትም የፌዴራል ፖሊስ የሥራ ኃላፊዎች የምክር ቤቱን ውይይት እንዲከታተሉ እንደሚደረግ፣ የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትሩ አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ ገልጸዋል፡፡

በደኅንነትና በመከላከያ ተቋማት የተሻለ ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግም ራሱን የቻለ የመከላከያና የደኅንነት ጉዳዮች ልዩ ቋሚ ኮሚቴ እንዲመሠረት የሚያሻሽል ድንጋጌ አስገብቷል፡፡

ይኼ ልዩ ኮሚቴ የመከላከያና ደኅንነት  ተቋማት በጀት አፈጻጸም፣ የተቋማቱ ግዥና ፋይናንስ አስተዳደር፣ የኦዲት ግኝት፣ የተቋማቱ አባላት የሥራ ሁኔታና አስተዳደር ይገኙበታል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አፈ ጉባዔው እንደሚሆኑ፣ ሌሎቹ አባላት በአፈ ጉባዔው እንደሚመረጡ፣ እንዲሁም ከሞላ ጎደል የዚሁ ቋሚ ኮሚቴ ስብሰባ በዝርዝር እንደሚካሄድ ይደነግጋል፡፡

ምክር ቤቱ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ላይ ዕምነት አጥቻለሁ የሚል ውይይት ማድረግ እንደሚችል፤ በከፍተኛ ድምፅም ያቋቋመውን መንግሥት ማፈራረስና ሌላ ማቋቋም እንደሚችል በሕገ መንግሥቱም ቀድሞ በነበረው የአሠራር ሥነ ሥርዓት ደንብ ላይ ተቀምጧል፡፡

ይኼንን ሕግ በማብራራት ማንኛውም አካል በሚኒስትሮች ምክር ቤት ላይ ዕምነት አጥቻለሁ የሚል ሞሽን እንደሚያቀርብ አስቀምጧል፡፡

የአፈ ጉባዔው አማካሪ ኮሚቴ የማቀርብለት ሞሽን ሥርዓቱን ተከትሎ የቀረበ ሆኖ ካገኘው፣ ለምክር ቤቱ እንዲቀርብ እንደሚፈቅድ የምክር ቤቱ አባላት ሞሽኑን በአንድ ሦስተኛ ድምፅ የሚደግፉት ከሆነ በ15 ቀናት  ውስጥ ውይይት እንደሚደረግ ይደነግጋል፡፡ በቂ ውይይት ከተደረገ በኋላ ወደ ድምፅ መስጠት እንደሚካድና አብላጫ ድምፅ ያገኘው ውሳኔ ተፈጻሚ እንደሚሆን ይደነግጋል፡፡

ፓርላማው ችግር በሚታይባቸው አስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች ችግሩ ከተቋሙ የመነጨ ከሆነ ችግሩን እንዲያርም መመርያ እንደሚሰጠውና መታረሙንም ያረጋግጣል፡፡ ችግሩ ካልታረመና መሠረታዊ ከሆነ ለችግሩ ተጠያቂ በሆነው አካል ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዕርምጃ እንዲወስድ ያደርጋል፡፡ ዕርምጃውም ከኃላፊነት ማንሳት ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...