Friday, February 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊያልፀደቀው ማስተር ፕላን የንግድ ሕንፃዎች 60 በመቶ ለመኖሪያ ቤት እንዲሆኑ ደነገገ

ያልፀደቀው ማስተር ፕላን የንግድ ሕንፃዎች 60 በመቶ ለመኖሪያ ቤት እንዲሆኑ ደነገገ

ቀን:

– ሥራ ላይ በመዋሉ ባለሀብቶች ተቃውሞ እያሰሙ ነው

ያልፀደቀው የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የጋራ ማስተር ፕላን በመሀል አዲስ አበባ ለቅይጥ አገልግሎት በሚውሉ መሬቶች ላይ ሕንፃ የሚገነቡ፣ 60 በመቶ የሚሆነው የሕንፃው ክፍል ለአፓርታማ እንዲውል ይደነግጋል፡፡

ማስተር ፕላኑ ከመፅደቁ በፊት በተለይ በአዲስ አበባ ጥቅም ላይ እየዋለ ሲሆን፣ ለቅይጥ አገልግሎት የሚሆኑ የንግድ ሕንፃዎች ለመገንባት ፈቃድ የጠየቁ ባለሀብቶች 60 በመቶው ለመኖሪያ ቤት እንዲውል ካላደረጉ፣ ፈቃድ እንደማይሰጣቸው ተገልጾላቸዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ባለሀብቶች ግን ፍላጐታቸው ባልሆነ የሥራ መስክ እንዲሰማሩ አስገዳጅ አሠራር መውጣቱ ሕገወጥ ነው በማለት፣ አሠራሩ እንዲስተካከል በመጠየቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን የግንባታ ፈቃድ የሥራ ሒደት መሪ አቶ ይትባረክ ገብረ መድኅን፣ ማስተር ፕላኑ በተለያዩ አካባቢዎች የተለያዩ ግንባታዎች እንዲካሄዱ የሚያስገድድ መሆኑን ገልጸው፣ በተለይ በብዛት ለመኖሪያ በሚውሉ አካባቢዎች ለቅይጥ አገልግሎት የሚውል ሕንፃ የሚገነባ አካል ቢያንስ 60 በመቶ ለመኖሪያ ቤት አገልግሎት እንዲያውል ያዛል ብለዋል፡፡ ‹‹ማስተር ፕላኑ ባይፀድቅም ተግባራዊ እየተደረገ በመሆኑ እኛም ሥራ ላይ አውለነዋል፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡ በዚህ መሠረትም ለአዲስ አበባ ከተማ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን የግንባታ ፈቃድ እንዲሰጣቸው የሚያመለክቱ ባለሀብቶች፣ ይህንን አሠራር ካልተቀበሉ የግንባታ ፈቃድ አይሰጣቸውም በማለት አስረድተዋል፡፡

አቶ ይትባረክ ግንባታ ለማካሄድ ፈልገው ይህ ጉዳይ ሲገለጽላቸው ቅሬታ የሚያቀርቡ ባለሀብቶች መኖራቸውን ገልጸው፣ መሥሪያ ቤታቸው ይህንኑ ቅሬታ ለአዲስ አበባና ለኦሮሚያ ልዩ ዞን የጋራ ማስተር ፕላን ጽሕፈት ቤት እያቀረበ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ነገር ግን ከማስተር ፕላን ጽሕፈት ቤት፣ የከተማውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ ሲባል የተወሰነ ነው የሚል ምላሽ እየተሰጠ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ልዩ ዞን በጋራ እየተሠራ ያለው ማስተር ፕላን በአሁኑ ወቅት እየተገባደደ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ በተያዘው በጀት ዓመት እንደሚፀድቅ በቅርቡ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ምንም እንኳ ማስተር ፕላኑ በአሁኑ ወቅት ባይፀድቅም፣ የከተማው የወደፊት ዕድገት ከማስተር ፕላኑ ጋር ተጣጥሞ መሄድ ስላለበት እየተተገበረ መሆኑን ከንቲባው ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ማስተር ፕላኑ በተለይ የአዲስ አበባ የመሬት አጠቃቀም ላይ ዝርዝር ጉዳዮች ውስጥ በጥልቀት በመግባት የተነተነ ሲሆን፣ በመካከለኛው የከተማው ክፍል በተለይም ለመኖሪያ የተመደቡ ቦታዎች ላይ ሆቴል ወይም እንግዳ ማረፊያ የሚገነቡ ባለሀብቶች ላይ ‹‹60 በመቶ መኖሪያ ቤት መገንባት›› የሚለው አሠራር ተግባራዊ እንዳይሆን ሲያደርግ፣ ለቅይጥ አገልግሎት በሚገነቡ የንግድ ማዕከል ሕንፃዎች ላይ ግን 60 በመቶ የመኖሪያ ቤት መገንባትን አስገዳጅ አድርጓል፡፡

ቅሬታ ያላቸው ባለሀብቶች የከተማው አስተዳደር ለሪል ስቴት ልማት ሰፋፊ ቦታዎችን በአነስተኛ ሊዝ ዋጋ በማቅረብ እንጂ፣ በእንደዚህ ዓይነት አሠራር የከተማው የመኖሪያ ቤት ችግርን መፍታት አያስችለውም፡፡ የግለሰብ መብት ላይ ጣልቃ መግባት ነው በማለት መከራከሪያቸውን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ የካቤኔ አባል የሆኑት አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያዳመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል...

የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት የፈጠሩት አምቧጓሮ

ባለፈው ቅዳሜና እሑድ በአዲስ አበባ የተካሄደው የአፍሪካ ኅብረት 37ኛው...

የብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ትግበራ የፈጠራቸው አሉታዊና አዎንታዊ ጎኖች

የአገሪቱ ንግድ ባንኮች በዓመት የሚሰጡት የብድር መጠን ላይ የኢትዮጵያ...

ቱግ ቱግ!

የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ለመታደም የመጡ እንግዶችን ሸኝተን ከፒያሳ ወደ...