Tuesday, February 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየተራዘመው የኢትዮጵያ የግብፅና የሱዳን ውይይት ከሳምንት በኋላ ሊካሄድ ነው

የተራዘመው የኢትዮጵያ የግብፅና የሱዳን ውይይት ከሳምንት በኋላ ሊካሄድ ነው

ቀን:

በኢትዮጵያ ጥያቄ የተራዘመው የኢትዮጵያ ግብፅና ሱዳን የጋራ የቴክኒክ ኮሚቴ ስብሰባ በቀጣዮቹ አሥር ቀናት ውስጥ በካይሮ እንደሚካሄድ ተጠቆመ፡፡

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የኢትዮጵያ የሥራ ኃላፊዎች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ውይይቱ ሊካሄድ ታስቦ የነበረው ባለፈው ሳምንት ውስጥ ነበር፡፡ ነገር ግን በዚያው ሳምንት በኢትዮጵያ የመንግሥት ምሥረታ ይካሄድ ስለነበር እስከ አውሮፓውያኑ የጥቅምት ወር መጨረሻ ድረስ እንዲራዘም መጠየቁን ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በኩል ውይይቱን ለማካሄድ የሚቻልበት ዝግጅት መጠናቀቁን፣ የቀጣዩ ውይይት አስተናጋጅ የሆነችው ግብፅ የውይይቱን ቀን ቆርጣ የምታሳውቅበት ቀን ብቻ እየተጠበቀ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የታላቁ ህዳሴ ግድብ በግብፅና በሱዳን ላይ የሚያመጣውን ተፅዕኖ ለመገምገም ሦስቱ አገሮች ያዋቀሩት የጋራ ኮሚቴ፣ ሁለት ዓለም አቀፍ ኩባንያዎችን ከፈረንሣይና ከኔዘርላንድ መምረጡ ይታወሳል፡፡

የጋራ ኮሚቴው በደረሰበት ስምምነት መሠረት የፈረንሣዩ ቢአርኤል ኢንጂነርስ የሚፈለጉትን ሁለት ጥናቶች በመሪነት 70 በመቶ በመሸፈን እንዲያካሂድ ተወስኗል፡፡

ቢርኤል ኢንጂነርስ የኮንትራት ውሉን የሚፈራረምና አጠቃላይ ሕጋዊ ኃላፊነቱ የሚወድቅበት ድርጅት እንዲሆንና ሰላሳ በመቶ የሚሆነውን ቀሪ ሥራ ለኔዘርላንዱ ኩባንያ ዴልታ ሬዝ እንዲሰጥ ተወስኖ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ዴልታ ሬዝ በመስከረም ወር አጋማሽ ላይ ራሱን ከጥናት ሥራው ማግለሉን አሳውቋል፡፡ በዚህ የተነሳ ነበር የሦስቱ አገሮች የጋራ ኮሚቴ ውይይት የተቋረጠው፡፡ ውይይቱ እ.ኤ.አ. ኦክቶበር 5 ቀን 2015 እንዲካሄድ ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ቢሆንም፣ በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ የመንግሥት ምሥረታ የሚካሄድ በመሆኑ እንዲራዘም ተደርጓል፡፡

በዚህ መንግሥት ምሥረታ መሠረት በኢትዮጵያ በኩል ድርድሩን በበላይነት ሲከታተሉ የነበሩት የቀድሞው የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አቶ ዓለማየሁ ተገኑ በአቶ ሞቱማ መቃሳ እንዲተኩ መደረጉ ይታወሳል፡፡ በዚህም መሠረት አቶ ሞቱማ በዓባይ ወንዝ ፖለቲካ ጉዳይ የሚሳተፉ አራተኛው ሚኒስትር ሆነዋል፡፡

የዓባይ ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ እስኪፈርም ድረስ የነበረው የዓባይ ተፋሰስ ተጋሪ የሆኑ ዘጠኝ አገሮች ድርድር የቀድሞዎቹ ሚኒስትሮች አቶ ሽፈራው ጃርሶና አቶ አስፋው ዲንጋሞ በበላይነት መከታተላቸው ይታወቃል፡፡ የህዳሴው ግድብ ይፋ ከሆነ ጀምሮ ያለውን ድርድር ደግሞ አቶ ዓለማየሁ ተገኑ ሲከታተሉ ቆይተዋል፡፡

በአቶ ዓለማየሁ የሥልጣን ዘመን ውስጥ የተጀመረውና ያልተጠናቀቀውን ውይይት በአሁኑ ወቅት አቶ ሞቱማ የተረከቡ ሲሆን፣ በዚህ ወር መጨረሻ አካባቢ በሚካሄው የሦስቱ አገሮች ውይይት ላይም ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በዚህ ውይይት ላይ ቤአርኤልና ዴልታ ሬዝ የተባሉት ኩባንያዎች በጋራ ጥናቶቹን እንዲያከናውኑ፣ አልያም ቢአርኤል ብቻ ጥናቱን እንዲያከናውን የሚያስችል ውሳኔ ይወስናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡    

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የካቲት አብዮት – ጥያቄዎችሽ ዛሬም እየወዘወዙን ነው!

በበቀለ ሹሜ አጭር መግቢያ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ከ1960ዎች ወጣቶች ርዝራዦች አንዱ...

የሰሞኑ የ“መኖሪያ ቤቶች” የጨረታ ሽያጭ ምን ዓይነት ሕጋዊ መሠረት አለው?   

በዳዊት ዮሐንስ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ አየር ላይ ከሚንሸረሸሩ ዜናዎች...

ሁለቱ ወጎች፡ ከሰማየ ሰማያት አድርሶ መላሹ ቋንቋ! እስከ በዓሉ ቤርሙዳ

በተክለ ጻድቅ በላቸው ሰማየ ሰማያት አድርሶ መላሹ ቋንቋ! ከሁለት ሦስት ዓመት...

ለትግራይ ክልል ድርቅ ተፈናቃዮች አፋጣኝና ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንዲደረግ ተጠየቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዩች ቋሚ...