Tuesday, December 6, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ኪንና ባህልየቶሚ ቲ የበጎ አድራጎት ዕርምጃ

  የቶሚ ቲ የበጎ አድራጎት ዕርምጃ

  ቀን:

  ‹‹ከቀድሞ ጀምሮ አገሬ መጥቼ በጎ ነገሮች የማሳካት ዕቅድ ነበረኝ፤ ዩኒሴፍ ለውጥ ያመጣ ትልቅ ድርጅት ስለሆነ ከነሱ ጋር የመሥራት ዕድሉ ሲመጣ በደስታ ነው የተቀበልኩት፤›› ያለው ባለፈው ሳምንት ዩኒሴፍ አምባሳደር አድረጎ የመረጠው ሙዚቀኛ ቶማስ ጎበና (ቶሚ ቲ) ነው፡፡ የመጀመርያ ሥራው የሴቶች ጥቃትን ለማስቆም የሚካሄድ ፐብሊክ ሰርቪስ አናውንስመንት (ፒኤስኤ) እንደሚሆንም ለሪፖርተር ገልጿል፡፡

    ተወልዶ ያደገው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ ውስጥ የጐጐል ቦዴሎ ባንድ ቤዚስት ነው፡፡ ሙዚቀኛው ላለፉት ሁለት ዓመታት በበጎ ፈቃደኝነት በዩኒሴፍ ወጣቶችን የማጎልበት እንቅስቃሴዎች ላይ የተሳተፈ ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት ድርጅቱ በይፋ አምባሳደር አድርጎታል፡፡ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታትም በሴቶችና ሕፃናት ጉዳዮች ላይ ባተኮሩ ክንውኖች የሚሳተፍ ይሆናል፡፡

  ቶሚ ቲ ለሪፖርተር እንደገለጸው፣ ስለ ሴቶችና ሕፃናት ጥበቃ ግንዛቤ መፍጠርና በተለያዩ ቦታዎች ወጣቶችን ማነሳሳት ተቀዳሚ ኃላፊነቶቹ ናቸው፡፡ ዩኒሴፍ ዓላማዎቹ ግብ እንዲመቱ በሕዝብ ዘንድ የሚታወቁና ተፅዕኖ መፍጠር የሚችሉ ሙዚቀኞችን ለአምባሳደርነት ያጫል፡፡ ቶሚ ቲም ይህንን ዕድል ተጠቅሞ በበርካታ ሰብዓዊ ሥራዎች እንደሚሳተፍ ተናግሯል፡፡

  ሙዚቀኛው አምባሳደር የሆነው በአገር አቀፍ ደረጃ በመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ መሥራት ለሚፈልጋቸው የማነሳሳት ሥራዎች መልካም አጋጣሚ እንደሆነም ተናግሯል፡፡

  ከዚህ ቀደም ከድርጅቱ ጋር በጥምረት ከሠራቸው መካከል ከመርካቶ ጀምሮ ቢሾፍቱና ናዝሬት የሚገኙ በዩኒሴፍ የተቋቋሙ የወጣቶች ማዕከሎችን መጎብኘትና ተሞክሮውን ማካፈል ይጠቀሳል፡፡ በዲላ ዩኒቨርሲቲ በኤችአይቪ ኤድስ ላይ ያተኮረ እንዲሁም በአፋር ክልል ግርዛት ላይ ያተኮሩ እንቅስቃሴዎች ሲደረጉም ተሳትፏል፡፡ በአፋር ክልል፣ ዶቢ ቀበሌ በዩኒሴፍ ድጋፍ የተዘረጋ የንፁህ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክትም ተያይዞ ይነሳል፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች ያስተዋላቸው ጅማሮዎች እንዳስገረሙትም ሙዚቀኛው ተናግሯል፡፡

  በናዝሬት ከተማ በአንድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ከውኃ መያዣ ፕላስቲክና ከወዳደቁ ቁሳቁሶች ሮኬት ለመሥራት የሞከሩ ወጣቶች መመልከቱን እንደ ምሳሌ ጠቅሷል፡፡ ‹‹የተሟላ ግብዓት ቢያገኙ ትልቅ ደረጃ ሊደርሱ እንደሚችሉ አመላክቶኛል፤›› ብሎ፣በሙያው የበለጠ አስተዋጽኦ ለማድረግ እንዳነሳሳውም አክሏል፡፡

  ‹‹ሰው ባለው ነገር ደከም ያለውን ሰው ማበረታታት ይችላል፤›› የሚለው ቶሚ ቲ፣ ሁሉም ሰው ቢተባበር ለውጥ ማምጣት እንደሚችል ያምናል፡፡ በሙዚቀኛነቱ ያለውን ዕውቅና ለበጎ ተግባር በማዋል፣ ወጣቶችን በማነሳሳት ተጨባጭ ለውጥ እንደሚያስመዘግብም  ተስፋ ያደርጋል፡፡ ‹‹ብዙዎች ዕውቀቱና ችሎታው አላቸው ከኛ የሚፈልጉት ማበረታቻና ተስፋ መስጠትን ነው፤›› ይላል፡፡ በተጨማሪም ኢትዮጵያ ውስጥ የኢንተርቴመንት ድርጅት የማቋቋም ዕቅድ አለው፡፡ በአገሪቱ የሚሠሩ ሙዚቃዎች ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ለማስቻልና ችሎታ ያላቸው ወጣት ሙዚቀኞችን በዘርፉ ለማበልፀግ የሚያግዝ ድርጅት እንደሚሆን ተናግሯል፡፡

  ዩኒሴፍ ከዚህ ቀደም አምባሳደር ካደረጋቸው ሙዚቀኞች መካከል አስቴር አወቀ፣ አቤሎን መለሰና ሃና ጎደፋ ይጠቀሳሉ፡፡ ቶሚ ቲ ከተሳተፈባቸው የዩኒሴፍ ዓለም አቀፍ ፕሮጀክቶች መካከል ኢማጅን ፕሮጀክት አንዱ ነው፡፡ በዓለም ላይ ያሉ ሕፃናት ለሚገጥሟቸው ፈተናዎች ትኩረት እንዲሰጥ ለማድረግ ያለመ ፕሮጀክት ሲሆን፣ የጆን ሌነንን ‹‹ኢማጅን›› የተሰኘ ሙዚቃ የተለያዩ ግለሰቦች በየራሳቸው መንገድ እንዲያዜሙት በማድረግ የተከናወነ ነበር፡፡ ሙዚቀኛው ከሌሎች የዩኒሴፍ አምባሳደሮች ጋር ማለትም ኬቲ ፔሪና አንጃሊክ ኪጆን ጋር ሠርቷል፡፡

    

   

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ዳግም ነፍስ የዘራው የተማሪዎች ማርች ባንድ

  የሙያው ፍቅር ያደረባቸው ገና በልጅነታቸው ነው፡፡ በ1970ዎቹ መጀመርያ፣ ለቀለም...

  በስንደዶና ሰበዝ የተቃኘው ጥበብ

  በአንዋር አባቢ ተወልዳ ያደገችው መሀል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ነው፡፡...

  አዲስ ጥረት የሚጠይቀው  ኤችአይቪ  ኤድስን  የመግታት  ንቅናቄ

  ‹‹ኤችአይቪ በመላው ዓለም  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ዋነኛ የሕዝብ...

  የኅትመት ብርሃን ያየው ‹‹የቃቄ ወርድዎት›› ቴአትር

  ከአራት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ይታይ...