Monday, May 20, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ብሔራዊ ባንክ የዓባይ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ሹመት አፀደቀ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለዓባይ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንትነት የታጩትን የአቶ በለጠ ዳኘውን ሹመት ማፅደቁ ተገለጸ፡፡

ከባንኩ የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው፣ የአቶ በለጠ ሹመት የፀደቀው የዓባይ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥያቄው ባቀረበ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ ሹመቱ የፀደቀላቸው አዲሱ የዓባይ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ወደ ባንኩ ከመምጣታቸው ቀደም ብሎ፣ የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ የቅርንጫፍ ማስተባበሪያ መምርያ ዳይሬክተር በመሆን ለስድስት ዓመታት ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

በባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ 25 ዓመታት ማገልገላቸው የተገለጸው አቶ በለጠ፣ ኢንዱትሪውን የተቀላቀሉት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመቀጠር ነው፡፡ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሥር ዓመት የሠሩ ሲሆን፣ በኃላፊነት ደረጃም የባንኩ የቅርንጫፍ መመርያ ሥራ አስኪያጅ ሆነው ያገለግሉ እንደነበር የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡

 በአቢሲኒያ ባንክ ውስጥም በተመሳሳይ የኃላፊነት መደብ የቅርንጫፎች መምርያ ኃላፊና የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ በመሆን ሲያገለግሉ እንደነበር ታውቋል፡፡

አቶ በለጠ በኢኮኖሚክስ የመጀመርያ ዲግሪ፣ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ሁለተኛ ዲግሪ አላቸው፡፡

በምክትል ፕሬዚዳንትነት የተሾሙበት ዓባይ ባንክ ከ3,300 በላይ ባለአክሲዮኖች ሲኖሩት፣ ከ90 በላይ ቅርንጫፎች አሉት፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች