Wednesday, February 28, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ለጉዳት ካሳ ከ2.4 ቢሊዮን ብር በላይ ከፈሉ

ተዛማጅ ፅሁፎች

በኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ 17 የኢንሹራንስ ኩባንያዎች፣ በ2007 በጀት ዓመት ለጉዳት ካሳ ከ2.4 ቢሊዮን ብር በላይ መክፈላቸው ታወቀ፡፡

የኢንሹራንስ ኩባንያዎቹ የ2007 ዓ.ም. የመጀመርያ ደረጃ የኦዲት ሪፖርት  እንደሚያመለክተው፣ በበጀት ዓመቱ ከተከፈለው የጉዳት ካሳ ውስጥ ከ65 በመቶ በላይ የተከፈለው ለሞተር ወይም ከተሽከርካሪዎች አደጋ ጋር ለተያያዘ ጉዳት ነው፡፡

ኢንሹራንስ ኩባንያዎቹ ከተሽከርካሪዎች አደጋ ጋር በተያያዘ የሚከፍሉት የካሳ ክፍያ አሁንም ለውጥ ሳያሳይ መቀጠሉን ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡

ኩባንያዎቹ ከሰጡት የኢንሹራንስ ሽፋን ውስጥ 94 በመቶ ሕይወት ነክ ላልሆኑ ኢንሹራንስ ዘርፎች ሲሆን፣ ስድስት በመቶው ብቻ ለሕይወት ኢንሹራንስ ሽፋን የተሰጠ ነው፡፡

ኩባንያዎቹ በተጠቀሰው በጀት ዓመት ያሰባሰቡት የዓረቦን መጠን 5.5 ቢሊዮን ብር ነው፡፡ በጥቅል ካሰባሰቡት ዓረቦን ውስጥ ከ5.3 ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆነው ሕይወት ነክ ካልሆነ የመድኅን ሽፋን የተሰበሰበ ነው፡፡ ከ315 ሚሊዮን ብር በላይ ደግሞ ከሕይወት ኢንሹራንስ የመድን ሽፋን የተሰበሰበ ነው፡፡

ሁሉም የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በበጀት ዓመቱ ከ823 ሚሊዮን ብር በላይ ከታክስ በፊት ማትረፍ እንደቻሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ትርፉ ቀደም ካለው በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር ከ85 ሚሊዮን ብር በላይ ብልጫ አለው፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት 17 የኢንሹራንስ ኩባንያዎች መካከል አንዱ የመንግሥት ሲሆን፣ የቀሩት በባለአክሲዮኖች የተደራጁ የግል ኩባንያዎች ናቸው፡፡

 

 

 

 

 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች