ጥሬ ዕቃዎች
- (1/2) ግማሽ ኪሎ ግራም መኮረኒ
- 6 ጭልፋ ቦለኝዝ ሶስ
- 4 ጭልፋ ባሻሜል ሶስ
- 1 የሾርባ ማንኪያ የገበታ ቅቤ
- 1 ጭልፋ የተፈጨ ቺዝ
- ጨው
አዘገጃጀት
- በቅድሚያ ኦቨኑን በ2500 ሴንቲግሬድ ማሞቅ፤
- በትልቅ ድስት ሁለት ሊትር ውኃና ጨው አፍልቶ መኮረኒው ጥርስ ላይ ያዝ እስከሚያደርግ ድረስ ለአምስት ደቂቃ መቀቀል፤
- መኮሮኒው ከበሰለና ካጠለልነው በኋላ ጎድጓዳ ሰሀን ውስጥ መጨመር፤
- አራቱን ጭላ ቦሎኝዝ መኮረኒው ውስጥ ጨምሮ በደንብ መለወስ፤
- አራት ጭልፋ ባሻሜል ሶስና ጨው ጨምሮ በደንብ መለወስ፤
- የላዛኛ ማብሰያ በደንብ ቅቤ መቀባት፤
- ጎድጓዳ ሰሀን ውስጥ የሚገኘውን መኮረኒ ወደ ላዛኛ ማብሰያ ውስጥ መጨመር፤
- ቀሪውን ሁለት ጭልፋ ቦሎኝዝ ሶስ ከላይ ቀብቶ የተፈጨረውን ቺዝ መነስነስ፤
- ኦቨን ውስጥ አስገብቶ ለ20 ደቂቃ ያህል ማብሰል፤
- ከበሰለ በኋላ የተወሰነ ደቂቃ አቀዝቅዞ ቆራርጦ ማቅረብ፡፡
- ጆርዳና ኩሽና ‹‹የምግብ አዘገጃጀት›› (2007)