Saturday, May 25, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ዳሸን ባንክ የቀድሞ ንግድ ባንክ ባልደረቦች በምክትል ፕሬዚዳንትነት ተሰየሙለት

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵ ንግድ ባንክ የዲስትሪክት ሥራ አስኪያጅ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩ ሁለት የባንክ ባለሙያዎች፣ የዳሸን ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው መሰየማቸው ተሰማ::

የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ በዳሸን ባንክ ቦርድ ጥያቄ ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ ሹመታቸው ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቀርቦ የፀደቀላቸው አቶ ሔኖክ ከበደና አቶ ያሬድ መስፍን ናቸው፡፡ ሁለቱም የባንክ ባለሙያዎች አዲስ አበባ የሚገኙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለት ዲስትሪክቶችን ሲመሩ የቆዩ ናቸው ተብሏል፡፡

ዳሸን ባንክ ከሦስት ወራት በፊት በሁለት የምክትል ፕሬዚዳንትነት ቦታዎች ላይ በኃላፊነት እንዲሠሩ ያቀረባቸውን፣ በባንኩ ውስጥ በተለያዩ የኃላፊነት መደቦች ይሠሩ የነበሩትን የአቶ ኃይሉ ቡልቡላንና የአቶ ጌትነት መስፍንን ሹመት ብሔራዊ ባንክ ሳያፀድቅለት መቅረቱ ይታወሳል፡፡

ከብሔራዊ ባንክ ውሳኔ በኋላ የዳሸን ባንክ ቦርድ ለቦታው የሚመጥኑ ባለሙያዎችን ከባንኩ ውጪ ሲያፈላልግ ቆይቶ፣ ሁለቱን ተሿሚዎች ማግኘት ችሏል፡፡

እንደ ምንጮች ገለጻ፣ አዲሶቹ የዳሸን ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንቶች በቅርቡ ሥራ ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

አቶ ሔኖክ ምክትል ፕሬዚዳንትና የኦፕሬሽን ማኔጅመንት ኃላፊ፣ አቶ ያሬድ ደግሞ ምክትል ፕሬዚዳንትና የሪሶርስ ፋሲሊቲ ሆነው የሚሠሩ መሆኑ ታውቋል፡፡

ዳሸን ባንክ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከግል ባንኮች በአትራፊነት በቀዳሚነት የሚጠቀስ ባንክ ነው፡፡ በ2007 በጀት ዓመት ኦዲት ያልተደረገ የሒሳብ ሪፖርቱ እንደሚያመለክተው፣ ከ950 ሚሊዮን ብር በላይ ማትረፍ ችሏል፡፡ ባንኩ በመላ አገሪቱ ከ200 በላይ ቅርንጫፎች ሲኖሩት፣ የባንኩ የሀብት መጠንም ከ23 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱ ይነገራል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች