Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበቀለም ውስጥ የሚገኝ የእርሳስ ውህድ መጠን እንዲቀነስ አፋጣኝ መፍትሔ ሊወሰድ እንደሚገባ ተገለጸ

በቀለም ውስጥ የሚገኝ የእርሳስ ውህድ መጠን እንዲቀነስ አፋጣኝ መፍትሔ ሊወሰድ እንደሚገባ ተገለጸ

ቀን:

በውጭው ዓለም ከ40 ዓመታት በፊት ጥቅም ላይ እንዳይውል የታገደው የእርሳስ ውህድ በአገር ውስጥ በከፍተኛ መጠን ጥቅም ላይ እየዋለ እንደሚገኝ፤ ነገር ግን የውህዱ መጠን ሊቀንስ እንሚገባ ተገለጸ፡፡ ይህ በሕፃናት ጤና ላይ ከፍተኛ ችግር እንደሚያስከትል ፔስቲሳይድ አክሽን ኔክሰስ አሶሴሽን ማክሰኞ 16 ቀን 2008 ዓ.ም. በካሌብ ሆቴል ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ተገልጿል፡፡

የፔስቲሳይድ አክሽን ኔክሰስ አሶሴሽን ዳይሬክተር አቶ ታደሰ አመራ እንደገለጹት እ.ኤ.አ. በ2013 የተደረገ ጥናት እንደሚያመለክተው በአገር ውስጥ የሚመረቱ የዘይት ቀለሞች የእርሳስ ውህድ መጠን አደገኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ በጥናቱ መሠረት 87 በመቶ የሚሆኑት ባለዘይት ቀለሞች ከፍተኛ የእርሳስ ውህድ መጠን ተገኝቶባቸዋል፡፡ በናሙናው 130,000 ppm የእርሳስ ውህድ የያዙም ነበሩ፡፡ ይህም በሌላው ዓለም ከተፈቀደው 90 ppm የእርሳስ መጠን በ1,400 ጊዜ የበለጠ ነው፡፡

በ2015 በተደረገ ተመሳሳይ ጥናትም የተወሰኑ መሻሻሎች ቢታዩም ችግሩ አሁንም አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተመልክቷል፡፡

የእርሳስ ውህድ ከአዋቂ ይልቅ ታዳጊዎች ላይ በተለይም ከስድስት ዓመት በታች በሆኑ ሕፃናት ላይ የከፋ ጉዳት እንደሚያደርስ የተናገሩት በፔስቲሳይድ አክሽን ኔክሰስ አሶሴሽን በአፍሪካን ሊድ ፔይንት ኢሊሚኔሽን ፕሮጀክት ኦፊሰር አቶ ልዑልሰገድ ሙሉጌታ ናቸው፡፡ በዕለቱ የሊድ ውህድ በሕፃናት ጤና ብሎም በአንድ አገር የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ የሚኖረውን አሉታዊ ተፅዕኖ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ አስረድተዋል፡፡

በጥናቱ መሠረት የሕፃናት የእርሳስ ተጋላጭነት በማይክሮ ግራም ይለካል፡፡ በመጨረሻው ዝቅተኛ የእርሳስ ተጋላጭነት እይታ በደም ውስጥ የእርሳስ መጠን መጨመር በቅድመ ትምህርት ቤት ባሉ ሕፃናት ላይ ይበረታል፡፡ የማሰብ አቅማቸውንም በስድስት ጊዜ ይቀንሳል፡፡ በተጨማሪም በመጀመሪያዎቹ የዕድሜ ክልል ላይ የሚፈጠር የእርሳስ ተጋላጭነት ዘረመልን ይቀይራል፡፡ ‹‹ለምሳሌ ከወሊድ በፊት በተፈጠረ የእርሳስ ተጋላጭነት የመጣ የዘረመል ለውጥ የመርሳት በሽታን ያስከትላል፤›› ብለዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ የኬሚካልና ኬሚካል ውጤቶች ደረጃ ዝግጅት ባለሙያ አቶ ታሪኩ ጫኔ እንዳሉት መሥሪያ ቤቱ ተጨማሪ ጥናት በማድረግ ችግሩ እንደተባለው አሳሳቢ ሆኖ ከተገኘ አፋጣኝ መፍትሔ ይሰጣል፡፡ ‹‹ከዚህ ቀደም በነበረን አሠራር የሚመረቱ ቀለሞች ጥራት፣ ምን ያህል ጊዜ ያገለግላሉ፣ ፀሐይና ዝናብ የመቋቋም አቅማቸው ምን ድረስ ነው፣ ከተቀቡ በኋላ በምን ያህል ጊዜ ይደርቃሉ፣ ውበቱስ ምን ይመስላል በሚል መስፈርት ነበር የምትፈትሸው፡፡ አሁን ግን የሊድ መጠኑ ምን ድረስ እንደሆነ ለመለካት እንገደዳለን፤›› ብለዋል፡፡

በመድረኩ ከተገኙ የቀለም ፋብሪካዎች መካከል ለሰባት ዓመታት ያህል ገበያ ላይ የቆየው ብራይት ቀለም ፋብሪካ ይገኝበታል፡፡ አቶ አብርሃም ብርሃኔ የፋብሪካው ባለቤትና የቴክኒክ ኃላፊ ሲሆኑ ፋብሪካቸው ከሁለት ዓመት በፊት የእርሳስ ንጥረ ነገር መጠቀም እንዳቆመ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ፋብሪካችን ንጥረ ነገሩን መጠቀም ያቆመው ከውጭ የምናስገባው የሊድ እሽግ ላይ የነበረውን መረጃ አንብበን ነው፡፡ ከዚያ በኋላ በእርሳስ ምትክ ዚርኮኒየም የተባለውን ንጥረ ነገር እየተጠቀምን እንገኛለን፡፡ ሁሉም ፋብሪካ እርሳስ ጐጂ መሆኑን ያውቃል፡፡ ነገር ግን ምን ያህል ጐጂ እንደሆነ በውል አይታወቅም፤›› በማለት ተቋሙ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ቢሠራ አጥጋቢ ምላሽ ማግኘት እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

ምንም እንኳ የእርሳስ ውህድ በየትኛውም መጠን አደገኛ ቢሆንም በዓለም ገበያ እስከ 90 ppm የእርሳስ መጠን ያላቸው ቀለሞች ተቀባይነት አላቸው፡፡ በአገር ውስጥም ከ90 ppm ያልበለጠ ማምረት እንዲቻል ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ ነገር ግን ‹‹አንድ ፋብሪካ የእርሳስ መጠኑ ከ90 ppm በላይ ይሁን አይሁን የሚያረጋግጥበት ላብራቶሪ የለውም፤›› ያሉት የንፋስ ስልክ ቀለም ፋብሪካ ኬሚካል ኢንጂነር ናቸው፡፡ እሳቸው እንደሚሉት ከግንዛቤ ማስጨበጫው ጐን ለጐን የላብራቶሪው ጉዳይ ሊታሰብበት ይገባል፡፡ ‹‹አለዚያ ምን ያህል የእርሳስ ውህድ እንዳለው ለማሳየት ወደ አውሮፓና ሌሎች አገሮች ሲላክ ከፍተኛ ወጪ ያስወጣል፤›› ብለዋል፡፡       

spot_img
Previous article
Next article
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...