Tuesday, April 23, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የህንዱን ጂንስ ፋብሪካ ሥራ አስጀመሩ

ተዛማጅ ፅሁፎች

ከአንድ ወር በኋላ የጂንስ አልባሳትን ወደማምረት ተግባር እንደሚሸጋገር ይፋ ያደረገው የህንዱ ካኖሪያ አፍሪካ ቴክስታይልስ ኩባንያን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝና ሌሎች ባለሥልጣናት በፋብሪካው በመገኘት ሥራ አስጀመሩ፡፡  በአሁኑ ወቅት በቀን 55 ሺሕ ሜትር የጂንስ ክር የሚያመርትበትን ፋብሪካ ቅዳሜ ጥቅምት 13 ቀን 2008 ዓ.ም. በቢሾፍቱ ከተማ አስመርቋል፡፡

በ45 ሚሊዮን ዶላር ሥራ የጀመረው ካኖሪያ ትልልቅ የአሜሪካ ኩባንያዎች ላይ ማተኮሩንና ከወዲሁ ጥያቄ እየቀረበለት እንደሚገኝ ሪፖርተር ያነጋረገራቸው የኩባንያው ምክትል ፕሬዚዳንት መግለጻቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በቢሾፍቱ ከተማ የተገነባው የህንዱ ፋብሪካ፣ ሥራ ከጀመረ ከወዲሁ ትልልቅ አልባሳት ገዥዎችና የፋሽን ኩባንያዎች ምርቱን እየተጠባበቁ እንደሚገኙ ለሪፖርተር የገለጹት የኩባንያው የገበያ ዘርፍ ምክትል ፕሬዚዳንት ጃይ ሶያንታር ናቸው፡፡

ካኖሪያ በአብዛኛው የጂንስ ጨርቆችን በማምረት ለውጭ ገበያ እንደሚያቀርብ ሲጠበቅ ከወዲሁ ፒቪኤች፣ ቪኤፍ ኮርፖሬሽን እንዲሁም ጄ.ሲ. ፔሪ የተባሉ የአሜሪካ ግዙፍ ኩባንያዎች ለመግዛት እየተጠባበቁ እንደሚገኙ ሶያንታር አስታውቀዋል፡፡ በዓመት ከአንድ ሚሊዮን ሜትር በላይ የጂንስና የሌሎች አልባሳት ጨርቆችን በማምረት ለገበያ የማቅረብ አቅም ያለው ፋብሪካ መሆኑም ተነግሮለታል፡፡ 

ፋብሪካው በይፋ ሥራ መጀመሩን በማስመልከት በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ የኩባንያው ኃላፊዎች ይፋ እንዳደረጉት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መስተጓጎል እንዳያጋጥመው 130 ኪሎ ቮልት የሚሸከም የኃይል ማሰራጫ መስመር ተዘርግቶለታል፡፡ በአሁኑ ወቅት 400 ሠራተኞችን በመቅጠር ሥራውን የጀመረ ሲሆን፣ ወደፊት የሠራተኞቹ ቁጥር እንደሚጨምርም ይጠበቃል፡፡

ካኖሪያ ፋብሪካን ጨምሮ በአገሪቱ ከሚንቀሳቀሱ 130 ያህል የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ የክር ማምረቻና የስፌት ፋብሪካዎች በጠቅላላው በየዓመቱ አንድ ቢሊዮን ዶላር የኤክስፖርት ገቢ ሲጠበቅ፣ ከአምስት ዓመት በኋላም በዘርፉ የሚመሩት ምርቶች 4.5 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ዋጋ እንደሚኖራቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች