Friday, December 2, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisment -
  - Advertisment -

  ክቡር ሚኒስትር

  [ክቡር ሚኒስትሩ ከውጭ ስልክ ተደወለላቸው]

  • ሄሎ ክቡር ሚኒስትር!
  • ሄሎ ማን ልበል?
  • ከአሜሪካ ወዳጅዎት ነኝ፡፡
  • እንዴት ነህ ባክህ?
  • አለሁ ክቡር ሚኒስትር፣ አልተቻላችሁም እኮ፡፡
  • ደግሞ ምን አደረግን?
  • ሰሞኑን ተቆጣጥራችሁት የለም እንዴ?
  • ምኑን ነው የተቆጣጠርነው?
  • ሚዲያውን ነዋ፡፡
  • ሚዲያው የእኛው አይደል እንዴ?
  • የአገር ውስጡን ማለቴ አይደለም፡፡
  • ታዲያ የቱን ነው የምትለኝ?
  • የውጭውን ነዋ፡፡
  • ደግሞ ምን አሉ?
  • እርስዎ ግን ማታ ቲቪ አያዩም እንዴ?
  • በደንብ ነው እንጂ የማየው፡፡
  • እኮ የቱን ቲቪ ነው የሚያዩት?
  • ልማታዊውንና የአገራችንን ነዋ፡፡
  • የውጭውን አያዩም ማለት ነው?
  • ኪራይ ሰብሳቢዎችን ለማጥፋት እየታገልን ደግሞ መልሰን እነሱን እንድናበረታታቸው ትፈልጋለህ?
  • ሰሞኑን እኮ በተከታታይ ስለኢትዮጵያ በሲኤንኤን ላይ እየተዘገበ ነው፡፡
  • ይኼን የጭቃ ጅራፋቸውን ጀመሩ ማለት ነው?
  • የምን የጭቃ ጅራፍ?
  • በቃ ኢትዮጵያ ዳግም በረሃብ ተጠቃች ምናምን እያሉ ነዋ፡፡
  • ኧረ እንደሱ አላሉም፡፡
  • ከኒዮሊብራሊስቶች ሌላ ምን ይጠበቃል ታዲያ?
  • ኧረ ኢትዮጵያ ተመንድጋለች እያሉ ነው፡፡
  • አያዩም ብለህ ትቀልድብኛለህ አይደል?
  • ሲኤንኤን አይተው አያውቁም ሰሞኑን?
  • ይኼን ኪራይ ሰብሳቢ ቻናል ምን ይጠቅመኛል ብዬ ነው የማየው?
  • ብቻ ለማንኛውም ስለኢትዮጵያ ዕድገት የተለያዩ ዘገባዎች ሰሞኑን በተከታታይ እየታዩ ነው፡፡
  • እውነትህን ነው?
  • እውነቴን ነው ስልዎት፡፡
  • እኔ እኮ ድሮም ነግሬህ ነበር፡፡
  • ምን ብለው?
  • የአገራችን ስም በዓለም ላይ ይቀነቀናል አላልኩህም ነበር፡፡
  • ጀመረዎት እንግዲህ፡፡
  • ምኑ ነው የጀመረኝ?
  • ይኼ ኩፈሳ ነዋ፡፡
  • ምን ኩፈሳ ነው በዓይንህ እያየኸው አይደል እንዴ?
  • ክቡር ሚኒስትር እንዳይሳሳቱ፡፡
  • እንዴት?
  • አገሪቷ ውስጥ ዕድገት የለም አላልኩም፡፡
  • እኛ ስንናገር አላምን ስትሉ ይኸው የምታምኑት ሚዲያ ዕድገት መኖሩን ተናገረ፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር ጥንቃቄ ያስፈልጋል የምለው ለዚህ ነው፡፡
  • የምን ጥንቃቄ?
  • ሲኤንኤን አገሪቱ አድጋለች ስላለ ሌላው የቤት ሥራ ሊረሳ አይገባም፡፡
  • የምን የቤት ሥራ?
  • ዕድገት ቢኖርም ከእሱ ጐን መንግሥት ሊመልሳቸው የሚገቡ በርካታ ጥያቄዎች አሉ፡፡
  • የምን ጥያቄ?
  • የመልካም አስተዳደር፣ የሙስና፣ የቢሮክራሲ፣ የፍትሕ፣ የጐደለውን እርስዎ ይሙሉበት፡፡
  • እነሱማ መቼ ሞልተው ያውቃሉ?
  • ስለዚህ እነሱ እስኪሟሉ ድረስ መሠራት አለበት፡፡
  • ምኑ?
  • የቤት ሥራው፡፡

   

  [ክቡር ሚኒስትሩ አማካሪያቸውን አስጠሩት] 

  • አቤት ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • አንተ ስልክህን አታጥፋ አላልኩህም እንዴ?
  • ኧረ እኔ አላጠፋሁም፡፡
  • ዛሬ ስንቴ እንደደወልኩልህ ታውቃለህ?
  • አላውቅም ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ከሃያ ጊዜ በላይ ነው የሞከርኩልህ፡፡
  • እንግዲህ ኔትወርኩ ይሆናላ፡፡
  • የምን ኔትወርክ ነው የምታወራው?
  • የመሥሪያ ቤታችንን ሳይሆን የቴሌን ነዋ፡፡
  • የቴሌ ኔትወርክማ ምን ይወጣለታል?
  • ምንም ተዋጥቶለት አያውቅም፡፡
  • መሸለሙን አልሰማህም እንዴ?
  • ማን ነው የተሸለመው?
  • ቴሌ ነዋ፡፡
  • በምንድን ነው የተሸለመው?
  • በጥራት ነዋ፡፡
  • ፅድቁ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ አሉ፡፡
  • አሽሙርህን እዛው፡፡
  • ተሸለመ ሲሉኝ ገርሞኝ እኮ ነው፡፡
  • የተሸለመው እኮ በአውሮፓውያን ነው፡፡
  • ጭራሽ?
  • እናሳ፡፡
  • የሽልማት ጉዳይ እኮ መጣራት አለበት፡፡
  • ምኑ ነው የሚጣራው?
  • አንዳንድ ድርጅቶች እኮ ዝም ብለው ነው ሽልማት የሚሰጡት፡፡
  • ለምንድን ነው ዝም ብለው የሚሸልሙት?
  • እነሱም ዝም ብለው ገንዘብ ስለሚሸለሙ ነዋ፡፡
  • ማን ነው የሚሸልማቸው?
  • ሽልማቱን የሚሰጧቸው ድርጅቶች ናቸዋ፡፡
  • እና እርስ በእርስ ነው የሚሸላለሙት ነው የምትለኝ?
  • አዎ አንዱ ሰርተፊኬት ይሸልመዋል ሌላው ደግሞ ገንዘብ ይሸልመዋል፡፡
  • ልክ እንደ አዝማሪ ቤት?
  • አሁን በደንብ የገባዎት መሰለኝ፡፡
  • ስለዚህ ተሸለምኩ ሲሉን ማመን የለብንም እያልከኝ ነው?
  • አንድ ነገር ማረጋገጥ አለብን፡፡
  • ምንድን ነው ማረጋገጥ ያለብን?
  • እነሱም አለመሸለማቸውን፡፡

  [ክቡር ሚኒስትሩ የሰው ኃይል አስተዳደሩን አስጠሩት] 

  • ፈለጉኝ ክቡር ሚኒስትር?
  • አንተ ግን አንድ ሰው ለመቅጠር አንድ ዓመት ሊፈጅብህ ነው?
  • ምን ላድርግ ክቡር ሚኒስትር?
  • ምን ማለት ነው ምን ላድርግ?
  • የሚመጥን ሰው እኮ አጥቼ ነው፡፡
  • ለምንድን ነው ሰው የጠፋው?
  • ሁሉም ፈተናውን ወደቁ፡፡
  • እንዴት ሁሉም ፈተናውን ሊወድቁ ይችላሉ?
  • ክቡር ሚኒስትር በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሰናል፡፡
  • የምን አሳሳቢ ደረጃ?
  • አንድ ዓረፍተ ነገር እንኳን በቅጡ መጻፍ አይችሉም፡፡
  • ለምን ሲባል?
  • እኔም ግራ ገብቶኛል፡፡
  • ማስታወቂያው ሲወጣ ዲግሪ ያላቸው ተብሎ አይደል እንዴ የወጣው?
  • በሚገባ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ታዲያ እንዴት ዓረፍተ ነገር መጻፍ ያቅታቸዋል?
  • ይኼ የሚያመላክተው የትምህርት ጥራት ጉዳይ አሳሳቢ መሆኑን ነው፡፡
  • ምን እያልክ ነው?
  • የትምህርት ጥራት ጉዳይ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው እያልኩኝ ነው፡፡
  • ኪራይ ሰብሳቢ ነህ ልበል?
  • እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
  • አንተ አሁን ከUN እበልጣለሁ እያልክ ነው?
  • እኔ እንደ ተቆርቋሪ ዜጋ ነው የነገርኩዎት፡፡
  • ይኸው UN ያወጣው ሪፖርት ኢትዮጵያ በትምህርት በኩል የልማት ግቡን ለማሳካት ከጫፍ ደርሳለች እያለ አይደል እንዴ?
  • ምርጫው የእኛው ነው፡፡
  • የምን ምርጫ?
  • በUN ሪፖርት መደስኮር ወይም ለችግራችን ትክክለኛ መፍትሔ ማፈላለግ፡፡
  • የምን ችግር ነው?
  • ይኸው ፈተናውን ያለፈ ሰው የለማ፡፡
  • አክብደኸው ይሆናላ፡፡
  • ኧረ ስታንዳርድ ፈተና ነው፡፡
  • እስቲ ፈተናውን አሳየኝ፡፡
  • ይኸው ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • በእንግሊዝኛ ነው እንዴ?
  • ክቡር ሚኒስትር ሥራው እኮ ከውጭ ድርጅቶች ጋር የሚያገናኝ ነው፡፡
  • እሱስ እውነትህን ነው፡፡
  • እስቲ እርስዎ ራስዎ ይሥሩት፡፡
  • እ…
  • ምነው ከበድዎት እንዴ?
  • ማን እኔ? እንኳን ይኼን…
  • ኧረ አውቃለሁ እርስዎ ጥይት አይደሉ እንዴ?
  • የምን ጥይት?
  • የመድፍ ነዋ፡፡
  • ለማንኛውም ፈተናው ይቅለል፡፡
  • ከዚህ በታች?
  • አዎና፡፡
  • የምንቀጥራቸውም ሰዎች ግን እንደ ፈተናው ነው የሚሆኑት፡፡
  • እንደፈተናው ስትል አልገባኝም፡፡
  • ቀላል፡፡

  [ክቡር ሚኒስትሩ ቤት ሲገቡ ሚስታቸውን አገኙዋቸው] 

  • እንዴት ዋልሽ?
  • ባክህ ሰልችቶኛል፡፡
  • ምኑ?
  • ቤት መወዘፉ፡፡
  • ዲኤስቲቪ አስገባ ብለሽኝ አስገባሁ፡፡
  • እሱም ይሰለቻል፡፡
  • የአገር ውስጡን አታይም ታዲያ?
  • እሱም በጣም ይሰለቻል፡፡
  • ምን ተሻለ ታዲያ?
  • ሥራ ያስፈልገኛል፡፡
  • የምን ሥራ?
  • ሥራ ፍጠርልኝ፡፡
  • ተምረሻል?
  • አንተ እያለህ እንዴት እማራለሁ?
  • እኔ ደግሞ ምን ላድርግሽ?
  • ይኸው የቤት እመቤት አድርገህ አስቀረኸኝ፡፡
  • ለምን አትደራጂም ታዲያ?
  • የት ነው የምደራጀው?
  • በአነስተኛና ጥቃቅን ነዋ፡፡
  • ይኼ ነበር የቀረህ?
  • ምን አለበት?
  • አሁን ባክህ አንድ ሱቅ ክፈትልኝ፡፡
  • የምን ሱቅ?
  • ኬክ ቤት ነገር፡፡
  • የት ነው የምከፍትልሽ?
  • አንዱ ባለሀብት ሞል ላይ ነዋ፡፡
  • እሱስ ተከፈተ ስኳሩና ዱቄቱ ከየት ይመጣል?
  • ከእናንተ መሥሪያ ቤት ነዋ፡፡
  • አሁን የሚገርም ሐሳብ አመጣሽ፡፡
  • እንዴት?
  • በዚህ እንዲያውም የመሥሪያ ቤታችን የዘመናት ችግር ይቀረፋል፡፡
  • የምን ችግር?
  • የሀብት ብክነት ችግር ነዋ፡፡
  • ስለዚህ ኬክ ቤቱን ትከፍትልኛለህ?
  • በአንድ ስልክ እጨርሰዋለሁ፡፡

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

  አሜሪካ ሕወሓትን በማሳመንና በመጫን በሰላም ሒደቱ ትልቅ ሚና መጫወቷን የኢትዮጵያ ዋና ተደራዳሪ አስታወቁ

  የተመድና የአውሮፓ ኅብረት አበርክቶ አሉታዊ እንደነበር ጠቁመዋል በመንግሥትና በሕወሓት መካከል...

  የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅን የሚተካ ረቂቅ ተዘጋጀ

  ከቫት ነፃ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ገደብ ተቀመጠለት የገንዘብ ሚኒስቴር ከሃያ...

  አዋሽ ባንክ ለሁሉም ኅብረተሰብ የብድር አገልግሎት የሚያስገኙ ሁለት ክሬዲት ካርዶች ይፋ አደረገ

  አዋሽ ባንክ ለሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች በዘመናዊ መንገድ ብድር ማስገኘት...

  የአገር ውስጥ የፍራፍሬ ገበያን ፍላጎት ይሸፍናል የተባለለት የብላቴው እርሻ ልማት

  መንግሥት የግብርና ምርታማነትና የፍራፍሬ ምርትን ለማሳደግ በ‹‹አረንጓዴ አሻራ›› በሚል...
  - Advertisment -

  ትኩስ ፅሁፎች

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...

  የጉድለታችን ብዛቱ!

  ከፒያሳ ወደ ሜክሲኮ ልንጓዝ ነው። ጎዳናውን ትውስታ እየናጠው ሁለትና...
  spot_img

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር! ቀድሜ ቀጠሮ እንዲያዝልኝ ስጠይቅ እንደገለጽኩት በተቋሙ ሠራተኛ ተወክዬ ነው የመጣሁት። እንዴ? አንተ የእኛ ተቋም ባልደረባ አይደለህም...

  [የተቃዋሚ ፓርቲው ትይዩ ሚኒስትር ክቡር ሚኒስትሩ ጋ ደውለው መንግሥት በሙሰኞች ላይ ለመውሰድ ስላሰበው የሕግ ዕርምጃ ሐሳብ እየተለዋወጡ ነው]

  ሄሎ… ማን ልበል? ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ጤና ይስጥልኝ… ማን ልበል? የእርስዎ ትይዩ ነኝ፡፡  አቤት? ያው ፓርቲዬን ወክዬ የፍትሕ ሚኒስትሩ ትይዩ ነኝ ማለቴ ነው፡፡ ኦ... ገባኝ… ገባኝ...  ትንሽ ግራ አገባሁዎት አይደል? ትይዩ...

   [ክቡር ሚኒስትሩ እራት እየበሉ መንግሥትን በሚተቹ ጋዜጠኞች ላይ እየተወሰደ ያለውን ዕርምጃ የተመለከተ መረጃ እየቀረበላቸው ነው]

  ለጋዜጠኞቹ መንግሥትን እንዲተቹ መረጃ የሚሰጧቸው ታሪካዊ ጠላቶቻችን ናቸው፡፡ እነሱ አይደሉም፡፡ እና የትኞቹ ናቸው? እዚሁ ከተማችን የሚገኙ ምዕራባውያን ናቸው። እንዴት ነው መረጃውን የሚያቀብሏቸው? እራት እያበሉ ነው። ምን? አዎ፣ እራት ግብዣ ይጠሯቸውና መተቸት...