Tuesday, November 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለድርቅ ተጎጂዎችና ገበያ ለማረጋጋት ለሚገዛው አንድ ሚሊዮን ቶን ስንዴ ስምምነት ተፈጸመ

ለድርቅ ተጎጂዎችና ገበያ ለማረጋጋት ለሚገዛው አንድ ሚሊዮን ቶን ስንዴ ስምምነት ተፈጸመ

ቀን:

በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የምግብ እጥረት ችግር ለደረሰባቸው ወገኖችና በከተሞች ገበያን ለማረጋጋት፣ አንድ ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ስንዴ ለመግዛት የወጣውን ጨረታ ካሸነፉ ኩባንያዎች ጋር ስምምነት ተፈጸመ፡፡

የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ይገዙ ዳባ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ባለፈው ሐሙስ ጥቅምት 19 ቀን 2008 ዓ.ም. ጨረታውን ላሸነፉ ኩባንያዎች ሥራው ተሰጥቷል፡፡ ይህ ጨረታ የተከፈተው ጥቅምት 12 ቀን 2008 ዓ.ም. ሲሆን፣ በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አብርሃ ተከስተ የሚመራው የአገልግሎት ድርጅቱ ቦርድ የጨረታውን ውጤት በማፅደቁ ስምምነት ሊፈጽም ችሏል፡፡

ግዥ እንዲፈጸም ከተወሰነው አንድ ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ስንዴ ውስጥ 400 ሺሕ የሚሆነው በዝናብ እጥረት ምክንያት የምግብ ዋስትና ችግር ለገጠማቸው ዜጐች የሚውል ነው፡፡ ይህ ስንዴ በቀጥታ በእርሻና የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር ሥር ለሚገኘው የስትራቴጂክ መጠባበቂያ ምግብ ክምችት ኤጀንሲ ገቢ የሚደረግ ነው፡፡

ቀሪው 600 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ደግሞ በከተሞች ገበያ ለማረጋጋት የሚውል ሲሆን፣ የስንዴው ባለቤት የኢትዮጵያ እህል ንግድ ድርጅት ነው፡፡

ይህንን ስንዴ ወደ አገር እንዲያስገቡ ሥራው የተሰጣቸው አሥር ያህል ኩባንያዎች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ሀከትና ግሌን ኮር የተሰኙ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ይገኙበታል፡፡ የሚገዛው ስንዴ በሁለቱ መንግሥታዊ ተቋማት አማካይነት በቅርቡ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ተከፍቶ እንዲገባ ይደረጋል፡፡

በስንዴ ግዢው የቀረበው ዝቅተኛ ዋጋ በአንድ ቶን 233.26 ዶላር ሲሆን፣ ከፍተኛው ደግሞ 265.25 ዶላር ነው፡፡

በዝናብ እጥረት ምክንያት በድርቅ ለተጐዱ የኅብረተሰብ ክፍሎች ቀደም ሲል 222 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ስንዴ እንዲገዛ ተወስኖ ነበር፡፡ ይህንን ስንዴ ለማቅረብ የወጣውን ጨረታ ያሸነፉት ፓኔክስና ፕሮሚሲንግ የተሰኙ ኩባንያዎች ናቸው፡፡ አቶ ይገዙ እንዳሉት፣ ይህ ስንዴ በአሁኑ ወቅት ሌተር ኦፍ ክሬዲት ተከፍቶ ወደ አገር እንዲገባ እየተደረገ ነው፡፡

መንግሥት በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት 8.2 ሚሊዮን ዜጐች ለምግብ እጥረት ተዳርገዋል፡፡ ይህንን ችግር ለመፍታት መንግሥት እስካሁን አራት ቢሊዮን ብር ያወጣ መሆኑ ተገልጾ፣ በአጠቃላይ እስከ 12 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግም ይፋ ተደርጓል፡፡

መንግሥት ችግሩን ለመቅረፍ ከአገር ውስጥ ገበያ 50 ሺሕ ሜትሪክ ቶን በቆሎ በመግዛት ላይ ሲሆን፣ በቅርብም የምግብ ዘይት ለመግዛት መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡ መንግሥት ለችግሩ ሰለባዎች የተለያዩ የሰብዓዊ ድጋፎች በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡ የሰዎችን ሕይወት ከመታደግ በተጨማሪም፣ በተለይ ለአርብቶ አደሮች የእንስሳት መኖ በማከፋፈል ላይ እንደሚገኝ ተመልክቷል፡፡

በእርሻና የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ምትኩ ካሳ፣ እስካሁን ከለጋሾች ድጋፍ ባለመገኘቱ መንግሥት በራሱ አቅም ችግሩን ለመቅረፍ እየሠራ መሆኑን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል በምሥራቅ አፍሪካ በተከሰተው የኤልኒኖ የአየር ፀባይ ምክንያት በተከሰተ ድርቅ፣ ከሁለት ወራት በኋላ የተረጂዎች ቁጥር 22 ሚሊዮን እንደሚደርስ የተገመተ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ አሁን ያለው የ8.2 ሚሊዮን የድርቅ ተጎጂዎች ቁጥር አድጎ 15 ሚሊዮን ሊደርስ እንደሚችል ተተንብይዋል፡፡ ይህ ድርቅ ባለፉት 30 ዓመታት ከደረሱት ሁለ የከፋው ነው እየተባለ ነው፡፡     

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ ሲኒመር ትሬዲንግ...

የባህር በር በቀጣናዊ ተዛምዶ ውስጥ

በበቀለ ሹሜ መግቢያ በ2010 ዓ.ም. መጋቢት ማለቂያን ይዞ ዓብይ አህመድ በጠቅላይ...

ሥጋት ያስቀራል ተብሎ የሚታሰበው የጫኝና አውራጅ መመርያ

በአዲስ አበባ ከተማ በሕገወጥ መልኩ በመደራጀት ማኅበረሰቡ ላይ እንግልትና...

ማወቅ ወይስ አለማወቅ – ድፍረት ወይስ ፍርኃት?

በአሰፋ አደፍርስ ወገኖቼ ፈርተንም ደፍረንም የትም አንደርስምና ለአገራችን ሰላምና ክብር...