የመጻሕፍት ዓውደ ርእይ በአዳማ
ዝግጅት፡- ‹‹አዳማ መጻሕፍት ታነባለች›› በሚል መሪ ቃል የመጻሕፍት ዓውደ ርእይ በአዳማ ከተማ የተዘጋጀ ሲሆን፣ የመጻሕፍት ሽያጭና የሥነ ጽሑፍ ምሽቶች ይካሄዳሉ፡፡ ለአዳማ ማረሚያ ቤት መጻሕፍት ይለገሳሉ፡፡ ከአዲስ አበባ፣ ሻሸመኔ፣ አዋሳና አዳማ የተውጣጡ መጻሕፍት ሻጮችና አሳታሚዎች ይሳተፋሉ፡፡
ቀን፡- ከጥቅምት 26 እስከ 30፣ 2008 ዓ.ም.
ቦታ፡- አዳማ ከተማ
አዘጋጅ፡- አዳማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ፣ ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲና እናት ማስታወቂያ
****
የሙዚቃ ምሽት
ዝግጅት፡- የባላገሩ አይዶል አሸናፊ ዳዊት ድጌ የምስጋና የሙዚቃ ምሽት አዘጋጅቷል
ቀን፡- ጥቅምት 27
ቦታ፡- ባታ የባህል ምግብ ቤትና መናፈሻ ፓርክ
ሰዓት፡- 12፡30
አዘጋጅ፡- እንዳሻው የኪነ ጥብብ ፕሮሞሽን
****
ውይይት
ዝግጅት፡- ‹‹ወሬሳ›› በተሰኘው የዓለማየሁ ገላጋይ መጽሐፍ ላይ ውይይት የሚካሄድ ሲሆን፣ መነሻ ሐሳብ በአብነሳ ስሜ ይቀርባል
ቀን፡- ጥቅምት 28
ቦታ፡- ብሔራዊ ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ (ወመዘክር) አዳራሽ
ሰዓት፡- 8፡00
አዘጋጅ፡- ጎተ ኢንስቲትዩት፣ እናት ማስታወቂያና፣ ወመዘክር
****
የሙዚቃ ኮንሰርት
ዝግጅት፡- የፖላንድ የነፃነት ቀን ክብረ በዓልን ምክንያት በማድረግ ግርማ ይፍራሸዋ፣ ማርያ ፓሚያኖስካና ሌሎችም ሙዚቀኞች በጥምረት ኮንሰርት ያቀርባሉ
ቀን፡- ኅዳር 10
ቦታ፡- ሸራተን አዲስ ሆቴል
ሰዓት፡- 12፡00
አዘጋጅ፡- ፖላንድ ኤምባሲ