- Advertisement -

ክቡር ሚኒስትር

[የክቡር ሚኒስትሩ አንድ ወዳጅ ስልክ ደወለላቸው]

  • ሰላም ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እንዴት ነህ ወዳጄ?
  • አለሁ ክቡር ሚኒስትር፣ ገርሞኝ እኮ ነው የምደውለው፡፡
  • ምኑ ነው የገረመህ?
  • ተሻሽላችኋል አይደል እንዴ?
  • ማነው የተሻሻለው?
  • እናንተው ናችኋ፡፡
  • ምንድነው የምታወራው?
  • ሰሞኑን ቲቪ አላዩም እንዴ?
  • ሥራ ስለበዛብኝ አላየሁም፡፡
  • በቴሌቪዥን ሲታዩ ነበር እኮ፡፡
  • ምን ሳደርግ?
  • የመልካም አስተዳደሩ ውይይት ላይ ነዋ፡፡
  • እ…
  • ምነው ክቡር ሚኒስትር?
  • ተላለፈ እንዴ?
  • ለሁለት ተከታታይ ቀናት ነው የተላለፈው፡፡
  • ጉድ ፈልቷል በለኛ?
  • ምን ጉድ አለው?
  • አይ ተወው ወዲህ ነው፡፡
  • እኔ ግን በጣም ደስ ብሎኛል፡፡
  • ምኑ ነው ደስ ያለህ?
  • ባለሥልጣኖቻችን እንዲህ በግልጽ ስትወያዩ ሳይ አስደስቶኛል፡፡
  • ለመሆኑ እያንዳንዱ ነገር ነው እንዴ የተላለፈው?
  • የተቆራረጠ ነገር እንዳለው ያስታውቃል፣ ግን የተላለፈውም ቢሆን አስገራሚ ነው፡፡
  • መቼም አሳልፈው አይሰጡኝም?
  • ማነው አሳልፎ የሚሰጠዎት?
  • የተወራውን ሁሉ አስተላልፈው ነዋ፡፡
  • ወሬ ብቻ ምን ያደርጋል ክቡር ሚኒስትር?
  • ምን እያልክ ነው?
  • እንደዚያ ተወርቶ ወደ ተግባር ካላወጣችሁት ምንም ፋይዳ የለውም፡፡
  • ይኸው በቲቪ መተላለፉ ራሱ አንዱ ተግባር ነው፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር ሕዝብ እኮ ሰልችቶታል፡፡
  • ምኑ?
  • ወሬ!
  • የአሁኑ ግን በወሬ ብቻ የሚቀር አይመስለኝም፡፡
  • እሱን ነው የምለዎት፣ በወሬ ሲቀር እኮ አደጋ አለው፡፡
  • የምን አደጋ?
  • ምርጫውን ሙሉ ለሙሉ ያሸነፋችሁት እናንተው ናችኋ?
  • እሷን ነገር አሁን ነው መዘዟ እየገባችኝ የመጣችው፡፡
  • የምን መዘዝ?
  • ማሳበቢያ የለማ፡፡
  • ሕዝቡ ሰበብ ሳይሆን መፍትሔ ነው የሚፈልገው፡፡
  • እሱ እኮ ነው ግራ ያጋባን፡፡
  • ከልብ ካለቀሱ እንባ አይገድም አይደለም ነው የሚባለው፡፡
  • ማልቀስማ አልቅሰናል፣ መፍትሔው ነው የጠፋው፡፡
  • ለማንኛውም ሕዝቡ አሁን ጥሪ አይቀበልም፡፡
  • የምን ጥሪ?
  • የሰበብ!

 

[የክቡር ሚኒስትሩ ወዳጅ ሚኒስትር ደወሉ]

  • አዩት እንዴ ክቡር ሚኒስትር?
  • መተላለፉን ራሱ አሁን ነው የሰማሁት፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር ይኼ ጊዜ ወሳኝ ነው፡፡
  • በጣም ወሳኝ እንጂ፡፡
  • እርስዎ ላይ እንደዚያ ይረባረቡብዎታል ብዬ አላሰብኩም ነበር፡፡
  • ከፍቼ ስጫወት ተገኘኋ፡፡
  • ግድ የለም አሁን መጠናከር ያለብን ጊዜ ነው፡፡
  • የምን መጠናከር?
  • ኔትወርካችን መጠናከር አለበት፡፡
  • እየቀለድክ ነው?
  • ክቡር ሚኒስትር ቀልድ ያጠናክረናል ብዬ አላስብም፡፡
  • ትሰማኛለህ ወዳጄ?
  • በሚገባ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • አሁን መጠናከር ያለበት የቴሌ ኔትወርክ እንጂ የእኛ ኔትወርክ አይመስለኝም፡፡
  • ምን ነካዎት ክቡር ሚኒስትር፣ አሁን ነው እንጂ በደንብ መደራጀት ያለብን?
  • አትቀልድ ሰውዬ!
  • የምን ቀልድ ነው?
  • መደራጀት ያለባቸው አነስተኛና ጥቃቅኖቹ ናቸው፡፡
  • እንዲህማ እጅ አይስጡ፡፡
  • እኔ በቃኝ፡፡
  • ምኑ ክቡር ሚኒስትር?
  • መደራጀቱም፣ ኔትወርኩም፣ ግምገማውም፣ ወቀሳውም፣ ለቅሶውም በቃ ሁሉም፡፡
  • የምን ለቅሶ ነው ክቡር ሚኒስትር?
  • እኔ በየግምገማው ማልቀስ ሰልችቶኛል፡፡
  • እርስዎ እኮ እንባ ስለሚቀናዎት ነው፡፡
  • እናንተ ሰዎች ዓይኔ በእንባ እንዲጠፋ ትፈልጋላችሁ እንዴ?
  • ቆራጥ ይሁኑ እንጂ ክቡር ሚኒስትር?
  • ቆርጬማ ነው የምነግርህ፡፡
  • ምንድነው የቆረጡት?
  • ላለመሞሰን፡፡
  • እንዴ ምኑ ተያዘና?
  • በቃኝ እኔ ሕዝቡን ማገልገል ነው የምሻው፡፡
  • ያድርግልዎት ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • አሜን!

[የክቡር ሚኒስትሩ ሚስት ስልክ ደወሉላቸው]

  • እንዴት ዋልክ?
  • ደህና ዋልሽ?
  • እየፈለግክልኝ ነው፡፡
  • ምንድነው የምፈልግልሽ?
  • የቤት ሠራተኛዋን ነዋ፡፡
  • አንቺ ሴትዮ ይኼን እንኳን መሥራት አትችይም?
  • ምን ነካህ እንዲህ በቀላሉ የሚገኝ ነገር አይደለም፡፡
  • እኔ ታዲያ ከየት ላመጣልሽ እችላለሁ?
  • አንተ ታውቃቸዋለህ ብዬ ነዋ፡፡
  • ምኖቹን ነው የማውቃቸው?
  • ደላሎቹን ነዋ፡፡
  • ምን አልሽ አንቺ?
  • ያለ ደላላ በቀላሉ አይገኙም እኮ ነው የምልህ?  
  • እና እኔ ደላላ ላናግር?
  • ምን ችግር አለው? የቤት ሠራተኛ እኮ በጣም ያስፈልገናል፡፡
  • በቃኝ ብያለሁ እኔ፡፡
  • ምኑ?
  • የድለላው ሥራ፡፡

[የክቡር ሚኒስትሩ የቅርብ ዘመድ ደወለላቸው]

  • ሰላም ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ከየት ተገኘህ ዛሬ እባክህ?
  • አንድ ደስታ ላካፍልዎት ነው፡፡
  • የምን ደስታ?
  • መኪና ገዛሁ፡፡
  • እንኳን ደስ አለህ፡፡
  • ባምላክዎት ክቡር ሚኒስትር፣ ስለዚህ ዛሬ የመኪናዬን የደስ ደስ ምሳ ልጋብዝዎታ፡፡
  • ደስ ይለኛል፡፡
  • በቃ እኔ አሁን መጥቼ እወስድዎታለሁ፡፡

[ክቡር ሚኒስትሩ ዘመዳቸው በገዛው መኪና ምሳ ወደሚበሉበት ቦታ መሄድ ጀመሩ]

- Advertisement -
  • ክቡር ሚኒስትር እርስዎ እኮ በጣም ባለውለታዬ ነዎት፡፡
  • ምን አደረግኩልህ ብለህ ነው?
  • ኮሌጅ እስክጨርስ ድረስ እኮ የረዱኝ እርስዎ ነዎት፡፡
  • ይህማ ግዴታዬ ነው፡፡
  • ይኸው ሥራ ከገባሁ ጀምሮ አጠራቅሜ ይቺን መኪና ገዛሁ፡፡
  • በጣም ቆንጆ መኪና ናት፡፡
  • አመሰግናለሁ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ለመሆኑ የት ገዛሃት?
  • ያው በደላላ ነዋ፡፡
  • ምን?
  • ከደላላ ውጪ ከየት አመጣታለሁ?
  • መኪናውን ከሚያመጣው ኩባንያ ነዋ፡፡
  • እነሱማ ዋጋቸው አይቀመስም፡፡
  • እና በደላላ ነው የገዛኸው?
  • አዎና ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • አሁኑኑ አውርደኝ ከዚህ መኪና ላይ፡፡
  • ለምን ክቡር ሚኒስትር?
  • መነካካት አልፈልግም፡፡
  • ከማን ጋር ክቡር ሚኒስትር?
  • ከደላላ ጋር፡፡

[አንድ ዳያስፖራ ለክቡር ሚኒስትሩ ደወለላቸው]

  • ሰላም ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እንዴት ነህ እባክህ?
  • ዛሬ ምሳ ልጋብዝዎት ፈልጌ ነው፡፡
  • ምን ተገኘ?
  • በዚያው ይመርቁልኛል ብዬ ነው፡፡
  • ምኑን?
  • ቤቴን፡፡
  • መቼ ገዛህ?
  • ያው አገሬ ለመኖር ስለወሰንኩኝ አንድ ቤት ገዛሁ፡፡
  • በጣም ጥሩ አድርገኸል፡፡

[ክቡር ሚኒስትሩ የዳያስፖራው ቤት ምሳ ለመብላት ሄዱ]

  • ምግቡን ራስህ ነው እንዴ የምትሠራው?
  • እኔ እኮ ውጭ ስለለመድኩት ችግር የለብኝም፡፡
  • ሠራተኛ የለህም ማለት ነው፡፡
  • እዚህ አገር እኮ የቤት ሠራተኛ ማግኘት አስቸጋሪ ነው፡፡
  • ለምን ያስቸግራል?
  • ደላሎቹ በጣም አስቸጋሪ ናቸው አሉ፡፡
  • ወይ ደላላ?
  • እንዴ ክቡር ሚኒስትር ይኼን ቤት ራሱ እንዴት ነው ያገኘሁት?
  • ሠርተኸው መስሎኝ?
  • ኧረ ገዝቼው ነው፡፡
  • ከማን ነው የገዛኸው?
  • ያው በደላላ በኩል ነዋ የገዛሁት፡፡
  • እንዴ ደላላ የማይገባበት ነገር የለም ማለት ነው?
  • ክቡር ሚኒስትር እዚህ አገር ሁሉ ነገር በደላላ ነው የሚገኘው፡፡
  • እንዴ አገሪቷን ማን ነው እያስተዳደራት ያለው?
  • እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
  • እኛ ነን ወይስ ደላላ?

[ክቡር ሚኒስትሩ ቢሯቸው ሲገቡ ለጸሐፊያቸው የክፍለ ከተማው ሥራ አስፈጻሚ ዘንድ ደውላ እንድታገናኛቸው ነገሯት፡፡ ደውላ አገናኘቻቸው]

  • ፈለጉኝ ክቡር ሚኒስትር?
  • ምን እየሠራችሁ ነው?
  • ምን ሠራን ክቡር ሚኒስትር?
  • በየመንገዱ የተለጠፉትን ማስታወቂያዎች አይተሃቸዋል?
  • የምን ማስታወቂያ?
  • የድለላ ሥራ ማስታወቂያ፡፡
  • ምን ችግር አለው ታዲያ?
  • አገር ውስጥ የለህም እንዴ?
  • ኧረ አለሁ፡፡
  • ደላላን ማስወገድ አለብን እያልን በየመንገዱ ማስታወቂያቸውን ሲለጥፉ ዝም ልንል?
  • ክቡር ሚኒስትር የገባዎት አልመሰለኝም፡፡
  • ምኑ?
  • የድለላው ዓይነት፡፡
  • ምንም ዓይነት ድለላ አንቀበልም፡፡

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሾፌራቸው ጋር ወደ ቤት እየሄዱ ነው]

  • እስቲ እባክህ ፈልግልኝ?
  • ምን ክቡር ሚኒስትር?
  • የቤት ሠራተኛ፡፡
  • ምን ችግር አለ?
  • ልታገኝልኝ ትችላለህ?
  • አሁኑኑ ነዋ፡፡
  • ከየት ታገኝልኛለህ?
  • የትርፍ ጊዜ ሥራዬ ነው እኮ፡፡
  • ምኑ?
  • ድለላ!
- Advertisement -

በማህበራዊ ሚዲያዎች ይከታተሉን

ከ ተመሳሳይ አምዶች

[ክቡር ሚኒስትሩ የካቢኔ አባል የሆነ አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ ስልክ ደውሎላቸው ሰሞኑን በተካሄደው ድርጅታዊ ጉባዔ ዙሪያ እያወሩ ነው]

ሰላም ክቡር ሚኒስትር፡፡ ሰላም ሰላም፣ እንዴት ነህ? ቢዘገይም እንኳን አደረስዎት ክቡር ሚኒስትር። ለምኑ? ለፓርቲዎ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ እንኳን አደረስዎት ማለቴ ነው። ቆየ እኮ ከተጠናቀቀ? አስቀድሜ ቢዘገይም ያልኩት እኮ ለዚያ ነው...

[ክቡር ሚኒስትሩ የሹፌራቸው ሁኔታ አላምር ብሏቸው ምን እንደሆነ እየጠየቁት ነው]

ዛሬ አነዳድህ አላማረኝም። ምን አሉኝ ክቡር ሚኒስትር? አነዳድህ አላማረኝም! የሆንከው ነገር አለ? ጤንነት እየተሰማኝ አይደለም ክቡር ሚኒስትር። እስኪ ዳር ያዝና አቁመው። እሺ ክቡር ሚኒስትር ...ይኸው። ምን ሆነሃል? ምን ያልሆንኩት አለ ብለው...

[አንድ የመንግሥት ሹም በመንግሥት በኩል የተሰጠ መግለጫ እንዳለ ለማወቅ ክቡር ሚኒስትሩ ጋ ደወሉ]

ሰላም ክቡር ሚኒስትር? ሰላም… ሰላም... እንዴት አለህ? ወዳጆቻችን ደጋግመው እየደወሉ ነው። የትኞቹ? ሰሞኑን ብድር ያፀደቁልን። ምን ፈልገው ነው? ስምምነት ከደረስንበት ጉዳይ ጋር የሚጣረስ መረጃ በመንግሥት መሠራጨቱን ሰምተናል ነው የሚሉት። ምንን በተመለከተ...

[ክቡር ሚኒስትሩ የእጅ ስልካቸው እየጠራ ነው፣ ደዋዩ የታችኛው ክልል ገዥ ፓርቲ ሊቀመንበር መሆናቸው ተመልክተው አነሱት]

ሃሎ! እንዴት አሉ ክቡር ሚኒስትር። ደህና ነኝ። ክቡር ሚኒስትር ባለፈው ወደ አዲስ አበባ የመጣሁ ጊዜ በተመለከትኩት ሳላደንቅዎ ማለፌ ፀፅቶኝ ነው የደወልኩት። ምን አይተህ ነው? እያስገነቡት ያለውን የኮሪደር ልማት። ኦ...ዞር ዞር…...

[ክቡር ሚኒስትሩ ቀኑን ሙሉ ከዋሉበት የሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ተመልሰው ከባለቤታቸው ጋር እያወጉ ነው]

የምን ስብሰባ ላይ ዋልኩ ነበር ያልከኝ? የሥራ አስፈጻሚ። የምን ሥራ አስፈጻሚ? የገዥው ሥራ አስፈጻሚ። ምን ገጥሟችሁ ነው የተሰበሰባችሁት? ለመረጠን ሕዝብ ቃል የገባናቸውን ተግባራት አፈጻጸም የምንገመግምበት የተለመደ ስብሰባ ነው። የገባችሁት ቃል...

[ክቡር ሚኒስትሩ በመኖሪያ ቤታቸው ቁጭ ብለው ከባለቤታቸው ጋር እራት እየበሉ ሳለ የመሬት መንቀጥቀጥ ያሉበትን ሕንፃ አርገበገበው]

ይሄ ነገር አሳስቦኛል። የቱ? ንዝረቱ ነዋ? የምን ንዝረት? የመሬት መንቀጥቀጡ? እ... እሱን እንዴት? ከዚህ በላይ ጠንከር ብሎ ቢመጣ አዲስ አበባ ላይ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ሳስበው ይዘገንነኛል። ምን ይፈጠራል? አብዛኛው ነዋሪ ኮንዶሚኒየም ላይ...

አዳዲስ ጽሁፎች

የጤናው ዘርፍ ባለፉት ስድሥት ወራት

የወባ በሽታ ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገሮች ዋነኛ የጤናና የማኅበራዊ ቀውስ መንስዔ ነው፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት እ.ኤ.አ. በ2024 ያወጣው መረጃም 263 ሚሊዮን ሰዎች የወባ...

የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት በባለሙያ ዓይን

(በጎ ጎኖችና እርምት የሚፈልጉ ጉዳዮች) በዮሐንስ መኮንን በጥር ወር 2016 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ዋና ዋና ኮሪደሮችን በማዘመን ከተማዋን ለነዋሪዎቿና ለጎብኚዎቿ ምቹ ያደርጋታል የተባለ ፕሮጀክት በ43 ቢሊዮን...

በልዩነት ውስጥ ሆነንም እስኪ እንነጋገር

በገነት ዓለሙ ዴሞክራሲ መብቶችና ነፃነቶች የሚሠሩበት የሕዝብ አስተዳደር ነው፡፡ ሰብዓዊ መብቶችንና ነፃነቶችን መኗኗሪ ያደረገ ሥርዓት ነው፡፡ እነዚህ መሠረታዊ መብቶችና ነፃነቶች በተፈጥሮ የተገኙ፣ ሰው በመሆናችን ብቻ...

ለጤናማ የትራፊክ ፍሰትና ለመንገድ ደኅንነት ቅጣት መጣል ብቻውን መፍትሔ አይሆንም!

በአዲስ አበባ ከተማ ለተሽከርካሪዎች ምቹ የሆኑ መንገዶችን እየተመለከትን ነው፡፡ ከአዳዲሶቹ መንገዶች ባሻገር አንዳንድ ነባር መንገዶች የማስፋፊያ ሥራ ታክሎባቸው አገልግሎት ላይ ውለዋል፡፡ ከኮሪደር ልማቱ ጋር...

የግጭት አዙሪት ውስጥ ሆኖ የአፍሪካ ማዕከል መሆን ያዳግታል!

የአፍሪካ ኅብረት 38ኛው የመሪዎች ጉባዔ በአዲስ አበባ ሲካሄድ ብዙ ትዝ የሚሉ ጉዳዮች አሉ፡፡ እጅግ በጣም አሰልቺ፣ ውጣ ውረድ የበዛበትና ታላቅ ተጋድሎ ተደርጎበት ከከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ...

አገሬ ምንተባልሽ – ልብ ያለው ልብ ይበል

በቶማስ በቀለ ይቺ አገራችን ብዙ ተብሎላታልም፣ ብዙ ተወርቶባታልም፣ አገሪቱ በቅኝ ያልተገዛች ብቸኛ አገር (ላይቤሪያን ጨምሮ) ከመሆኗ አኳያ የሚነገርላት ብዙ ጥሩና የሚገርሙ ነገሮች ያሉትን ያህል፣ ከረሃብ...
[the_ad id="124766"]

በማህበራዊ ሚዲያዎች ይከታተሉን