Saturday, November 26, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናጠቅላይ ሚኒስትሩ ወሳኝነታቸውን ያሳዩበት መድረክ

  ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወሳኝነታቸውን ያሳዩበት መድረክ

  ቀን:

  በኢትዮጵያ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ እስከዛሬ ሲደረጉ ከነበሩ ከንግግር ያልዘለሉ የቁርጠኝነት ማሳያዎች አንድ እርከን የዘለለ እንደሆነ የተነገረለት በጥናት ላይ የተመሠረተ ውይይት፣ በቅርቡ በመንግሥት ከፍተኛው አስፈጻሚ አካል ተካሂዷል፡፡ ይህ ለሕዝብ ከወትሮው በተለየ በከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል ወቀሳና ተጠያቂነትን ያስነሳው ውይይት፣ መነሻ ምክንያቱ ታች መሬት ተወርዶ በመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ የዳሰሳ ጥናት መካሄዱ ነው፡፡

  የጥናቱ አቅራቢዎች በውይይቱ ወቅት የችግሩን ስፋትና መጠን ሲያስረዱ፣ ለወትሮው የሐሳብ ልዩነቶቻቸውን ከመጋረጃ በስተጀርባ በመጨረስ ለሕዝብ አንድ ሆነው በመቅረብ የሚታወቁት የኢሕአዴግ ቱባ ባለሥልጣናት፣ በአደባባይ ልዩነቶቻቸውን በግልጽ ያወጡበት ውይይት እንደነበር ታይቷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የአገሪቱ ቁንጮ ባለሥልጣን ሆነው ከመጡበት ጊዜ  ጀምሮ፣ በግልጽ የሥልጣን ባለቤትና የገዥው ፓርቲ አቅጣጫ የመወሰን ሥልጣን እንዳላቸው ያሳዩበትም ነበር፡፡ በተለይ በመሬት፣ በኢንቨስትመንት፣ በፍትሕና በተለያዩ መስኮች በጥናቱ የቀረበው አሳሳቢ ሥጋት ካልተወገደ አደገኛነቱንም በማስጠንቀቅ አውስተዋል፡፡

  ጠቅላይ ሚኒስትሩ አፅንኦት በመስጠት ለአገሪቱም ሆነ ለሕዝቡ አደገኛ የሆነውን የመልካም አስተዳደር ችግር መታገል የሕዝብ አመኔታን እንደሚያስገኝ አስታውቀው፣ የመንግሥት ባለሥልጣናትም በውስጣቸው መደንገጥ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ ከውይይቱ በኋላ ባለሥልጣናት በብሔር፣ በዝምድና፣ በጥቅማ ጥቅምና በመሳሰሉት ከተሳሰሯቸው ኔትወርኮቻቸው እንዲላቀቁም አስጠንቅቀዋል፡፡ ዝርዝሩን ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የትርፍ መጠኑን በ127 በመቶ ያሳደገው አቢሲኒያ ባንክ ካፒታሉን በ2.5 ቢሊዮን ብር እንዲያድግ ወሰነ

  የአቢሲኒያ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩ  ካፒታል በ2.5 ቢሊዮን ብር...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን 55 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ወሰነ

  የአዋሽ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ ዛሬ ህዳር 17 ቀን 2015...

  ከብሔራዊ ባንክ እውቅና ያገኘው ፔይሊንክ አክሲዮን ማህበር ምሥረታውን አካሄደ

  ከገንዘብ ንክኪ ነፃ የሆነ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ለመተግበር ያቀደው...