Wednesday, October 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅበሞጆ ከተማ ባሳለፍነው ሳምንት የተከሰተ አደጋ

በሞጆ ከተማ ባሳለፍነው ሳምንት የተከሰተ አደጋ

ቀን:

ግን ይኸን አይካደኝ

ብዙዎች ካወቁ ማሰብ መሥራቴን ቅን

እንዳሻው አንዳንዱ ነህ ይበለኝ ሰይጣን

ስሳሳት አይማረኝ ባልሳሳት ፈጥሮ

የሐሰትን ጉድፍ በራሴ ከምሮ

ይስደበኝ እንዳሻው ያጐሳቁለው ስሜን

ሰው መጥፎ ነው ብዬ አላወጣም እርሜን፡፡

ዐውቃለሁኝና ሰው ሰው ከተባለ

ጠማማ ግድ የለሽ ቅንም ሰው እንዳለ፡፡

ነገር ግን ማንም ሰው ይጥላኝም ይውደደኝ

አገሬን ወገኔን መውደዴን አይካደኝ፡፡

ጥፋት የሰው ባሕርይ መሆኑን ስለማውቅ

ስኅተተኛ ብባል ምንም አልደነቅ፡፡

በማንኛው ሰው ዘንድ በሚታይ ጉድለት

በሰዎች ፊት በደል በግዜር ፊት ኃጢአት

አልፈጸምሁኝም ብል ነው ፍጹም ሐሰት፡፡

ነገር ግን ማንም ሰው ይጥላኝም ይውደደኝ

አገሬን ወገኔን መውደዴን አይካደኝ፡፡

ዐውቃለሁ ምን ጊዜም እንደምለይ ካለም

ባደጋ በርጅና ወይንም በሕማም፡፡

ግን ከዚሁ ጋራ ይህ አይረሳኝም

ሞት ከሕይወቴ እንጂ ካገሬ አይለየኝም፡፡

ድሮ ሳልወለድ ነበርሁኝ ባገሬ

ባገሬ ነውና መነሻዬ ሥሬ

ካገሬም አልለይ ሙቼ ተቀብሬ

ይቀጥላልና ባገሬ ላይ ዘሬ፡፡

ባጠፋ ውቀሱኝ አጥፊ ነው ብላችሁ

ካሻም አጥፊ በሉኝ ከጥፋቴ አልፋችሁ፡፡

ነገር ግን ማንም ሰው ይጥላኝም ይውደደኝ

አገሬን ወገኔን መውደዴን አይካደኝ፡፡

  • አቤ ጉበኛ፣ እሬትና ማር

********************

ገደብህን እወቅ

መወገድ የሚገባው ህማም አንዱ ምንጭ ገደብን አለማወቅ ነው – የት ጋ ራስህን መግታት እንዳለብህ አለማወቅ፡፡

የነፃነትህን ሚዛን፣ የሀዘን የደስታህን መስፈርት፣ ሌሎች ባነፁት መስተዋታማ ሰንዱቅ ልኬት ኣትቁረጥ፡፡

ጠቢቡ እንዲህ ይላል፣ የፍፁም ነፃነት መከሰቻዎችና ምሳሌዎች እንስሳት ናቸው፡፡

በገደብ ውስጥ መኖር የተፈጥሮህ ነው፤ ልክ የዓሳ ተፈጥሮ መዋኘት፣ የወፍ ተፈጥሮም መብረር እንደሆነው ሁሉ፡፡ በኣዕዋፋት ሰማይ ውስጥ ነፃነቱን እሚፈልግ ዓሳ እንደምን ያለው ዓሳ ነው?

ነፃነትህን አለአግባብ በመጠቀም በራስህ ላይ ስንኩልነትን አታምጣ፡፡ የወርቃማዋን አማካይ ሕግ ተከተል፡፡ ወርቃማዋ አማካኝ ማለት፣ ለዛሬህም ለነገህም፣ ለራስህም ለብጤ የሰው ዘር ሁሉም፣ መልካምን በምታደርግ የሕግና የሥርዓት ገደብ ውስጥ መኖር ማለት እንጂ ሌላ ማለት አይደለችም፡፡

በፍላጎትህ ላይ ሉጋም በማበጀትና በነፃነትህ መሃል የራስህን ሚዛን አግኝ፡፡ ወርቃማዋን አማካኝ ለማግኘት ስትጣጣር ብትወድቅ ወይም መንገድ ብትስት፣ ራስህን ፈጥነህ ሰብስበህ  ጉዞህን እንደገና ጀምር፡፡

ልብ በል፤ በጎቹ ካመለጡ በሁዋላም እንኳ ጋጣቸውን መጠገን እጅግም መዘግየት አይደለም፡፡

ይህ የመማር ሒደት ነው፡፡ ከውድቀትህ ለመማር የመብቃትን ያህል ትሁት ሁን፡፡ ሲያስፈልግም ድርቅ ብለህ ለመገኘት ነፃ የመሆንን ያህል ተለጣጭ ሁን፡፡

  • ኦ’ታም ፑልቶ፣ የፈላሱ መንገድ፣ 2006 ዓ.ም.

*********************

ግራኝነትና የጤና ተፅዕኖው

ግራኝ መሆን ከዘር ጋር የሚገናኝ አይደለም፡፡ ሳይንቲስቶች ሰዎች ለምን ግራኝ እንደሚሆኑ በእርግጠኝነት አያውቁም፡፡ ቢሆንም ግን ዘር 25 በመቶ ለግራኝነት አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ በቴክሳስ ኦስቲን ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ሮናልድ ይዮ ይናገራሉ፡፡ ቢሆንም ግን ቁመትና የአእምሮ ብሩህነት ላይ ተፅዕኖ የማድረግ ያህል ዘር ግራኝነትን የመወሰን አቅም የለውም፡፡

አንድ የእንግሊዝ ጥናት እንደሚያሳየው፣ ግራኝነት በእርግዝና ወቅት ከሚኖር ጭንቀት ጋር ይያያዛል፡፡ በጣም የተጨነቁ ነፍሰ ጡሮች ማህፀን ውስጥ ያሉ ልጆች፣ ብዙ ጊዜ ፊታቸውን ከቀኝ ይልቅ በግራ ይነካሉ፡፡ ይህ አንድ ሕፃን ግራኝ መሆኑን የማወቂያ የመጀመሪያው ምልክት መሆኑን ሳይንቲስቶች ይጠቁማሉ፡፡ እ.ኤ.አ. 2008 በእናቶችና አምስት ዓመት በሞላቸው ሕፃናት ልጆቻቸው ላይ በስዊድን የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው፣ በእርግዝናቸው ወቅት ጭንቀት የነበረባቸው እናቶች ልጆች ቀኝም ግራም እጃቸውን እኩል መጠቀም የሚችሉ ወይም ግራኞች ይሆናሉ፡፡ በሌላ ጥናት ደግሞ ሲወለዱ አነስተኛ ክብደት ያላቸው ወይም በዕድሜ ከገፉ እናቶች የሚወለዱ ሕፃናት ግራኝ የመሆን ዕድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡

ግራኝነት መንትዮች ላይ በብዛት ያጋጥማል፡፡ እ.ኤ.አ. 1996 የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው፣ ፍፁም አንድ ዓይነትና አንዳይነት ከሆኑ መንትዮች 21 በመቶ የሚሆኑት ግራኝ ናቸው፡፡

ግራኝ መሆን የአዕምሮ የግራውን ክፍል እንዲጠቀሙ የግድ ይላል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ቀኝ የሆኑ ሰዎች ቋንቋን ለመረዳት የግራዉን የአዕምሯቸው ክፍል ይጠቀማሉ፡፡ ይህ ማለት ግን ግራኝዎች የቀኙን የአዕምሯቸው ክፍል ይጠቀማሉ ማለት አይደለም፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት 70 በመቶ ግራኝዎች የግራ አዕምሯቸውን ክፍል ይጠቀማሉ፡፡

ግራኝ መሆን ለአዕምሮ ሕመም ተጋላጭ ከመሆን ጋር ይያያዛል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2013 በያል ዩኒቨርሲቲ የተሠራ ጥናት እንደሚያሳየው፣ ግራኝዎች እንደ ስኪዞፍሬኒያ ላሉ የአዕምሮ ሕመሞች የመጋለጥ ዕድል አላቸው፡፡

(ካለፈው ሳምንት የሲኤንኤን ዘገባ የተወሰደ)

*****************************

የስፔን ከበሬ ጋር ድብድብ በትምህርት መልክ እንዲስጥ መታቀዱ ተቃውሞ አስነሳ

የስፔን ከበሬ ጋር ድብድብ (ቡል ፋይቲንግ) የተለመደ ነው፡፡ ሆኖም ልማዱ የመጣው በትምህርት ቤት እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት ስለተሰጠ ሳይሆን፣ በቀደምት ጊዜያት ልማድ ስለነበረ ነው፡፡ ሆኖም የስፔን ትምህርት ሚኒስቴር ከ15 እስከ 17 የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ጨርሰው ወደ ሙያ ሥልጠና የሚገቡ የመንግሥት ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ የቡል ፋይቲንግ ትምህርት እንዲወስዱ ማቀዱን አሳውቋል፡፡ ይህ ግን በመቶ ሺዎች በሚቆጠሩ የስፔን ዜጐች ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡

ለንድፈ ሀሳብና ለልምምድ 2 ሺሕ ያህል ሰዓት የሚፈጀው ትምህርቱ፣ በትምህርት ሚኒስቴር የታቀደው፣ በስፔን ከበሬ ጋር ድብድብ እያሽቆለቆለና የሕዝቡን ፍላጐት እያጣ በመምጣቱ ነው፡፡ ሆኖም ዕቅዱን 300 ሺሕ ያህል ሰዎች ተቃውመው ፊርማ አሰባስበዋል፡፡

የስፔን ትምህርት ሚኒስቴር ግን ጉዳዩን ተከላክሏል፡፡ ‹‹ከበሬ ጋር የሚደረግ ድብድብ በስፔን የረዥም ጊዜ ታሪክ ያለው ባህል ነው›› ሲል አሳውቋል፡፡

ስፔንን የሚያስተዳድረው ፒፕልስ ፓርቲ ለቡል ፋይቲንግ ትልቅ ስፍራ እንደሚሰጥ ይነገራል፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2013 ጀምሮም ቡል ፋይቲንግ በስፔን አንድ የባህል እሴት እንዲሁን እየሠራ እንደሚገኝ ዘርዲያን ዘግቧል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመገረም እየተመለከቱ አገኟቸው]

ምንድነው እንዲህ ቀልብሽን የሳበው? ስለሰላም ኖቤል ሽልማት ዜና እየተመለከትኩ ነበር። እና...

የወሎ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መመሥረትና የአማራ ክልል ጥያቄ

አማራ የኢሕአዴግ አንዱ መሥራችና አጋር ከሆነው ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ...

የሽንኩርት ዋጋ ሰማይ የነካበት ምክንያት ምንድነው?

ባለፉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት የሸማቾችን ኪስ ካስደነገጡ መሠረታዊ ከሚባሉ...

የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ኤግዚቢሽን ማዕከልን እንዲያስተዳድር የተሰጠው ኮንትራት ለምን ተቋረጠ?

በአዲስ አበባ ከተማ ለንግድ ትርዒት ዝግጅት ብቸኛ በመሆን የሚጠቀሰው...