Tuesday, December 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየባህር ትራንስፖርትና የሎጅስቲክስ አመራሮች በመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ ተወያዩ

የባህር ትራንስፖርትና የሎጅስቲክስ አመራሮች በመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ ተወያዩ

ቀን:

– የመዋቅር ማሻሻያ እንደሚደረግ ተጠቁሟል

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት አመራሮች በድርጅቱ አሠራር በሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ ጥቅምት 26 እና 27 ቀን 2008 ዓ.ም. በድሬዳዋ ከተማ መምከራቸውን፣ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አህመድ ቱሳ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚው እንደገለጹት የዕቃ መዘግየት፣ በደረቅ ወደቦች ላይ የፋሲሊቲ አለመሟላት፣ የዋጋ ውድነትና ከጭነት ላይ የዕቃዎች ሥርቆት አመራሮቹ ከተወያዩባቸው የመልካም አስተዳደር ዕጦት ችግሮች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድም የውይይቱ አጀንዳ እንደነበር ማወቅ ተችሏል፡፡

በድሬዳዋው የውይይት መድረክ የድርጅቱ መዋቅር አጀንዳ እንዳልነበር ሥራ አስፈጻሚው ቢናገሩም፣ የመዋቅር ማሻሻያ እንደሚደረግ ግን ጠቁመዋል፡፡ እሳቸው ይህን ቢሉም የሪፖርተር ምንጮች ግን የሚደረገው ማሻሻያ ሳይሆን መዋቅራዊ ለውጥ ሊባል የሚቻል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

እንደ ምንጮቹ ገለጻ ምን ዓይነት መዋቅራዊ ለውጥ ማድረግ እንደሚገባ የውጭ ድርጅት እንዲያጠና ታስቦ የነበረ ቢሆንም፣ በመጨረሻ በድርጅቱ ውስጥ በተቋቋመ ኮሚቴ ጥናቱ ተሠርቷል፡፡

በጥናቱ መሠረት በርካታ የሥራ መደቦች ክፍት ተደርገው ሠራተኞች በትምህርት ዝግጅታቸውና በሥራ ልምዳቸው፣ ለተለያዩ የሥራ ኃላፊነቶች እንዲያመለክቱም ተደርጓል፡፡

ከዚህ ቀደም ሦስቱን ድርጅቶች ማዋሀድ ያስፈለገው ድርጅቶቹ በተበጣጠሰ ሁኔታ ይሰጡት የነበረው አገልግሎት፣ ደንበኞች የተቀናጀ አገልግሎት እንዳያገኙ እንቅፋት መሆኑ ስለታመነበት ነበር፡፡ ስለዚህም ወደ አገር ውስጥ ለሚገባና ለሚላክ ጭነት የባህርና የየብስ ትራንስፖርት፣ የሎጅስቲክስና የደረቅ ወደብ አገልግሎትን ጊዜው በሚጠይቀው የተቀላጠፈ ደረጃ ለመስጠት ውህደቱ አስፈላጊ እንደሆነ በወቅቱ ተገልጾ ነበር፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...