Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየድሮን አጠቃቀም ሕግ ሊዘጋጅ ነው

የድሮን አጠቃቀም ሕግ ሊዘጋጅ ነው

ቀን:

የድሮን አገልግሎት አስፈላጊ እየሆነ በመምጣቱ መንግሥት የድሮን ፈቃድና አስተዳዳር ሕግ ሊያዘጋጅ መሆኑ ተሰማ፡፡

በድሮን በረራ የሚሠሩ የቅየሳ፣ የቅኝት፣ የፊልም ቀረፃና የፎቶግራፍ ሥራዎች ቢኖሩም፣ ኢትዮጵያ እስካሁን የድሮን ፈቃድ አሰጣጥ ሕግ የላትም፡፡ የተለያዩ የውጭ ኩባንያዎች ለተለያዩ ሥራዎች ድሮን አስገብቶ ለመጠቀም ቢፈልጉም ይህን የሚፈቅድ ሕግ ባለመኖሩ መቸገራቸውን ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ በዚህም የተነሳ አንዳንድ ግለሰቦች ደብቀው ወደ አገር ሲያስገቡ፣ ሌሎች ደግሞ በኤርፖርት ጉምሩክ እንደተያዘባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ በልዩ ፈቃድ አስገብተው ሥራ ላይ ያዋሉም እንዳሉ ለመረዳት ተችሏል፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁነኛው ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የአገሪቱ የአቪዬሽን ሕግ የሚደነግገው ማንኛውም በራሪ አካል ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ፈቃድ ማግኘት እንዳለበት ነው፡፡ ማንኛውም ድርጅት ወይም ግለሰብ ድሮን ለማስገባትና ለመጠቀም ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ፈቃድ ማግኘት ይኖርበታል፡፡ ይሁን እንጂ እስካሁን ባለሥልጣኑ የድሮን ፈቃድ ደንብ እንደሌለው ኮሎኔል ወሰንየለህ ተናግረዋል፡፡

ድሮን አዲስ ቴክኖሎጂ እንደመሆኑ መጠን ብዙ አገሮች የድሮን ፈቃድ ሕግ እንደሌላቸው የገለጹት ኮሎኔል ወሰንየለህ፣ የበለፀጉት አገሮች እንኳ ገና ሕግ በማውጣት ላይ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ የድሮን አገልግሎት እየሰፋ በመምጣቱ የድሮን ሕግ ማዘጋጀት አስፈላጊ እየሆነ እንደመጣ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የድሮን ፈቃድ ደንብ እንደሚያዘጋጅ የገለጹት ኮሎኔል ወሰንየለህ ባለሥልጣኑ ከመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ጋር በቅርበት እንደሚሠራ አስረድተው፣ ረቂቅ ሕግ ከተዘጋጀ በኋላ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በሙሉ ውይይት እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡ ድሮን የሚበርበት ከፍታ መጠንና በድሮን ላይ ስለሚገጠሙ የመሣሪያ ዓይነቶች በፈቃድ አሰጣጥ ሕጉ ውስጥ እንደሚካተት ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን አሠራሩን በማዘመን ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በርካታ የአቪዬሽን ባለሙያዎች እያሠለጠነ ነው፡፡ ከጥቂት ዓመታት በፊት ከፍተኛ የባለሙያ እጥረት (በተለይም የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች) የነበረበት ባለሥልጣኑ፣ በአሁኑ ወቅት ከራሱ አልፎ ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች የሚመጡ ባለሙያዎች ማሠልጠን ጀምሯል፡፡ ለማሠልጠኛ ማዕከሉ ከፍተኛ ወጪ በመመደብና የተለያዩ የማስተማሪያ መሣሪያዎች በማሟላት፣ ማዕከሉ የዓለም አቀፍ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ዕውቅናን እንዲያገኝ ጥረት እያደረገ ነው፡፡ በተጨማሪም ባለሥልጣኑ ዘመናዊ ራዳርና ሌሎች የበረራ ማቆጣጠሪያ መሣሪያዎች ገዝቶ በመግጠም ላይ ይገኛል፡፡

ባለሥልጣኑ በቅርቡ በአሜሪካ ፌደራል አቪዬሽን አድሚኒስትሬሽንና በዓለም አቀፍ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ኦዲት ተደርጐ የብቃት ማረጋገጫ አግኝቷል፡፡

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...