Wednesday, December 7, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየኢትዮጵያ ልማት ባንክ በተበዳሪዎች ድርሻ ላይ ማሻሻያ አደረገ

  የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በተበዳሪዎች ድርሻ ላይ ማሻሻያ አደረገ

  ቀን:

  – ለሁለተኛው ስትራቴጂክ ዕቅድ 112 ቢሊዮን ብር ብድር ሊያቀርብ ነው

        የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የ70/30 የብድር አቅርቦት ሥርዓቱ ላይ መጠነኛ ማሻሻያ አደረገ፡፡

  ላለፉት በርካታ ዓመታት የአገር ውስጥ ባለሀብቶች ሲያቀርቡት የነበረው የባለሀብቶች የብድር ድርሻ ይቀንስ ጥያቄን ከግምት በማስገባት ማሻሻያ መደረጉን፣ ከሪፖርተር ጋር ቆይታ ያደረጉት የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ባህረ ገልጸዋል፡፡ 

  በመሆኑም በማኑፋክቸሪንግ፣ በግብርናና እንዲሁም በግብርና ማቀነባበር ዘርፎች የሚሰማሩ የአገር ውስጥ ባለሀብቶች ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብድር በሚጠይቁበት  ጊዜ የሚጠበቅባቸው የብድር ድርሻ፣ ከቀድሞው 30 በመቶ ወደ 25 በመቶ ዝቅ መደረጉንና ይህንን ሲያሟሉም 75 በመቶ የፕሮጀክት ብድር ባንኩ እንደሚያቀርብ ፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል፡፡

  የአገር ውስጥ ባለሀብቶች ከኢትዮጵያ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ባደረጉባቸው ተደጋጋሚ ጊዜያት የብድር ድርሻ እንዲቀነሰላቸው ሲጠይቁ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ በተደጋጋሚ ባቀረቡት ጥያቄም ድርሻቸው አሥር በመቶ ወይም 20 በመቶ እንዲሆንላቸው ሲወተውቱ ነበር፡፡

  የተደረገው ማሻሻያ የባለሀብቶችን ጥያቄ የሚመለከት እንደሆነ የተጠየቁት አቶ ኢሳያስ፣ ‹‹ከዚህ በታች መውረድ ማለት የፕሮጀክቱ ባለቤትነት የመንግሥት ሆነ ማለት ነው፡፡ የባለሀብቶቹ ድርሻ በቀነሰ ቁጥር የባለቤትነት መንፈሳቸውን ይገድባል፤›› ብለዋል፡፡

  ባንኩ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን 112 ቢሊዮን ብር ለመፍቀድ እንዲሁም ከዚህ ውስጥ 104 ቢሊዮን ብር ለማስተላለፍ ማቀዱን ገልጸዋል፡፡

  ይህም ማለት ከመጀመርያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን በሦስት እጥፍ የሚበልጥ ነው፡፡ በመጀመርያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን ለመፍቀድ የታቀደው የብድር መጠን 44 ቢሊዮን ብር ሲሆን፣ 38 ቢሊዮን ብር ያህሉን ደግሞ ለማስተላለፍ አቅዶ ነበር፡፡

  የዕቅዱ አፈጻጸምም 39 ቢሊዮን ብር ብድር በመፍቀድ፣ 26 ቢሊዮን ብር ማስተላለፉን፣ እንዲሁም ለማስመለስ ካቀደው 14 ቢሊዮን ብር ውስጥ 13 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን አቶ ኢሳያስ አስረድተዋል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመው ጭፍጨፋና ሥጋቱ

  ኦሮሚያ ክልል ከቀውስ አዙሪት መላቀቅ ያቃተው ይመስላል፡፡ ከ200 በላይ...

  እናት ባንክ ካፒታሉን ወደ አምስት ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ወሰነ

  መጠባበቂያን ሳይጨምር የባንኩ የተጣራ ትረፍ 182 ሚሊዮን ብር ሆኗል እናት...

  ቡና ባንክ ዓመታዊ ትርፉን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ማሻገር ቻለ

  ቡና ባንክ በ2014 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ የትርፍ ምጣኔውን ለመጀመርያ...