Sunday, June 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊለመልካም አስተዳደር እንቅፋት የሚሆኑ አመራሮች ተጠያቂ የሚደረጉበት አሠራር ተዘረጋ

ለመልካም አስተዳደር እንቅፋት የሚሆኑ አመራሮች ተጠያቂ የሚደረጉበት አሠራር ተዘረጋ

ቀን:

– የሪፖርተር ዘጋቢ መልካም አስተዳደር ለማስፈን ከተጠራ ስብሰባ ተባረረ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ድሪባ ኩማ ከዚህ ዓመት ጀምሮ ችግር የሚፈጥር አመራር ተጠያቂ የሚሆንበት አሠራር ተዘርግቷል አሉ፡፡  

ከጥቅምት 25 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ቀናት በተካሄደው ስብሰባ፣ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን መወሰድ ስላለባቸው ዕርምጃዎች አስተዳደሩ ውይይት አድርጓል፡፡

- Advertisement -

ስብሰባውን ከንቲባ ድሪባ፣ ምክትል ከንቲባ አባተ ስጦታውና የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተወልደ ገብረ ፃድቃን መርተውታል፡፡ ስብሰባው ያነጣጠረው ከ2008 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ በሚደረገው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን በከተማው የተንሰራፋውን ሙስና ወይም ኪራይ ሰብሳቢነት በማስወገድ፣ የአገልግሎት አሰጣጡን እንዴት ማስተካከል ይቻላል በሚለው ጉዳይ ላይ ነው፡፡ ከንቲባ ድሪባ እንደተናገሩት፣ የከተማው አስተዳደር መልካም አስተዳደርን በማስፈን የኅብረተሰብን እርካታ ለመጨመር አስተዳደሩ የመዋቅር ለውጥ አድርጓል፡፡ የመዋቅር ለውጡንም በማገባደድ ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ከንቲባው አስተዳደሩ ባለፉት አምስት ዓመታት መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ጥረት ቢያደርግም አለመሳካቱን ገልጸው፣ ከዚህ ዓመት ጀምሮ ሁሉም መሥሪያ ቤቶች ዕቅዳቸውንና ስኬታቸውን ለመንግሥት፣ ለፓርቲና ለሕዝብ ይፋ ያደርጋሉ፡፡ በዚህ ወቅት ችግር እንዳለበት የተስተዋለበት አመራር ተጠያቂ ይሆናል፡፡ በዚህ ስብሰባ ላይ የካቢኔ አባላት፣ የክፍላተ ከተማና የወረዳ አመራሮች የታደሙ ሲሆን፣ በቡድን ስብሰባ በማካሄድ አመራሮቹ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡

ከቀረቡት አስተያየቶች ወይም ጥያቄዎች መካከል የአንድ ለአምስትና የለውጥ አደረጃጀቶች በመንግሥት መዋቅር መግባት እንደሌለባቸው፣ ከዲፕሎማ በታች ያላቸው የወረዳ አመራሮች ያለ ካቢኔ ውሳኔ መነሳታቸው አግባብ አለመሆኑና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የሚዲያ አካላት በተለይም የአስተዳደሩ መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ ከለላ ሊሰጠው እንደሚገባ የሚሉት ይገኙበታል፡፡

የአንድ ለአምስት አደረጃጀት ከድርጅት መዋቅር በተጨማሪ ወደ መንግሥት መዋቅር መግባቱ ይታወቃል፡፡ የለውጥ አደረጃጀቶች የሚባሉት ማለትም በአንድ ለአምስት ውስጥ ብርቱ የተባሉ ግለሰቦች ያሉበት አደረጃጀት ሲሆን፣ ይህም አደረጃጀት በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ገብቷል፡፡

እነዚህ አደረጃጀቶች በአስተዳደሩ መዋቅር ውስጥ እንዲገቡ መደረጉ አግባብ አይደለም ያሉ የአስተዳደሩ አመራሮች፣ አደረጃጀቶቹ በመንግሥት መዋቅር መግባታቸውና መዋቅር መለጠጥና የሥራ መደራረብ አምጥቷል በማለት አስተያየቶቻቸውን አቅርበዋል፡፡

ከዲፕሎማ በታች ያሉ የወረዳ አመራሮች ከኃላፊነት እንዲነሱ መደረጉ አግባብ መሆኑን አስተያየት የሰጡ አመራሮች ቢስማሙም፣ አመራሮቹ የተነሱበትን መንገድ ግን ተቃውመዋል፡፡ ምክንያቱም የተነሱበትን ውሳኔ ካቢኔው ካለማፅደቁም በላይ ከፍተኛ አመራሮችም በጉዳዩ ላይ አልተወያዩበትም ብለዋል፡፡

ውሳኔው ተግባራዊ በሚሆንበት ወቅት ችግር ቢፈጠር ኃላፊነቱን ማን ይወስዳል? የሚል ጥያቄ ለአወያዮቹ ቀርቧል፡፡ የወረዳ ተነሺዎች በጥቃቅንና አነስተኛ ማኅበር ተደራጅተው ኑሮአቸውን እንዲገፉ የተወሰነ ሲሆን፣ ለተነሽ ሴት አመራሮች በተለይም በትምህርት ላይ ከሆኑ በልዩ ድጋፍ የአንድ ዓመት ጊዜ እንዲሰጣቸውና ትምህርታቸውን እንዲያጠናቅቁ ተወስኗል፡፡

በፌዴራል መንግሥት እንደተደረገው ሁሉ በአዲስ አበባም መልካም አስተዳደር ለማስፈን የምርመራ ጋዜጠኝነት ሊበረታታ እንደሚገባ ተጠቅሷል፡፡ ከዚህ አንፃር የአዲስ አበባ መገናኛ ብዙኃን የምርመራ ጋዜጠኝነት እንዲያከናውን ከለላና ጥበቃ ሊደረግለት እንደሚገባ ከአመራሮቹ ሐሳብ ቀርቧል፡፡ ይህም በዕቅዱ ሰነዱ ላይ እንዲካተት ተጠይቋል፡፡

ነገር ግን ከዚህ መርህ በተጣረሰ መልኩ በዚህ ስብሰባ ተገኝቶ የነበረው የሪፖርተር ዘጋቢ ከስብሰባው እንዲወጣ ተደርጓል፡፡ የፌደራል መንግሥትም ሆነ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ የምርመራ ጋዜጠኝነት ትኩረት እንደሚሰጡ ቢገልጹም፣ በተግባር እየታየ ያለው ግን ከዚህ የራቀ እንደሆነ በተለይ በግል ፕሬስ የተሰማሩ ጋዜጠኞች እየተናገሩ ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ የሚዲያው ተፅዕኖ ፈጣሪነት ያስፈልጋል እየተባለ በአደባባይ ቢነገርም፣ በተለይ የግሉን ፕሬስ መረጃ በመንፈግና ከስብሰባ ውስጥ በማስወጣት በተቃራኒው ችግር የሚፈጥሩ በየቦታው እየታዩ መሆኑ በችግርነት እየተወሳ ነው፡፡     

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...