Wednesday, March 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ 12 ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋሉ

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ 12 ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋሉ

ቀን:

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ 12 ሰዎች ዛሬ መጋቢት 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ሪፖርተር ከታሳሪዎቹ ቤተሰቦች ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ሌሎች በቁጥጥር ሥር የዋሉ ግለሰቦች አቶ ፍቃዱ ማኅተመ ወርቅ፣ አቶ አንዷለም አራጌ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ ጦማሪ ማኅሌት ፈንታሁን፣ ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ፣ ጦማሪ ዘላለም ወርቃገኘሁ፣ ወ/ሮ ወይንሸት ሞላ (የሰማያዊ ፓርቲ አባል)፣ አቶ ይድነቃቸው አዲስ፣ አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ አቶ ተፈራ ተስፋዬና አቶ አዲሱ ጌታነህ ናቸው፡፡

ግለሰቦቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወላጅ እናት በመኖሪያ ቤታቸው ባዘጋጁላቸው የምሳ ግብዣ ላያ ተሰባስበው በነበሩበት ወቅት መሆኑንም ሪፖርተር ማወቅ ችሏል፡፡ የታሰሩበት ምክንያት ግን ምን እንደሆነ አልታወቀም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...

አወዛጋቢነቱ የቀጠለው የአዲስ አበባ የጤፍ ገበያ

ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጤፍ የተከሰተውን የዋጋ ንረት...